የሲዳማ ህዝብ የኣገሪቱን ህገ መንግስታት መሰረት ባደረገ መልኩ ያቀረበው የክልል ጥያቄ ምላሽ እስኪያገኝ ድረሰ እንደምታገል የሲዳማ ነጻነት ግንባር ኣስታወቀ፤ ለሲዳማ ህዝብ ጥያቄዎች መንግስት ተገቢውን ምላሽ እንዲሰጥ ጠየቀ

የሲዳማ ነጻነት ግንባር ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት ካላ ቤታና ሆጤሳ ከሰይፌ ነበልባል ሬድዮ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ  የሲዳማ ህዝብ ትግል እንደቀጠለ መሆኑን ገልጸው የሲዳማ ህዝብ ለነጻነቱ ከምኒሊክ ጊዜ ጀምሮ  በመታገል ላይ ነው ብለዋል። ኣክለውም ባለፉት ኣስር ኣመታት የክልል ጥያቄን እና ሌሎች የመልካም ኣስተዳደር ችግሮችን በተመለከተ የሚያነሳቸው ጥያቀዎች በግዥው ፓርቲ ዘንድ ምላሽ ሳያገኙ መቅረታቸውን ግልጸዋል። ገዥው ፓርቲ የሲዳማ ህዝብ በሰላማዊ መንገድ ያቀረበውን የክልል ጥያቄ በጉልበት የማዳፈን ስራ በመስራት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
የገዥው ፓርቲ የሲዳማ መብት ተከራካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችን የሲዳማ ህዝብ ኣይደግፋቸውም በማለት የሚያስወራው ህዝብን ለማደናበር እንጂ እውኔታ ኖሮት ኣይደለም ባይሆን የሲዳማ ህዝብ ለመብቱ የሚታገሉለትን ጠንቅቆ ያውቃል ብለዋል።
የሲዳማ ህዝብ የክልል ጥያቄ ትክክለኛ መሆኑን ገዥው ፓርቲ ጠንቅቆ ስለምያውቅ ህዝባዊ ጥያቄውን ላለመመለስ የተለያዩ የማወናበጃ ፖሮፖጋንዳዎችን በማስወራት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል።
የሲዳማ ህዝብ ህገ መንግስታዊ ጥያቄ ምላሽ እስክያገኝ ድረስ እንደምታገሉ ኣስታውቀዋል። 
ለሙሉ ቃለ ምልልስ የሚቀጥለውን ሊንክ ይጫኑ: ከካላ ቤታና ሆጤሳ ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር