በቅርቡ ሲዳማ ውስጥ የምካሄደውን የኣካባቢ ምርጫ ለማሸነፍ ብቸኛው ኣማራጭ የህዝቡን ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎችን መመለስ ብቻ ነው


ከሁለት ወራት በኃላ በኢትዮጵያ ብሎም በሲዳማ የምከሄደው የኣከባቢ ምርጫ ላይ ለመሳተፊ ሃዋሳን ጨምሮ በሲዳማ ዞን ውስጥ ኣራት የምሆኑ የፖለቲካ ድርጅቶች ተመዝግበው የምርጫ ምልክት መውሰዳቸውን ከኣገሪቱ ምርጫ ቦርድ ሰምተናል። እነዚህ በሲዳማ እንወዳደራለን ብለው የምርጫ ምልክት የወሰዱት የፖለቲካ ፓርቲዎች የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ(ሲኣን)፤ ደኢህዴን_ኢህኣዴግ፤ኢዴፓ እና ኢህኣፓ ናቸው። በነገራችን ላይ በምርጫ ቦርድ ኣደራጃጀት ሃዋሳ እና ሲዳማ የምል ክፍፍል የለም። በኣሁኑ ጊዜ ሃዋሳ እና ሲዳማ ተብለው የተከፋፈሉ ኣከባቢዎችን የምወክሉ ሰዎች በማንኛውም መንገድ የሲዳማ ተወላጆች መሆን ኣለባቸው። ምክንያቱ በዚህ ምርጫ ላይ ብቻ ሳይሆን በተለይ ከሶስት ኣመት በኃላ በምካሄደው ብሄራዊ ምርጫ በተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ የሲዳማን ብሄር የምወክሉ ግለሰቦች ከሁሉም የሲዳማ ኣካባቢዎች መምጣት ስላለባቸው ነው። ለምሳሌ ያህል ከሃዋሳ የምወከሉት ግለሰብ የሲዳማ ተወላጅ ካልሆኑ የሲዳማን ህዝብ በተወካዮች ምክር ቤት ውስጥ የምወክሉት ተወካዮች ቁጥር ያሳንሳል በተጎዳኝ በሃዋሳ የምያሸንፈው የሌላ ብሄርሰብ ተወላጅ ለብሄረሰቡ ተጨማር የተወካይ ቁጥር ይጨምርለታል ማለት ነው። ይህ ማለት ቀድሞም ብሆን የሲዳማ ህዝብ ብዛት እና በተወካዮች ምክር ቤት ያለው ውክልና ተመጣጣኝ ኣይደለም የምል ኣመለካከት ያጠናክራል።
ወደ ጉዳያችን ስንመለስ፤ በዚህ ጽሁፍ በኣራቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች ላይ ትኩረት ከመሰጠት ይልቅ በሁለቱ ላይ ማለትም በሲኣን እና በደኢህዴን ላይ ትኩረት ለመሰጠት ፈልጋለሁ። እስቲ እነዚህ የፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይዘው ነው የቀረቡ? ለሲዳማ ህዝብ የምጠቅም ምን ይዘዋል? በምሉት እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ እንጫዎት።
በኣጠቃላይ በኣገሪቱ ደረጃ ሲታይ ‹‹በግንባታ ሒደት ላይ ነው›› የሚባለው የኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ከዜጎቹ፣ ከምሁራን፣ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ፍላጎት ካላቸው ሦስተኛ ወገን የውጭ አገር ተቋማትና አገሮች እንዲሁም ዜጎች፣ ከፖለቲካ ፓርቲዎችና ከሌሎች አካላትና ግለሰቦች የሚነሱትን ጥያቄዎች በሒደት የመመለስ ፍላጎት ያለው አይመስልም እንደሪፖርተር ጋዜጣ ዘጋባ፡፡
የጋዜጣው እንደምለው ከሆነ፤ ለማቀራረብ እንኳን የሚከብደው ተቃዋሚ ፓርቲዎችና ኢሕአዴግ የሚከተሉት ርዕዮተ ዓለም ላይ የሚቀርበው ጥያቄና የሚሰጠው ምላሽ አንዱ አንገብጋቢ ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ርዕሰ ጉዳይ ኢሕአዴግና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተቀራርበው ለመሥራት እንዳይችሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አድርጓል፤ ይላል፡፡ ኣያይዞም ሌላኛው ጥያቄ በኢሕአዴግና በመንግሥት መካከል ያለውን ግልጽ ያልሆነ ግንኙነት ወይም መቀላቀል ይመለከታል፤ ይለናል፡፡ እናም ኢሕአዴግ የፓርቲውንና የመንግሥትን ሚና በመቀላቀልና ፓርቲው ያለአግባብ የመንግሥትን ሀብት እንዲጠቀም እንዳደረገው በተደጋጋሚ ቅሬታ እንዲቀርብበት በር ከፍቷል፡፡
እንደጋዜጣው ከሆነ፤ የምርጫ ጉዳይ አስተዳዳሪ ተቋማትና በዲሞክራሲ ግንባታ ሒደቱ ላይ ከፍተኛ ሚና የሚጫወቱ ተቋማት ላይ የሚነሳው የነፃነትና የገለልተኝነት ጥያቄ ሌላው ጉዳይ ነው፡፡ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድና የመንግሥት የሚድያ ተቋማት አሁንም የዛሬ 18 ዓመት ይባሉ እንደነበረው ኢሕአዴግን ብቻ በማገልገል፣ በሕግ ሁሉንም ተወዳዳሪ ፖለቲካ ፓርቲዎች በእኩልነት እንዲያገለግሉ የተጣለባቸውን ኃላፊነት እየተወጡ አይደለም ተብለው ይተቻሉ፡፡
ወደ ሲዳማ ስንመለሰ ፤በየትኛውም መስፈርት ደኢህዴን ኢህኣደግ በሲዳማ ዞን ውስጥ ጠንካራ ፓርቲ ነው፡፡ በአንፃሩ ሌሎች የብሄሩ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የደኢህዴንን ያህል የተጠናከረ መሰረት የላቸውም። እድሜ ጠገቡ ሲኣን እንኳን መኖሩ የምታወቀው ምርጫ ሲመጣ ብቻ ነው። ሌሎች የሲዳማ የፖለቲካ ፓርቲዎች ነን ብለው የብሄሩን ስም ለጥፈው የምንቀሳቀሱት የፖለቲካ ፓርቲዎች ከኣገር ውጭ እንጅ ሲዳማ ውስጥ መፈጠራቸውን እንኳን የምያውቅ ሰው የለም። ባይሆን እነርሱ የምታወቁት በሲዳማ ዳይስፖራ ዘንድ ይመስላል። የእነርሱ ፖለቲካ ከኢንተርኔት ላይ ያለፈ ኣይደለም። እንታገልለታለን የምሉትን ህዝብ ጠንቅቀው የምያቁት ኣይመሰልም። ብያውቁት ኖሮማ ወደ ህዝቡ ገብተው ይታገሉለት ነበር ይባላል።
አንዳንድ የፖለቲካ ተንታኞች እንደሚሉት፣ በሲዳማ የተቃዋሚ ፓርቲዎች አለመጠናከር በተወሰነ መልኩ ኢሕአዴግና ያልዳበረው የፖለቲካ ባህል አስተዋጽኦ ያላቸው ቢሆንም፣ ትልቁን ድርሻ የፓርቲዎቹ ቁርጠኛ አለመሆንና ጠንክሮ አለመሥራት ነው፡፡ ወጣም ወረደም የሲዳማ ህዝብ ይሆነኛል የምለውን ለመምረጥ ተመዝግቧል።
በመጪው ሚያዝያ በሚካሄደው የአከባቢና ከተማ አስተዳደር ምርጫ ላይ ለመሳተፍ በሲዳማ ዞን1ሚሊዮን በላይ መራጮች መመዝገባቸውን ኣቶ ብርሃኑ ዱካሞ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሰሞኑን ተናግረዋል ።ሀዋሳ ከተማን ጨምሮ በሲዳማ ዞንና በሌሎች ከተሞች ደኢህዴን ከ115 ሺህ በላይ እጩዎችን ማስመዝገቡን እኚሁ ግለሰብ የገለጹ ሲሆን፤ ደኢህዴን ያስመዘገባቸው 115 ሺህ 368 ዕጩዎች ለዞን ፣ለወረዳ ፣ለከተማና ለቀበሌ ምክር ቤቶች ድርጅቱን ወክለው የሚወዳደሩ ናቸው። ደኢህዴን ለሲዳማ ዞን ፣ለሀዋሳ ፣ለይርጋለምና ለአለታ ወንዶ ከተሞች አስተዳደሮችና ለ21 ወረዳዎች ካስመዘገባቸው ዕጩዎች ውስጥ 105 ለዞን ምክር ቤት፣ 277 ለከተማ አስተዳደር ምክር ቤት፣ 1524 ለወረዳና ፣113 ሺህ 462 ለቀበሌ ምክር ቤት የሚወዳደሩ መሆኑን ተናግረዋል።
ከላይ እንደምናየው ደኢህዴን ዕጩዎቹን ማስመዝጋቡን እንደልባቸው በተቆጣጠሩት ሚዲያ ስንሰማ የሲዳማ ተቃዋሚ ድርጅት የሆነው የሲኣን እንቅስቃሴስ ምን ይመስላል የምል ጥያቄ በኣእምሮኣችን ሳይነሳ ኣይቀርም። ኣዎን ሲኣንን በተመለከተ ያለው መረጃ እንደምያመለክተው ከሆነ እስካሁን ዕጩዎቹን ኣለስመዝገበም። ኣንዳንድ እየተሰሙ ያሉት ጭምጭታዎች እንደምያሳዩት ሲኣን በዘንድሮ ምርጫ ለመወዳደር ከሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች የተለየ ኣቋም ይዞ ወደ ምርጫ የገባ ቢሆንም የገዥው ፓርቲ ኣባላት ኣናሰራም እያሉት መሆኑን እና ምናልባትም ከምርጫ ውድድሩ ራሱን ሳያገል እንደማይቀር ጭምጭምታዎች ኣሉ።
እንግዲህ ከኣንድ ሚሊዮን በላይ የምሆን የሲዳማ ህዝብ ለመምረጥ ተመዝግቦ ድምጹን ለመስጠት ድምጽ መስጫ ቀኑን በመጠባበቅ ላይ ነው። ታዲህ የዚህን ህዝብ ድምጽ ለማግኘት የብሄሩ ፖለቲካ ፓርቲዎች ምን ይዘው ነው የቀረቡት? ይህንን ጥያቄ ከማንሳታችን በፊት ለመሆኑ የሲዳማ ህዝብ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎቹ ምንድናቸው ካልን፤ በዋናነት የምነሱት የመልካም ኣስተዳደር ጥያቄ እና የክልል ጥያቄን ማንሳት ይቻላል።
እንደ ኣንድ የሲዳማ ተወላጅ ማለት የሚቻለው በተለይ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሲዳማ ህዝብ የመልካም ኣስተዳደር ችግር ተቋዳሽ እንደሆነና ህዝቡ በተለያዩ ኣጋጣምዎችን በመጠቀም ያሉበትን የመልካም ኣስተዳደር ችግሮች መፍትሄ እንዲያገኙ ለምመለከው ኣካል ጥያቄ ሲያቀርብ ቆይቷል። ገዥው ፓርቲ ደኢህዴን ኢህኣዴግ ለህዝቡ ጥያቄዎች ጆሮ ዳባ ልበስ ከማለት ኣልፎ የህዝቡን ጥያቄዎች በሬ ወለደ ወሬ ማለትን መርጧል። በተለያዩ ኣጋጣሚዎች ለተነሱት የመልካም ኣስተዳደር ጥያቄው ምላሽ ያልሰጠው ገዥው ፓርቲ የህዝቡ ጥያቄ የልማት ጥያቄ ነው እንጂ ሌላ ጥያቄ የህዝቡ ጥያቄ ኣይደለም በማለት ከርሟል። ህዝቡ ጥያቄ ከልማት ጥያቄ ውጪ ኣይደለም የምል ከሆነ ለምን የልማት ጥያቄውን በኣግባቡ እንደማይመልስ ግልጽ ኣይደለም።
ደኢህዴን በሲዳማ ዞን ውስጥ ያሉት ጥያቄው የልማት ናቸው ብሎ የምል ከሆነ እነዚህ ጥያቄዎች ለመመለስ ምን እያደረገ ነው። በርግጥ በተለያዩ የመንግስት ፕሮግራሞች ታቅፈው በመካሄድ ላይ ያሉ የልማት ስራዎች ኣሉ። እነዚህም ቢሆኑ በኣብዛኛው በህዝብ ተሳትፎ ላይ ትኩረት ያደረጉ ናቸው። ይህም ደኢህዴን ምርጫ ለማሸነፍ የምከተላቸውን ኣካሄዶች ከመሆን ያለፈ ትርጉም የለውም።
ይቀጥላል

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር