በሃዋሳ ከተማ በመገንባት ላይ ያለው የህጻናትና የአረጋዊያን ማዕከል ግንባታ ከ70 በመቶ በላይ ተጠናቀቀ

ሃዋሳ ጥር 24/2005 በሃዋሳ ከተማ ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ በመንግስትና በህብረተሰብ ተሳትፎ እየተሰራ ያለው የህጻናትና የአረጋዊያን ማዕከል ግንባታ ከ70 በመቶ በላይ መጠናቀቁ ተገለጠ ። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከሜሪ ጆይ ልማት ማህበር ጋር በመሆን በተለያዩ ማህበረሰብ አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ተባብረው ለማስራት የሚያስችል የጋራ መግባቢያ ሰነድም መፈራረማቸው ተገልፀዋል፡፡፡፡ በክልሉ መንግስት፣ በህብረተሰብ ተሳትፎና በሌሎች የልማት አጋሮች ድጋፍ ከሁለት ዓመት በፊት የተጀመረው የህጻናትና የአረጋዉያን ማእከል ግንባታ ዉስጥ እስካሁን ከሰባ በመቶ በላይ ተጠናቋል ። የሃዋሳ ከተማ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያና የበጎ ፈቃደኞች ማህበር ሰብሳቢ አቶ ዘለቀ ከበደ በዚሁ ወቅት እንደተናገሩት ከሃዋሳ ከተማ አስተዳደር በነፃ በተሰጠው ከ6ሺህ 400 ካሬ ሜትር በላይ ያለዉ ማእከል 22 የተለያዩ አገልግሎት መስጫ ክፍሎች አሉት ። ማዕከሉ በዋናነት ቤተ መፃህፍት፣ የምክር አገልግሎት መስጫ /ካውንስልንግ/ የህክምና ክፍል፣ የመዝናኛ ፣ ዎርክሾፕና ሴራጅም እንዲሁም ሌሎች አገልግሎት መስጫዎች አካቶ የያዘ መሆኑን አስረድተዋል ማእከሉ ባለፉት ስድስት ዓመታት ከሜሪ ጆይ የልማት ማህበር ጋር በመተባበር በተለይም ሴት አረጋዊያንን በተለያዩ የገቢ ማስገኛ ስራዎች በማሳተፍ ከኢኮኖሚ ጥገኝነት እንዲላቀቁ ባከናወናቸዉ ስራዎች አበረታች ውጤት መመዝገቡ ተገልጧል ። የሜሪ ጆይ ልማት ማህበር መስራችና ስራ አስኪያጅ ሲስተር ዘብይደር ዘውዴ በበኩላቸው ማህበሩ በአዲስ አበባ እና በደቡብ ክልል 12 ከተሞች ለችግር የተጋለጡ ከ42ሺህ በላይ ህፃናትና 800 አረጋዉያን በቋሚነት የአልባሳት፣ የጤና፣የትምህርት፣የስነልቦና፣ የመጠለያ፣ የምግብና ሌሎች ድጋፍ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በሃዋሳ ከተማ በመገንባታ ላይ የሚገኘው የአረጋዊያንና ህፃናት ማዕከል ከሁለት ወር በኋላ ሙሉ ለሙሉ ተጠናቀው አገልግሎት እንደሚሰጥ የገለጹት ስስተር ዜብዳር ማዕከሉ አገልግሎት መስጠት ስጀምር በቀን ከ300 በላይ ለችግር የተጋለጡ ህፃናትና አረጋዊያን በማዕከሉ የሴራጅም፣ የቤተመፃህፍት፣ የምግብ፣የህክምና፣የካውንስልግ እና የሌሎች አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡ ልማት ማህበሩ የአረጋዊያንና የህፃናት ችግር ቀጣይነት ባለው መንገድ ለመፍታት በጥናትና ምርምር፣ በስልጠናና በአቅም ግንባታ ዙሪያ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል ሰነድ ተፈራርሟል ። አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ስነ ትምህርት ኮሌጅና የባህሪይ ጥናት ትምህርት ዲን ፕሮፈሰር ሎሬት ጥሩሰው ተፈራ ከፊርማው ስነስርዓት በኋላ ባስተላለፉት መልዕክት የህፃናት፣የወጣቶችና የአረጋዊያን ችግሮችን ደረጃ በደረጃ ለመፍታት የሚያስችሉ የምርምር ስራዎችን በማከናወን በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ የልማት ዘርፎች የበኩላቸውን ሚና እንዲጫወቱ ኮሌጁ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=5092&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር