አሮሬሳ ወረዳ የ119 ሺህ 874 ዶላር የገንዘብ ድጋፍ ከጃፓን መንግሥት ኣገኘ

አዲስ አበባ የካቲት 13/2005 ጃፓን በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚካሄዱ የማኅበረሰብ ልማት ሥራዎች የሚውል ከ581 ሺህ ዶላር በላይ ለአራት መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ለሲዳማ ዞን አስተዳደር ዛሬ ድጋፍ አደረገች። የልማት ሥራዎችን ለማከናወን ከጃፓን መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ የተደረገላቸው በትግራይ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በሐረር ክልል ለሚገኙ የልማት ማኀበራትና ድርጅቶች እንዲሁም ለሲዳማ ዞን አስተዳዳር ነው። በድጋፍ የተገኘው ገንዘብ በአራቱ ክልሎች በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ማኅበረሰቦች የትምህርት ቤቶች ማስፋፋያ፣ ንጹህ የመጠጥ ውኃ ግንባታና ለጤና አገልግሎት መስጫ ተቋማት ግንባታ የሚውል ነው። የጃፓን መንግሥት በድጋፍ ከሰጠው ገንዘብ ውስጥ 122 ሺህ 229 ዶላር በከንባታ ጠንባሮ ዞን ውስጥ ለሙዱላ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ግንባታ ሲውል 119 ሺህ 874 ዶላር ደግሞ በሲዲማ ዞን አሮሬሳ ወረዳ ለሚገኝ ትምህርት ቤት ግንባታና ቁሳቁስ ማሟያ እንደሚውል ተገልጿል። እንዲሁም 118 ሺህ 575 ዶላር በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል ለማንዱራ ወረዳ ለትምህርት ቤትና የአስተዳደር ቢሮ ግንባታ የሚውል ሲሆን 116 ሺህ 208 ዶላር ደግሞ በሐሪር ክልል ለድሬ ጢያራና ለሶፊ ወረዳ ለንጹህ የመጠጥ ውኃ ግንባታ ይውላል። 

ቀሪው 104 ሺህ 689 ዶላር ደግሞ በትግራይ ክልል ለእንደርታና ለክልት አውላዕሎ ወረዳ ንጹህ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ማከናወኛ የሚውል ሲሆን ፕሮጀክቶቹ ሲጠናቀቁ ከ5 ሺህ በላይ አባወራዎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ። በኢትዮጵያ የጃፓን ኤምባሲ ጉዳይ አስፈፃሚ ሚስተር ሃጂሜ ኪታኦካ በኤምባሲው በተካሄደው የፊርማ ሥነ-ሥርዓት ላይ እንደገለጹት የትምህርት ተቋማቱና የንጹህ የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ግንባታ ሲጠናቀቅ በአጠቃላይ ከ15 ሺህ በላይ የአካባቢውን ነዋሪችን ተጠቃሚ ያደርጋል። እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ1997 ጀምሮ በኢትዮጵያ ውስጥ ለተከናወኑ ከ300 በላይ የልማት ፕሮጀክቶች ጃፓን ድጋፍ ማድረጓንም ተናግረዋል።
http://www.ena.gov.et/story.aspx?ID=5709

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር