ከሲዳማ እና ቤንች ማጂ ዞኖች 106 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ተመርቶ ብሄራዊ ባንክ ቀረበ

ሃዋሳ የካቲት 12/2005በደቡብ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት በባህላዊ መንገድ የተመረተ 106 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ ለብሄራዊ ባንክ መቅረቡን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ ገለጸ ፡፡ በቢሮው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መላኩ እንዳለ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ወርቁ ተሰብስቦ ለባንኩ የቀረበው ከቤንች ማጂና ሲዳማ ዞኖች ነዉ ። በባህላዊ መንገድ የተመረተዉ ወርቅ በህጋዊነት ተደራጅተው በሚንቀሳቀሱ 18 የወርቅ አምራቾችና ግብይት ህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ለባንኩ መቅረቡን አስረድተዋል ። የዘንድሮዉ የግማሽ በጀት አመት ክንውን ከእቅዱ አኳያ ዝቅተኛ ቢሆንም ከ2001 ሙሉ በጀት አመት ከነበረው ጋር ሲነጻጸር ከሁለት ዕጥፍ በላይ ብልጫ እንዳለው ተናግረዋል ። በየዞኖቹ በባህላዊ መንገድ የሚመረተው ወርቅ በህገ ወጥ መንገድ እንዳይባክን የግብይት ጣቢያዎችን ከማጠናከር ባሻገር የግብይት ስርዓት ህጋዊ መልክ በማስያዝና አቅርቦቱን በቀጣይ ለማሻሻል ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ቢሮዉ ተቀናጅቶ እየሰራ መሆኑን አቶ መላኩ ጨምረው ገልጸዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=5642&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር