ከሻሸመኔ ጅምላ ንግድ አከፋፋይ ድርጅት /ጅንአድ/ መጋዘን ወጥቶ በህገ ወጥ መንገድ በሀዋሣ ከተማ ሲራገፍ የነበረ ዘይት በቁጥጥር ሥር መዋሉን የክልሉ ንግድ ኢንድስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡

ከሻሸመኔ ጅምላ ንግድ አከፋፋይ ድርጅት /ጅንአድ/ መጋዘን ወጥቶ በህገ ወጥ መንገድ በሀዋሣ ከተማ ሲራገፍ የነበረ ዘይት በቁጥጥር ሥር መዋሉን የክልሉ ንግድ ኢንድስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ አስታወቀ፡፡
በቢሮው የንግድ ኢንስፔክሽንና ሬጉሌሽን ዋና የሥራ ሂደት  ጊዜያዊ አስተባባሪ ወይዘሮ መስከረም ባህሩ እንደተናገሩት ባለሦስት ሊትር 91 ካርቶንና ባለ አምስት ሊትር 234 ካርቶን ዘይት በአይሱዙ መኪና ተጭኖ በአንድ ነጋዴ መጋዘን ሲራገፍ ከክልሉ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን በደረሰ ጥቆማ መሠረት በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል፡፡


በገንዘብ ሲተመን ከ138 ሺህ ብር በላይ የሚያወጣ ሲሆን   ወደ ኦሮሚያ ክልል ጎዴ ዞን የሚሄድ እንደነበር ነው የገለፁት፡፡
በተጠርጣሪው መጋዘን ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ ባለ 2ዐ ሊትር 336 ጀሪካን ዘይትም በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ተጠርጣሪ ግለሰብ በቁጥጥር ሥር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሆነም አስተባባሪዋ ተናግረዋል፡፡ ባልደረባችን አደገ አየለ እንደዘገበው፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/05TirTextN305.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር