በ2005 ዓ.ም ለሚካሄደው የአካባቢና የከተማ ምርጫ 23 ሚሊዮን የሚጠጉ መራጮች ተመዝግበዋል


አዲስ አበባ ጥር 14/2005 በመጪው ሚያዚያ ወር 2005 ዓ.ም ለሚካሄደው የአካባቢና የከተማ አስተዳደሮች ምርጫ የመራጮች ምዝገባ እንደቀጠለ ነው። በዘጠኙ ክልሎችና በሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች ከታህሳስ 22 እስከ ጥር 13 /2005 ዓ.ም ድረስ በተካሄደው የመራጮች ምዝገባ 23 ሚሊዮን የሚጠጉ መራጮች መመዝገባቸውን የምርጫ ቦርድ አስታወቋል፡፡ የቦርዱ የህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ምክትል ኃላፊ አቶ ይስማ ጅሩ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት ከተመዘገቡት መራጮች መካከል 10 ሚሊዮን 794 ሺህ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡ ቦርዱ በአጠቃላይ በሃገር አቀፍ ደረጃ ለመምረጥ ይመዘገባል ተብሎ ከሚጠበቀው ከ28 ሚሊዮን በላይ መራጭ መካከል 83 በመቶ የሚሆኑት የመራጭነት ካርድ መውሰዳቸውንም ጠቁመዋል፡፡ በተለያየ ምክንያት የመራጭነት ካርድ ያልወሰዱ መራጮችም በቀሪዎቹ 10 ቀናት የመራጭነት ካርዱን እንዲወስዱ ጥሪ አቅርበዋል።
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=4804&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር