ሃዋሳን ጨምሮ በክልሉ ከተሞች ከ130 የሚበልጡ የሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራትና 32 ዩኒየኖች ምርቱን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በማቅረብ ገበያን ማረጋጋት ስራውን በመቆጣጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦን ማበረከታቸውን አስታውቀዋል፡፡


በደቡብ ክልል ከ500 ሺህ ኩንታል የሚበልጥ ስኳርና ስንዴ ተሰራጨ
አዋሳ ጥር 22/2005 በደቡብ ክልል በተጠናቀቀው ግማሽ የጀት ዓመት ከ500 ሺህ ኩንታል የሚበልጥ ስኳርና ስንዴ በማሰራጨት ገበያውን በማረጋጋት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉን የክልሉ ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ ገለጸ፡፡ የቢሮ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ የኔወርቅ ቁምላቸው ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በክልሉ ያለውን ህብረተሰብ ከሚጎዱ የንግድ አሰራሮች በመከላከል ገበያን የማረጋጋቱ ስራ ውጤታማ ሆኗል፡፡ የክልሉ መንግስት መሰረታዊ የፍጆታ እቃዎች ስርጭት የሚመራበትን አሰራር ቀይሶ በሁሉም አከባቢ የስራ መዋቅሮችን በመዘርጋት ባለፉት ስድስት ወር ከ508ሺህ 054 ኩንታል በላይ ስኳርና ስንዴ በማሰራጨት ገበያን የማረጋጋት ስራ ማከናወኑን አስታውቀዋል፡፡ ስርጭቱ ፍትሃዊና ተደራሽ በሆነ መንገድ የተከሄደው በየአከባቢው የሚገኙ የጅንአድ ቅርንጫፍ ማዕከላት፣ ከ14 ዞኖችና ከ22 የከተማ አስተዳደር በተመረጡ የጅምላ ንግድ ፈቃድ ባላቸው ነጋዴዎችና በተደራጁ የህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ነው ብለዋል፡፡ በዘይት አቅርቦት በኩል የሚታየውን ችግር ለመቅረፍ በስምንት የጅንአድ ማዕከላትና በየከተሞች በተቋቋሙ ዩኒየኖች አማካኝነት ከ14 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለተጠቃሚዎች መከፋፈሉን ተናግረዋል፡፡ በተለይ ሃዋሳን ጨምሮ በክልሉ ከተሞች ከ130 የሚበልጡ የሸማቾች የህብረት ስራ ማህበራትና 32 ዩኒየኖች ምርቱን በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ በማቅረብ ገበያን ማረጋጋት ስራውን በመቆጣጠር ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦን ማበረከታቸውን አስታውቀዋል፡፡ የህብረተሰቡን ተጠቃሚነትና ገበያን ለማረጋጋት የሚሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንዲሆኑና ስርጭቱን ፍትሃዊ፣ ግልፅና ተደራሽ ለማድረግ ከክልል ጀምሮ በየደረጃው ኮሚቴ በማቋቋምና በየስርጭት ጣቢያዎች በመገኘት የክትትልና የቁጥጥር ስራዎች ማከናወናቸውን ተናግረዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=4999&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር