POWr Social Media Icons

Thursday, December 13, 2012


ሃዋሳ ታህሳስ 04/2005 በሀዋሳ ከተማ መንግስታዊ ያልሆኑ 74 ድርጅቶች ከ253 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ በጀት ህብረተሰቡን ያሳተፉ የልማት ፕሮግራሞች እያካሄዱ መሆናቸውን የከተማው ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ገለጸ፡፡ የመምሪያው ምክትል ሃላፊ አቶ አሻሬ ኡጋ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በከተማው ስምንት ክፍለ ከተሞች የሚካሄደው የልማት ፕሮግራም ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት የሚቆዩ ናቸው፡፡ ከልማት ፕሮግራሞቹ መካከል የጤና፣ የትምህርት፣ የከተማ ግብርና፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የህጻናት ድጋፍና ክብካቤ፣የገቢ ማስገኛ ፣አቅም ግንባታን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ዘርፎች መሆናቸውን አስታውቀዋል የከተማውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማፋጠን መንግስት የሚያደረገውን ጥረት ለማገዝ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ህብረተሰቡን በማሳተፍ የሚካሄዱት የልማት ፕሮግራሞች ሲጠናቀቁ ከ200ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡ የድርጅቶቹን የስራ አንቅስቃሴና አፈጻጸም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ክትትልና ቁጥጥር እያደረጉ መሆናቸውንም አመልከተዋል፡፡ እየተጠናቀቀ ባለው የአውሮፓውያኑ 2012 የስራ ዘመን ድርጅቶቹ በመደቡት ከ84 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የከተማው ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደረጉ ተመሳሳይ የልማት ፕሮግራሞች ማካሄዳቸውን የመምሪያው ምክትል ሃላፊ ገልጸዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=3941&K=1
 በኪንክኖ ኪአ
በሲዳማ ዞን በሚገኙ ሁሉም ወረዳዎች በሥራ አጥነት የሚሰቃዩ ወጣቶች ቁጥር ከጊዜ ቀደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ፡፡ ሥራ ያጡ ወጣቶችም በተለያዩ ወረዳዎች ሠላማዊ ሠልፍና ተቃዉሞ እያሰሙ መሆናቸዉ ታዉቀዋል፡፡ ሰሞኑን በአርቤጎና ወረዳ በተካሄደዉ ተቃዉሞ ሰልፍ ሳቢያም ከ15 በላይ ወጣቶች መተሰራቸዉ ተሰመቶአል፡

በአሁኑ ጊዜ በተለያዩ ሙያና ት/ት ዘርፎች ተከታትለዉ ከተመረቁ በኀላ የሥራ እድል በማጣት በርካታ ወጣቶች በከፍተኛ ችግር ላይ መዉደቃቸዉ በሰፊዉ ይነገራል፡፡ የከፍተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ት ካጠናቀቁ በኀላ በተለያዩ ኮሌጆች፡ የሙያ ማሠልጠኛ ተቐማትና ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸዉን የተከታተሉ ወጣቶች ቁጥር በርከት እያሌ መምጣቱ የሚነገር ሲሆን ከዚሁ ቁጥር ጋር የሚመጣጠን የሥራ እድል በመንግሥት ባለመመቻቸቱ ከፍተኛ የሆነ የሥራ አጥነት ችግር በዞኑ ተንሰራፍተዋል፡፡ 
 
ወጣቶቹ በት/ት የቀሰሙትን እዉቀት ተጠቅመዉ ሕብረተሰቡን ለማገልገልና የራሳቸዉን ሕይወት ለማሻሻል ከፍተኛ ተነሳሽነትና አቅምያላቸዉ ቢሆንም ት/ታቸዉን አጠናቀዉ ከ5 እና ከዚያ በላይ ዓመታትን የለሥራ በማሳለፋቸዉ ሰቢያ ሊለማ የሚችል እዉቀት፤አቅምና ጉልበት በጥቅም ላይ ሣይዉል እንደሚባክን ተጠቁመዋል፡፡
 
የሥራ አጥ ወጣቶች የኑሮ መሠረት በአጭሩ አብዛኞቹ የሥራ አጥ ወጣት ምሁራን የተገኙት ከገጠሩ ማህበረሰባችን ከፍል ነዉ፡፡ ትምህርታቸዉን ለመከታተልም ከፍተኛ የሆነ የኢኮኖሚ ወጪ አድርገዉ፤ አብዛኞቹ ደግሞ በግል ት/ት ተቐማት በራሳቸዉ አቅም ትምህርታቸዉን የተከታተሉ ናቸዉ፡፡ እንደሚታወቀዉ አብዛኛዉ የሲዳማ ማህበረሰብ የገጠር ነዋሪ በመሆኑ የኢኮኖሚ መሠረቱ ግብርና ከመሆኑም በተጨማሪ የገቢ ምንጫቸዉና አቅምቸዉ ይኼ ነዉ የሚባል አይደለም፡፡ ይህም ሆኖ እነዚህ የድሀዉ የህብረተሰብ ክፍሎች ነገ ብሩህ ቀን ይወጣል በማለት ያላቸዉን ሽጠዉ፤ ጨርሰዉ ልጆቻቸዉን በክፍያ አስተምሮአል፡፡ አብዛኞቹ ወላጅ የሌላቸዉ ወጣቶችም ያላቸዉን የመሬት ይዞታ ሽጠዉ፤ ሽንኩርትና ጎመን እየተሸከሙና እየሸጡ ትምህርታቸዉን ተከታትለዋል፡፡ በዚህ ሁሉ ችግር ዉስጥ እያለፉ በጽናትን በትጋት ትምህርታቸዉን እንደሚያጠናቅቁ ይታወቃል፡፡ያላቸዉን ሀብትን ንብረት ለልጆቻቸዉ ት/ት መሸፈኛ አድርገዉ በድህነት የተዋጡና ተስፋ የቆረጡ ቤተሰቦች ከልጆቻቸዉ በርካታ ነገሮችን መጠበቃቸዉ ደግሞ ሌላዉ አሳሳቢ ጉዳይ ይሆናል፡፡
 
የመንግሥትንና ሌላ የሥራ ዕድል ካጡ፤ የግል ሥራና ፈጠራ ባልዳበረበት ሀገር ሌላ አማራጭ ያለመኖሩ ጉዳይ እሙን ነዉ፡፡ ወደ ገጠር ተመልሰዉ መሬት ለማረስ ይገደዳሉ፡፡ ብዙዎቹ ደግሞ ይዞታቸዉን ሽጠዉ የት/ት ወጪ መሸፈኛ ስላደረጉ መሄጃም የላቸዉም፡፡ በዚህ ሁኔታ ለብዙ ዓመታት ለመኖር የገደዳሉ፡፡ 
 
በዘመናዊና ሰይንሳዊ ት/ት ራሳቸዉን ያለማመዱ ወጣት ምሁራን የህብረተሰቡን ችግር በተሻለ መንገድና አቅም ይፈታሉ ተብሎ የሚገመት ቢሆንም የሥራ ዕድል ባለመኖሩ ዕምቅክህሎታቸዉን ሳይጠቀሙ ለመኖር/ለመሞት እንደሚገደዱ ተነግሮአል፡፡
 
በወረዳዎች አከባቢ ያሉት የመንግስት አመራር አከላትም የለዉን የሥራ ዕድል አመቻችተዉ ወጣት ምሁራንን በልማታዊ ሥራዎች ላይ የማሳተፍ ፍላጎት እምብዛም አይታይባቸዉም፡፡ ከዚሁ በተቃራኒ ከከፍተኛ የት/ት ተቐማት የሚወጣጡ ምሁራንን እንደትልቅ ጠላት አድርጎ የማየት አዝማሚያን ያንጸባርቃሉ፡፡ ወጣቶቹን ልክ በነርሱ ወንበር ላይ ለመቀመጥ የሚማሩ የሚመስላቸዉ ካዲሬዎች በርካታ ናቸዉ፡፡ ይህ ሁኔታ በተስፋፋበት፤ ወጣቱ ተስፋ በቆረጠበት ሁኔታ እድገትና ትራንስፎርሜሽን የማይታሰብ ነገር ነዉ፡፡ አብዛኞቹ የየወረዳዎቹ ባለስልጣናት ከግል ተቐማት ’የገዙትን የድግሪና የድፕሎማ ወረቀት ይዘዉ እኛም ድግሪ አለን…የሚካበድ ነገር የለም ይላሉ፡፡

 
ሰሞኑን በሲዳማ ዞን ዉስጥበሚገኙ በአባዛኛዎቹ ወረዳዎች የሚገኙ በሥራ-አጥነተ ለብዙ ዓመታት የቆዩና የተጎሳቆሉ ወጣት ምሁራን ተቃዉሞአቸዉን በተለያዩ መንገዶች እየገለጹ የገኛሉ፡፡ በያዝነዉ ሳምንት በአርቤጎና ወረዳ የሚገኙ 650 የሚደርሱ የሥራ-አጥ ወጣት ምሁራን በወረዳዉ ዋና ከተማ ያዬ ሠላማዊ ሠልፍ በማካሔድ ተቃዉሞአቸዉን ገልጸዋል፡፡ ወጣቶቹ ካለፉት 6 ዓመት አንስቶ በስራ ፍለጋ ሲንከራተቱ የቆዩ ቢሆንም የሚሰማቸዉን አካል አላገኙም፡፡ ይልቁንም እንደትልቅ የሥርዓቱ ጠላቶች ተደርገዉ ተቆጠሩ፡፡ ይህ ሁኔታ ያሳሰባቸዉ ወጣቶች በአርቤጎና ያዬ ስታድዬም ተሰብስበዉ ስለመፍትሄዉ መወያየት ይጀምራሉ፡፡ አንድ ለሕዝብ የጎላ ጥቅም ያላመጣ የወረዳ ካቢኔ አባል እስከ5000 ብር (የአበል ሳይጨምር)ደመወዝ ሲቀበል፤ በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ ምሁራን ወጣቶች ያለትርጉም ኑሮ ይመርራቸዉና ወደ ወረዳዉ ም/ቤት ያመራሉ፡፡ ከዚያም በኡኡታና በሰልፍ ተቃዉሞአቸዉን ይገልጻሉ፡፡ የከተማዉ ነዋሪ ህዝብም ችግሮቻቸዉን የተመለከተ በመሆኑ የወጣቶቹን ተቃዉሞ ይደፋል፡፡ወጣቶቹ መደሪያቸዉን የወረዳ አስተዳደር ግቢ አድርገዋል፤ ይህን ደግሞ አስተያየት ሰጪዎቹ የአርቤጎናዉ የግብጽ ጣህርር አደባባይ ብለዉታል፡፡ 

 
የወረዳዉ ፖሊስ ተቃዉሞዉን ለመቀልበስ ያደረገዉ ሙከራ ሳይሳካ ሲቀር ተጨማሪ የፖሊስ ኀይል ለማግኘት ወደዞን በደወለዉ መሰረት የዞኑ የፖሊስ ኀይል ወጣቶቹን በቁጥጥር ሥር ለማዋል ይሞክራል፡፡ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሚሊዮን ማቴዎስ ወደሥፍራዉ በማቅናት ወጣቶቹን ባወያዩበት ወቅት እንዳሉት ለዚህ ሁሉ የሥራ-አጥ ወጣት ባንድ ጊዜ የስራ ዕደል መፍጠር ስለማይቻል መንግሥት ቀስ በቀስ የሥራ ዕድል እንደሚያመቻች ተናግሮአል፡፡ በዉይይቱ ላይ አንድ ግለሰብ በብዙ ሽህ የሚቆጠር ብር ከኪሱ ሲያስገባ አቅማቸዉን ጨርሰዉ የተማሩ ወጣቶች በድህነት ቀንበር ሥር ኑሮአቸዉን ይገፋሉ፡፡ ይህ ደግሞ ኢ-ፍትሐዊነት የሰፈነበት አገዛዝ መገለጫ መሆኑን ያመለክተናል፡፡
 
የዞኑ ፖሊስ በወሰደዉ የሓይል ርምጃ በርካታ ወጣቶች የተጎዱና የአካል ድብደባ የደረሰበቸዉ ሲሆን፤ 15 የሚሆኑት ደግሞ በወረዳዉ ፖሊስ ጣቢያ ታስረዉ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችለዋል፡፡ የታሳሪቆቹ ቤተሰቦችም በሁሉም የገጠር ቀበሌዎች በቁጣ የወረዳዉን አመራር በመጤቅ ላይ መሆናቸዉ ታዉቐል፡፡
 
በመቀጠልም የሥራ ዕድሉ በአስቾካይ ካልተመቻቸ…. በአንድ ግለሰብ የተያዙ ከ3 በላይ የሚሆኑ መደቦች ካልተስተካከሉ… ሁኔታዉ ወደሌላ አቅጣጫ ሊያመራ እንደሚችል አስገንዝበዋል፡፡ ይህ በእንድህ እንዳለ፤ በወ/ገነት፤ በአለታ ወንዶና በበንሳ ዳዬ ወረዳቆች የሚገኙ የሥራ-አጥ ምሁራን ወጣቶች ተመሳሳይ ቅሬታ እያሰሙ መሆናቸዉን ከሥፍራዉ የተገኙ መረጃዎች ጠቁመዋል፡፡
http://www.facebook.com/n/?groups%2F289317227830513%2Fpermalink%2F362083180553917%2F&mid=7336d0eG5af42165d210G12177eG96&bcode=1.1355378656.Abm9hfgh7iNQNhJr&n_m=nomonanoto%40gmail.com