POWr Social Media Icons

Tuesday, December 4, 2012

በወረዳው ጊዲቦ በተባለ ቀበሌ ነዋሪ ለሆኑ አባወራና እማወራ አርሶ አደሮች ለሁለተኛ ዙር የመሬት ልኬት ካርታና ሰርተፍኬት አሰጣጥ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ሳሙኤል ባሰሙት ንግግር አርሶ አደሩ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታና ሰርቲፍኬት ማግኘቱ በመሬቱ የባለቤትነት መብት ተሰምቶት ልማቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ያስችላል፡፡


የወረዳው ግብርና ገጠር ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በርናባስ ሮማ በበኩላቸው መንግስት የአርሶ አደሩን የመሬት ይዞታ ዋስትና ለማረጋገጥ መሬቱን አልምቶ የምርቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ሰፊ ስራ እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡
ከቀበሌው ነዋሪዎች መካከል  አርሶ አደር ብሩ ሙፋቶሃና ሴት አርሶ አደር አማረች ተስፋዬ በሰጡት አስተያየት የይዞታ ማረጋገጨ ካርታና ሰርቲፍኬት መስጠቱን በንብረታቸው ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻሉም ሌላ ሁሉንም ፆታዎች በእኩል ደረጃ የመሬት ባለቤት እንዲሆኑ በማድረጉ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡ የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን እንደዘገበው፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/23HidTextN205.html
ሃዋሳ ህዳር 25/2005 ህገ መንግስቱ የፈጠራቸው መልካም ሁኔታዎችን በመጠቀም የተጀመረውን የጸረ ድህነት ዘመቻ በማጠናከር የመለስን ራዕይ እውን ለማድረግ የክልሉ ህዝብ በጋራ ጠንክሮ መስራት እንዳለበት የደቡብ ክልል ምክር አፈ ጉባዔ አስገነዘቡ፡፡ ዘንድሮ ለሰባተኛ ጊዜ የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች ቀን በክልል ደረጃ ሲዳማ ዞን በይርጋዓለም ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት ትናንት በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል፡፡ አፈጉባዔ ወይዘሮ ገነት ወልዴ ፕሮግራሙን ሲከፍቱ እንደተናገሩት ህገ መንግስቱ የፈጠራቸውን ምቹና መልካም ሁኔታዎችን በመጠቀም ድህነትን ለማስወገድና የመልካም አስተዳደር ለማስፈን በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተቀየሱ የልማት ራዕዮችን እውን ለማድረግ ሁሉም በጋራ ጠንክሮ ሊሰራ ይገባል፡፡ ህዳር 29 ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በልዩነታቸው ውበትን፣ በውበታቸው አንድነትን የመሰረቱበት ብቻ ሳይሆን ባህል፣ ወግ፣ ልማዳቸውንና ቱውፊታቸውን ያደሱበት ልዩና ታሪካዊ ቀን ነው ብለዋል፡፡ የክልሉ ህዝብ በህገ መንግስቱ የተጎናጸፈውን ራስን በራስ የማሰተዳደር ነፃነት በመጠቀም ባለፉት 21 ዓመታት በርካታ የልማት፣ የመልካም አስተዳደርና የሰላም ድሎችን ሊያስመገብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ መሃንዲስነት የተዘረጉትን የልማት መስመሮችንና መልካም ፖሊሲዎችን በማስቀጠል ድህነትን ታሪክ አድርጎ ለማለፍ ዘርፈ ብዙ ጥረቶች መደረጋቸውን ጠቁመው በመስኩ አመርቂ ውጤት እየተመዘገበ ነው ብለዋል፡፡ ወይዘሮ ገነት በማያያዝም በክልሉ ብሎም በሀገሪቱ ዘላቂና ቀጣይነት ያለውን ልማት በማስመዝገብ ድህነትን ለማስወገድ ለተያዘው ዕቅድ መሳካት አመራሩ፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ ወጣቶችና ሌሎች የህብተሰብ ክፍሎች በየተሰማሩበት ጠንክሮ ሊሰሩ ይገባል ብለዋል፡፡ ክብረ በዓሉ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ለዘመናት ሲያነሱት የነበረውን የነፃነትና የዕኩልነት ጥያቄ ምላሽ ያገኘበት ዕለት በመሆኑ በዓሉ ለዘለዓለም ሲዘከር ይኖራል ብለዋል፡፡ የሲዳማ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ በበኩላቸው በክልሉ እየተካሄዱ ያሉትን የልማት ጅምሮችን በማፋጠን ዋነኛ ጠላት የሆነውን ድህነትን ድል ለመንሳት የሁሉም አካላት የተቀናጀ ጥረት ወሳኝ ነው ብለዋል፡፡ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በመፈቃቀርና በመቻቻል ላይ የመሰረቱትን አንድነታቸውን በማጠናከር ባለፉት ዓመታት በድሀነት ላይ በከፈቱት ዘመቻ በልማት፣በመልካም አስተዳደር፣ በሰላምና በዴሞክራሲ መስክ አኩሪ ድሎችን ማስመዝገብ መቻላቸውን ገልጸዋል፡፡ በበአሉ ላይ ከተገኙት መካከል መምህር ሙላቱ ስማቸውና መብራቴ በርሄ በሰጡት አስተያየት ህዳር 29 በሀገሪቱ የህግ የበላይነት የሰፈነበት፣ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች በሁሉም መስክ እኩልነታቸውና የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታቸው ተረጋግጦ ተቻችለውና ተፈቃቅረው መኖር የጀመሩበት ታላቅ ቀን ነው ብለዋል፡፡ ተማሪ ቤተልሄም አበበና ዘላለም አደም በበኩላቸው ህዳር 29 ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ከአስከፊው ስርዓት ተላቀው ባህላቸውን፣ ቋንቋቸውንና ማንነታቸውን በአደባባይ ለዓለም ህዝብ እንዲያሳዩ ያደረገ ልዩ ቀን ከመሆኑም ባሻገር ለእኛ ለወጣቶች የተለየ ቦታ ስላለው ለቀጣይ ትውልድ ለማስተላለፍ የሚጠበቅብንን ሁሉ እንወጣለን ሲሉ ገልጠዋል ፡፡ በዚሁ ክብረ በዓል የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የዞን አመራሮች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የአካባቢው ነዋሪዎችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት የተሳተፉ ሲሆን በተለያዩ የልማት ሲኬቶችና በህገ መንግስቱ ዙሪያ የተዘጋጁ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበዉ ዉይይት ተካሂዶባቸዋል ። 
 http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=3755&K=1