POWr Social Media Icons

Tuesday, November 13, 2012ሀዋሳ (ኢዜአ)፦ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቅበላ አቅሙን ለማሳደግ በይርጋዓለም ከተማ በ55 ሚሊዮን ብር ወጪ ያስገነባው አዲሱ የአዋሳ ካምፓስ ትናንት ተመርቆ አገልግሎት መስጠት ጀመረ፡፡ ካምፓሱን መርቀው የከፈቱት የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የዩኒቪርሲቲው አስተዳደር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ናቸው፡፡
የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሴፍ ማሞ በምረቃው ሥነ ሥርዓት ላይ እንደገለጹት፤ የዩኒቨርሲቲውን የቅበላ አቅም ለማሳደግ ከሚካሄዱ የማስፋፊያ ግንባታዎች አንዱ አካል የሆነው አዲሱ የአዋሳ ካምፓስ በ65 ሄክታር ቦታ ላይ ያረፈ ነው፡፡
በ2002 ዓ.ም ተጀምሮ በአሁኑ ወቅት የተጠናቀቀው ይኸው ካምፓስ ለ800 ተማሪዎች የመኝታ አገልግሎት የሚሰጥ ዘመናዊ ህንፃ ፣ የመማሪያና ሌሎችም ክፍሎችን የያዘ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
ካምፓሱ በአሁኑ ወቅት በአካውንቲንግ፣ በማኔጅመንት፣ በኢኮኖሚክስና፣ በኮፕሬቲቭስ ዘርፍ በመጀመሪያ ዲግሪ የተቀበላቸውን 580 ተማሪዎችን በመመዝገብ ለማስተማር መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በዚሁ አዲስ ካምፓስ በ38 ሚሊዮን ብር ወጪ የተጀመሩ የአስተዳደር ቢሮዎች፣ የተማሪዎች መመገቢያ፣ ቤተመጻሕፍትና የመምህራን መኖሪያ ግንባታ በቅርቡ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንደሚበቃ ዶክተር ዮሴፍ አመልክተው፤ የካምፓሱን የቅበላ አቅም በማገናዘብ ሌሎች የማስፋፊያ ግንባታዎች ለማካሄድ 320 ሚሊዮን ብር መመደቡን ጠቁመዋል፡፡
አዲሱን ካምፓስ እንዲከፈት ድጋፍ ላደረጉ ለክልሉ፣ ለሲዳማ ዞን፣ ለዳሌ ወረዳና ለይርጋዓለም ከተማ አስተዳደር፣ ለአካባቢው ማህበረሰብና ለሌሎችም ባለድርሻ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ 
የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እና የዩኒቨርሲቲው ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ካምፓሱን መርቀው ከከፈቱ በኋላ እንደተናገሩት በአገሪቱ ከ21 ዓመት በፊት የቅበላ አቅሙ 3 ሺ ተማሪዎች ብቻ የሆነ አንድ ዩኒቨርሲቲ እንደነበር አስታውሰው አሁን በመገንባት ላይ ያሉትን ሳይጨምር የቅበላ አቅማቸው 100 ሺ የሆነ 31 ዩኒቨርሲቲዎች አገልግሎት በመስጠት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡
ወደ አዲሱ ካምፓስ የገቡት ተማሪዎችም በትምህርታቸው በርትተው ውጤታማ እንዲሆኑ የመስተዳድሩና የአካባቢው ማህበረሰብ ድጋፍ እንደማይለያቸው አቶ ሺፈራው አረጋግጠውላ ቸዋል፡፡
የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች በበኩላቸው የካምፓሱ መከፈት ለልማት መሰረት የሆነውን የተማረ የሰው ሃይል ለማፍራት ምቹ ሁኔታ የሚፈጥር ከመሆኑ ባሻገር ለበርካታ ሰዎች የስራ ዕድል ለመፍጠርና ልማትን ለማፋጠን ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልፀዋል፡፡
ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ አዋዳን ጨምሮ በአምስት ካምፓሶች፣ በ8 ኮሌጆች እና በቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ36 የትምህርት ክፍሎች የተዋቀረ ሲሆን፤ በመደበኛና በተከታታይ የትምህርት መርሐ ግብሮች 25 ሺ 250 ተማሪዎችን በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና በዶክትሬት ዲግሪ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
የቅበላ አቅሙን ለማሳደግ በሚያካሂደው የማስፋፊያ ግንባታ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ዓመት መጨረሻ የተማሪዎች ቁጥር ወደ 30 ሺህ ለማድረስ እየሰራ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ጨምረው ገልጸዋል፡፡
በምረቃው ሥነ ሥርዓት የካምፓሱ አዲስ ተማሪዎች፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች፣ መምህራን፣ የመስተዳድር አመራሮች፣ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡ 
አቶ ባልጉዳ ጳውሎስ የአለታ ወንዶ ወረዳ አካል ጉዳተኞች ማህበር ሊቀመንበር እንዳሉት አካል ጉዳተኞች ካለባቸው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች ተላቀው የበኩላቸውን  አስተዋፅኦ ለማበርከት የልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ የባለ ድርሻ አካላት ድጋፍና ትብብር ወሳኝ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

አቶ ተፈራ ጨመሳ የክልሉ አካል ጉዳተኞች ማህበር አማካሪ በበኩላቸው አካል ጉዳተኛችን ለማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ ልማት ከማብቃት በተጨማሪ የአካል ጉዳተኛ ህፃናትን የትምህርት ተሳትፎ በማሳደግ የወደፊቱን የትውልድ ተስፋ እንዲያብብ ማድረግ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ለአስሩ አካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ለእያንዳንዱ ተማሪ በወር 15ዐ ብር ለአስር ወራት ድጋፍ በማድረግ ለሁሉም ተማሪዎች 15 ሺህ ብር ተመድቦላቸው በመማር ላይ እንደሚገኝ ገልፀዋል፡፡ የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን እንደዘገበው፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/02HidTextN405.html
የወረዳው ምክር ቤት 3ኛ ዙር 9ኛ መደበኛ ጉባኤ ሲካሄድ ዋና አስተደደሪው አቶ አማረ ሻላሞ እንዳሉት  የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት ሁሉም የልማት እቅዶች በጠንካራና በተደራጀ የልማት ሰራዊት መመራት አለባቸው ብለዋል፡፡

በወረዳው በሚከናወነው የበልግና የመኸር እርሻ 7 ሺህ 831 ሄክታር መሬት በዋና ዋና ሰብሎች በመሸፈን 16 ሺህ 584 ኩንታል ምርት ለመሰብሰብ መታቀዱን ገልፀዋል፡፡
ለዚህም15 ሺህ 13ዐ ኩንታል ዳኘና ዩሪያ ማዳበሪያ እንዲሁም አሲዳማ አፈርን በማከም ለእርሻ ሥራ ለማዋል 2ዐዐ ኩንታል ኖራና የተለያዩ ሰብሎች 3 ሺህ 289 ኩንታል ምርጥ ዘር በግብዓትነት እንደሚሠራጭም አቶ አማረ አስረድተዋል፡፡
ጉባኤው ከ39 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት በማፅደቅ መጠናቀቁንም የሲዳማ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን መምሪያ ዘግቧል፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/02HidTextN505.html