POWr Social Media Icons

Saturday, November 10, 2012-    በአንደኛው ቅጣት 10 ዓመት በሌላኛው ደግሞ ዕድሜ ልክ እስራት ወስኗል

በታምሩ ጽጌ

በደቡብ ክልል የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በአንድ ወጣት ላይ በተፈጸመ የግድያ ወንጀል በቀረቡለት የተለያዩ ክሶች ላይ የተለያዩ የቅጣት ውሳኔዎችን መስጠቱ እያነጋገረ ነው፡፡

ድርጊቱ የተፈጸመው አማረ ሙሉጌታ በተባለ የ23 ዓመት ወጣት ላይ በሐዋሳ ከተማ ሚያዝያ 5 ቀን 2003 ዓ.ም. ምሽት ላይ መሆኑን፣ ሁለቱም የክልሉ የከፍተኛ መርማሪ ከሳሾች ክሶች ያስረዳሉ፡፡

የከተማው ከፍተኛ መርማሪ ከሳሽ መጀመርያ ለሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ግንቦት 29 ቀን 2003 ዓ.ም. ክሱን ያቀረበ ሲሆን፣ ለክሱ መነሻ የሆነው ፍሬ ጉዳይ አማረ ሙሉጌታ በተባለ የ23 ዓመት ወጣት ላይ በሁለት ጓደኞቹ የተፈጸመን የግፍ አገዳደል ወንጀል የሚያስረዳ ነው፡፡

ከሳሽ በክሱ ላይ እንዳብራራው፣ ሟች አማረ ሚያዝያ 5 ቀን 2003 ዓ.ም. እስከ ሌሊቱ አጋማሽ ድረስ አፈወርቅ ሌሊሳና ውብሸት ደሞል ከሚባሉ ጓደኞቹ ጋር በተለያዩ ሬስቶራንቶችና ሆቴሎች ሲዝናኑ ያመሻሉ፡፡ ጓደኞቹ አስቀድመው በነበራቸው የመግደል ሐሳብ፣ ወጣቱን በተለያዩ መጠጥ ቤቶች በማዞርና በማጠጣት በስካር ራሱን እንዲስት ካደረጉት በኋላ፣ ወደ ሰዋራ ሥፍራ በመውሰድ ውብሸት የተባለው ጓደኛው ሲይዘው፣ ጌታሁን የተባለው ሌላኛው ጓደኛው በስለት የግራ ደረቱን እንደወጋው ክሱ ያብራራል፡፡


ጓደኞቹ ድርጊቱን ሌላ ሰው የፈጸመው ለማስመሰል ለመሞት በማጣጣር ላይ የነበረውን አማረ ሙሉጌታን በመሸከም አሴር ወደሚባል ሆስፒታል ቢወስዱትም፣ ሕክምና ሳይደረግለት ሕይወቱ ማለፉን የቅጣት ውሳኔው ሰነድ ያስረዳል፡፡

ጓደኞቹ በጥርጣሬ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ ፍርድ ቤት ቀርበው በሰጡት ቃል፣ ጓደኛቸው መሆኑንና ለሦስት ዓመታት እንደሚተዋወቁ፣ ድርጊቱ ተፈጸመ በተባለበት ዕለትም እስከ ምሽቱ ሰባት ሰዓት አካባቢ አብረው መቆየታቸውን ካስረዱ በኋላ፣ አብረው እንዲሄዱ ሲለምኑት ባለመስማማቱ ተለይቷቸው ከሄደ ከደቂቃዎች በኋላ እሱ ወደታጠፈበት ቦታ ሲሄዱ ወድቆ እንዳገኙትና ወደ ሆስፒታል እንዳደረሱት በመግለጽ፣ ቃላቸውን መስጠታቸውን ውሳኔው ይገልጻል፡፡

ከሳሽ የከተማው ዋና መርማሪ አምስት አስረጅ ምስክሮችን ለፍርድ ቤቱ አቅርቦ ያሰማ ሲሆን፣ አንደኛ ምስክር ከሌሊቱ ሰባት ሰዓት ሟችና ተጠርጣሪዎች እየተጨቃጨቁ ሲሄዱ ማየቱንና አብረውት እንዲሄዱ ሲለምኑት እንደነበር፣ እንደማይሄድ ሲነግራቸው ስልኩን እንዲሰጣቸው ሲጠይቁት እንዳልሰጣቸውና ወደ ስታዲየም ትቷቸው መሄዱን ገልጾ፣ ከጥቂት ደቂቃ በኋላ ተሸክመውት ወደ ሆስፒታል ሲወስዱት ማየቱንና ‹‹ወግተውት›› ሸሹ እንዳሉት ሲመሰክር፣ ቀሪዎቹም የሆስፒታሉ የጥበቃ ሠራተኛና ሌሎችም ምስክሮች ያዩትን መመስከራቸውን ውሳኔው ይገልጻል፡፡

ፍርድ ቤቱ የምስክሮቹን ቃል ከተቀበለ በኋላ ምስክሮቹ የሰው ግድያ ወንጀልን በሚያሟላ መልኩ አለማስረዳታቸውን ገልጾ፣ ተከሳሾቹ የተከሰሱበትን አንቀጽ በመቀየር በወንጀል ሕጉ 540 መሠረት እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡

ተከሳሾቹ የተከሳሽነት ቃላቸውን ከሰጡ በኋላ መከላከያ ምስክሮቻቸውን ማሰማታቸውን የሚገልጸው ውሳኔው፣ ፍርድ ቤቱ የግራ ቀኙን ክርክር ለመመርመር ተከሳሾቹ ተከላከሉ በተባሉበት የሕግ አንቀጽ ሥር ተከላክለዋል? ወይስ አልተከላከሉም? ጥፋተኛ ናቸው ወይስ አይደሉም? የሚለውን ጭብጥ ይዞ መመርመሩን ውሳኔው ያብራራል፡፡

ሟች በግራ በኩል የላይኛው ደረቱ ላይ ተወግቶ መሞቱን የሐዋሳ ሪፈራል ሆስፒታል ማረጋገጡንና በተከሳሾቹ አንደበት መረጋገጡን፣ በፖሊስ አማካይነት ፍርድ ቤት ቀርበው በወንጀል ሕጉ 35 መሠረት ከሰጡት ቃልና ከሳሽ ካቀረበው እንዲሁም ከተከሳሾች የተከሳሽነት ቃል ፍርድ ቤቱ ግምት መወሰዱን በመተንተን፣ ሟችና ተጠርጣሪዎች አብረው ማምሸታቸውንና አብረን ካላደርን በሚል ተጨቃጭቀው፣ ‹‹እሄዳለሁ አትሄድም›› ሲባባሉ በተደረገው ትግል የአንደኛው አንገት ተቧጭሮ መቁሰሉንና የአንደኛ ተከሳሽ እጅ በሟች መነከሱን፣ ሟች ይዞት በነበረ 10 ሺሕ ብር ቼክም አለመግባባት ተፈጥሮ እንደነበር ፍርድ ቤቱ ማረጋገጥ መቻሉን በውሳኔው አስፍሯል፡፡

ተከሳሾቹ ወድቆ አግኝተው ወደ ሆስፒታል መውሰዳቸውን ገልጸው እንዳልገደሉት ቢናገሩም፣ ከመለያየታቸው በፊት ተፈጥሮ በነበረው አለመግባባትና በአምስት ደቂቃ ውስጥ ሟች በሌላ ሰው ተወግቶ ወድቆ እንዳገኙት መናገራቸውን ፍርድ ቤቱን ሊያሳምነው ባለመቻሉ፣ ሟች ደውሎ እንዳይናገር ስልኩን እንዲሰጣቸው መጠየቃቸው፣ ሊወስዱት ይታገሉት የነበረው ወደ አንደኛው ጓደኛ ቤት መሆኑን ቢናገሩም፣ ወዴት ሊወስዱት እንደነበር በግልጽ እንደማይታወቅ በመግለጽ የግድያ ወንጀል ድርጊቱ ኃላፊነት የእነሱ መሆኑ ውሳኔው ያብራራል፡፡

ሟች ከደከመ በኋላ ወደ ሆስፒታል መውሰዳቸው ወንጀሉን ሌላ ሰው እንደፈጸመ ለማስመሰልና ራሳቸውን ከተጠያቂነት ለማዳን መሆኑን ፍርድ ቤቱ ግንዛቤ በመውሰዱ፣ በወንጀል ሕግ 540 መሠረት በሙሉ ድምፅ ጥፋተኛ በማለት እያንዳንዳቸው በ10 ዓመት ፅኑ እሥራት እንዲቀጡ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል፡፡

ተከሳሾቹ ይግባኝ ቢጠይቁም የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የሥር ፍርድ ቤትን ቅጣት አፅንቷል፡፡ ለሰበር አቤቱታ ቢያቀርቡም የሕግ ስህተት እንደሌለው በማስረዳት መዝገቡን መልሶት ነበር፡፡

ከላይ የተጠቀሰውን የክስ ሒደት መርምሮ የመጀመሪያውን የቅጣት ውሳኔ የሰጠው ፍርድ ቤትና የክልሉ ዓቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤት ግን፣ የሟች አማረ ገዳዮች ሌሎች ናቸው ተብሎ ክስ ሲመጣላቸው ተቀብለው አስተናግደዋል፡፡

የሟች አማረ ገዳዮች ተብለው እያንዳንዳቸው አሥር ዓመታት ተፈርዶባቸው ማረሚያ ቤት የገቡት ፍርደኞች፣ በእስር ላይ እያሉ፣ የከተማው ከፍተኛ መርማሪ ገዳዮች አብነት (ቀዬ) እና ተስፋ ፅዮን አበራ መሆናቸውን በመግለጽ አዲስ ክስ መመሥረቱን፣ መስከረም 14 ቀን 2005 ዓ.ም. ሌላ የቅጣት ውሳኔ መተላለፉን የሐዋሳ ከተማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለሁለተኛ ጊዜ የሰጠው ውሳኔ ያስረዳል፡፡

በሁለተኛው ክስ ወንጀለኛ ሆነው የቀረቡት አብነት (ቀዬ) እና ተስፋ ፅዮን በሌላ የወንጀል ድርጊት በማረሚያ ቤት እንደነበሩ የሚገልጸው ውሳኔው፣ አዲሶቹ ተከሳሾች ሟች አማረ ሙሉጌታን የገደሉት እነሱ መሆናቸውን፣ ነገር ግን በስህተት አፈወርቅና ውብሸት የሚባሉ ምስኪኖች መታሰራታቸውን ሲያወሩ ‹‹ሰማን›› ባሉ ታራሚዎች አማካይነት መከሰሳቸውን ውሳኔው ያብራራል፡፡

አዲሶቹ ተከሳሾች ድርጊቱን እንዳልፈጸሙ ክደው መከራከራቸውን፣ ነገር ግን ከሳሽ ባቀረበባቸው የማስረጃ ምስክሮች እንዳስመሰከረ ውሳኔው ይገልጻል፡፡ ፍርድ ቤቱም እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቶ ተከላክለዋል፡፡

አብነት (ቀዬ) የሚባለው ተከሳሽ መከላከያ ምስክር እንደሌለው ገልጾ ራሱ በሰጠው ቃል፣ ድርጊቱ በተፈጸመበት ወቅት ሐዋሳ እንዳልነበር፣ ሟችንም ሆነ የተፈረደባቸውን እንደማያውቃቸው፣ ወደ ሐዋሳ የመጣው ለሥራ ተቀይሮ መሆኑንና ከሥራ ቦታ ተይዞ መቅረቡን ማስረዳቱን ውሳኔው ይገልጻል፡፡ ተስፋ ፅዮን የሚባለው ተከሳሽ በሌላ ወንጀል ተፈርዶበት በማረሚያ ቤት እያለ ወንዶ ኬሮ የተባለ ታራሚ ‹‹እፈልግሀለሁ›› ካለውና ካገኘው በኋላ ሁለት ልጆች አሥር ዓመት እንደተፈረደባቸውና ባልሠሩት ወንጀል መሆኑን እንዳስረዳው ገልጿል፡፡ በመቀጠልም ወንዶ ኬሮ የሚባለው ታራሚ፣ አብነት (ቀዬ) በሠራው ወንጀል በመታሰራቸው እሱ መግደሉን ትመሰክርና 15 ሺሕ ብር ይሰጥሃል እንዳለው፣ ከተፈቱ እንደሚጨምሩለት ሲነግረው፣ እንዳልተስማማ ለፍርድ ቤቱ ማስረዳቱን ውሳኔው ይገልጻል፡፡ ሌሎቹም በመከላከያነት የቆጠራቸው ታራሚዎች ወንዶ ኬሮ የተባለው ታራሚ ሲገፋፋውና ገንዘቡ እንደሚከፈለው መስማታቸውን ማስመስከሩን ውሳኔው ገልጿል፡፡

ፍርድ ቤቱ ሁለቱም ፍርደኞች የከሳሽን ማስረጃ አለማስተባበላቸውን ገልጾ ጥፋተኛ በማለት፣ የግራ ቀኙን የቅጣት ማክበጃና ማቅለያ ካደመጠና ከሕጉ ጋር ካገናዘበና ከመረመረ በኋላ፣ ሁለቱም ተከሳሾች በዕድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ ማስተላለፉን ሰነዱ ይገልጻል፡፡

ፍርድ ቤቱ በአንድ የወንጀል ድርጊት በሁለቱ ላይ የአሥር ዓመት ፅኑ እስራት ፈርዶ ሰበር ደርሶ ከፀደቀ በኋላ፣ በሁለቱ ላይ ደግሞ ከወር በፊት በዕድሜ ልክ ፅኑ የእስራት ቅጣት ውሳኔ በማስተላለፉ ‹‹ለምን ቀድሞ ምርመራውን አላጣራም? ዓቃቤ ሕግስ በተዘጋ ፋይል ላይ እንዴት ሌላ ክስ ሊመሠርት ቻለ?›› በሚል ውሳኔው እያነጋገረ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

 http://www.ethiopianreporter.com/news/293-news/8463-2012-11-10-12-55-03.html

Addis Ababa, Ethiopia – Week 4 of the Ethiopia Premier League will continue here with current leaders Dedebit FC taking on Ethiopian Insurance; EEPCO hosting Adama and defending champions St. George entertaining newly promoted side, Ethiopian Water Works FC.
Mugher Cement will face Harar Beer at home and Sidama Coffee and Arba Minch will clash in the southern state derby in Yirgalem.
The league will continue on Monday with two matches featuring Ethiopian Coffee vs Hawassa and CBE vs Defence Force.
After 3 matches, Dedebit and Harar Beer seat on top of the league with 7 points each, followed by EEPCO, Ethiopian Coffee and St. George FC.
Week 4
Sunday, November 11
Dedebit v Insurance
EEPCO v Adama
Mugher v Harar Brewery
Sidama Coffee v Arba Minch
Water Works Sport v St George
Monday, November 12:
CBE v Defence Force
Ethiopian Coffee v Awassa

አዲስ አበባ ህዳር 1/2005 ኢትዮጵያ ከቡና በዚህ ዓመት ለማግኘት ያሰበችውን ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ ለማሳካት በዘርፉ የተሰማሩ አካላት የተቀናጀ ጥረት እንደሚያደርጉ የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የቡና ጉባዔ ተሳታፊዎች አረጋገጡ። በአዲስ አበባ ከተማ ላለፉት ሁለት ቀናት የተካሄደው ጉባዔ ተካፋዮች በማጠናቀቂያቸው ላይ እንደገለጹት የአገሪቱ ቡና በዓለም ገበያ ባለው ተቀባይነትና በተለይም ስፔሻሊቲ ቡና ባለው ተፈላጊነት ምርቱን በጥራትና በብዛት በማቅረብ በዕቅዱ የተያዘውን ገቢ ለማሟላት የጋራ ጥረት ያደርጋሉ። አገሪቱ ለዓለም ያበረከተችውን ቡና አልምታ ልትጠቀምባቸው የምትችላቸው ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ተሳታፊዎቹ አመልክተው፣የቡናውን ልዩ ባህርያት በመመርኮዝ ልማቱንና ግብይቱን በማሳደግ የተሻለ ገቢ ለማግኘት እንደሚቻል አስረድተዋል። ለዚህም ባለድርሻ አካላት ተገቢ ሚናቸውን እንዲወጡ በተቀናጀ መንገድ መንቀሳቀስ እንደሚገባቸውም አሳስበዋል። ጉባዔው በቡና ምርትና ግብይት ሂደት የተሰማሩ አካላትን በማሳበሰብ የኢትዮጵያን ቡና ሁኔታ የሚያሳውቅበት መልካም አጋጣሚ መፍጠሩን የኢትዮጵያ ኮፊ ኤክስፖርተርስ አሶሴሽን የቦርድ አባል አቶ ታደሰ መስቀላ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት አስረድተዋል። ጉባዔው በቡናው ዘርፍ ያሉትን ችግሮችና መልካም አጋጣሚዎች በስፋት በመዳሰስ በቀጣይ መከናወን ያለባቸውን ተግባራት ለመለየት የሚያስችሉ ጥናታዊ ጽሁፎች እንደቀረቡበት አስታውቀዋል። ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ጉባዔው በየዓመቱ ኤግዚቢሽንና የመስክ ጉብኝትን በማካተት እስከ አራት ቀናት ቆይታ እንዲኖረው ለማድረግ ከስምምነት ላይ መደረሱን አቶ ታደሰ ተናግረዋል። ተሳታፊዎቹ ኢትዮጵያ ጥራቱ የተጠበቀ ቡና ተከታታይነት ባለው መንገድ ማቅረብ በምትችልበት፣የኢትዮጵያን ቡና በዓለም አቀፍ ገበያ ያለዉ ሁኔታና የዘርፉን ስጋት መቀነስ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ በቡድኖች ተከፋፍለው ተወያይተዋል። ጥናት አቅራቢዎች ባቀረቧቸው ጽሁፎች እንዳመለከቱት ኢትዮጵያ ከቡና መገኛነቷ ባሻገር፤ልዩ ባህርያት ያለው ቡና ለገበያ በማቅረብ እያሳየች ያለቸውን መልካም ጅምር አጠናክራ መቀጠል እንዳለባት ያሳስባሉ። በተለይም ስፔሻሊቲ ቡናን በማቅረብ ገቢዋን የምታሳድግበት ሰፊ ዕድልም እንዳላት ከአሜሪካ ስፔሻሊቲ ቡና ማህበር ሚስተር ፒተር ጁሊያኖ ይናገራሉ።በደቡብ ክልል የይርጋ ጨፌና የሲዳማ ስፔሻሊቲ ቡናዎች ከፍተኛ ጥራት ያላቸው መሆናቸውንም መስክረዋል።የገላና ዓባያ ቡናም ተፈጥሮአዊነቱን ጠብቆ እንደሚገኝ አስታውቀዋል። አዲስ አበባ ላይ ቀመሳው የተደረገው ቡና በጉዞና ተያያዥ ችግሮች ኒው ዮርክ(አሜሪካ) ላይ ተፈልቶ ሲቀመስ ጣዕሙን የመቀነስ ችግር እንደሚታይበትም አስረድተዋል።ሆኖም ተፈጥሮአዊነቱንና ጥራቱን ጠብቆ በማምረት ገበያውን በይበልጥ ሰብሮ በመግባት ተወዳዳሪ መሆን እንደሚቻል ሚስተር ጁሊያኖ አስረድተዋል። የሞንዴሌዝ ኢንተርናሽናል የዘላቂነትና የሀብት ሥራ አስኪያጅ ሚስተር አሽሊን ራሞልቻን በበኩላቸው ኩባንያቸው በሚያመርታቸው የቸኮሌት፣የብስኩትና ከዱቄት የሚሰሩ ለስላሳ መጠጦች ውስጥ ቡናን በግብዓትነት እንደሚቀጠም አመልክተው፣በዓለም በሁለተኛ ደረጃ በሚይዘው የቡና ግብይታቸው የኢትዮጵያ ቡና ያለውን ሚና ቀላል እንዳልሆነ ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ቡናን ባሉት ልዩ ባህርያት ምክንያት በኩባንያው ከፍተኛ ተፈላጊነት እንዳለው አመልክተው፣ቡናውን በብዛት ለመግዛት ጥራቱን ጠብቆ በዘላቂነት ማቅረብ ወሳኝ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አንተነህ አሰፋ በበኩላቸው ምርት ገበያው በ17 ከተሞች የሚያካሂደውን የቡና ግብይት ወደ ሌሎች ከተሞችም በማስፋፋት በእድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዱ ከምርቱ ለማግኘት የሚደረገውን ዕቅድ ለማሳካት ጥረት እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። ምርት ገበያው ጥራትና ብዛት ያለው ቡና ለገበያ ለማቅረብ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ በአዳዲስ አሰራሮች ጭምር ለማገዝ ዝግጁ መሆኑንና በዚህም ስፔሻሊቲ ቡናን በቀጥታ ለመግዛት የሚያስችል ግብይት እንደሚጀምር ለተሳታፊዎቹ ባደረጉት ገለጻ አስረድተዋል። ''የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በኢትዮጵያ ቡና ላይ ተጨማሪ እሴት ለማከልና ጠንካራ ተወዳዳሪ እንዲሆን ይሰራል'' ሲሉም አቶ አንተነህ ተናግረዋል። የካሪቡ ኮፊ የቡናና ሻይ ሥራ አስኪያጅ ሚስተር ቻድ ትሬዊክ አገሪቱ የጫካ ቡናዋን ለዓለም አቀፍ ገበያ በማቅረብ ተጠቃሚነቷን በይበልጥ የምታሳድግበት ዕድል እንዳለ አመልክተዋል።የኢትዮጵያን የጫካ ቡና እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር ከ2004-06 ባሉት ዓመታት መጎብኘታቸውን አስታውሰው፣ምርቱን ሕጋዊ የምስክር ወረቀት እንዲያገኝ በማድረግና ለገበያ በማቅረብ ተጠቃሚነትን ማሳደግ እንደሚቻል ያስረዳሉ። የስታር ባክስ ተወካይ ሚስተር አርተር ካሩሌትዋ በበኩላቸው ኩባንያቸው ለኢትዮጵያ ቡና ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውና ጥራቱን በጠበቀ መልኩ የሚቀርበውን ቡና ለመግዛት ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተዋል። ለሁለት ቀናት የተካሄደውን ጉባዔ ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ኮፊ ኤክስፖርተር አሶሴሽን፣የአሜሪካ ዓለም አቀፍ የልማት ድርጅት(ዩ ኤስ ኤይድ)ና የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሆናቸውን የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘግቧል።


የኦባማ ማሸነፍና የኢህአዴግ 1ለ5 ስትራቴጂ ሚስታቸውን የሚወዱ መሪዎች እንፈልጋለን!በምርጫ 99 በመቶ ማሸነፍ ከመሸነፍ እኩል ነው!ከሁሉም በፊት መወያየት ያለብን የኢቴቪ ደባል ሆኖ ስለገባው የቻይና ኮሙኒስት መንግስት የቴሊቪዥን ጣቢያ /ሲሲቲቪ/ ነው፡፡ እንዴ --- እኔ እኮ እንዲህ አልመሰለኝም ነበር፡፡ ባለፈው ሰሞን  የቻይና ቴሊቪዥን ሃላፊዎች ከኢቴቪ ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት መፈራረማቸውን ስሰማ ትከሻዬን የከበደኝ ለካ ለዚህ ነው፡፡ በቃ ደስ አላለኝም ነበር፡፡ እናንተ ነገሩ ቀልድ እንዳይመስላችሁ - ቻይና በአጭር ጊዜ ውስጥ አፍሪካን በሙሉ ኮሙኒስት ካላደረገች ታዘቡኝ፡፡ አረ አያያዟ አያምርም! ኢህአዴግማ ደስታው ነው - በሰበቡ የኮሙኒስትነት አራራውን ይወጣብናል! /እንኳን ዘንቦብሽ --/  እኔ ግን ተናግሬአለሁ---አንድ ቀን አማን ነው ብለን ከእንቅልፋችን ስንነሳ እቺ ምስኪን አገር ኮሙኒስት ሆና እንዳትጠብቀን፡፡

የኢህአዴግን ባህል የማያውቁ የዋህ ዜጎች “እንዴ እኛ ሳንፈቅድ?” ሊሉ እንደሚችሉ እገምታለሁ /ሰውየው “ሚስትህ አረገዘች ወይ?” ቢሉት “ማንን ወንድ ብላ” አለ!/ የቀድሞው የአገሪቱ ፕሬዚዳንት የአሁኑ የተቃዋሚ ፓርቲ ሊ/መንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ያሉትን አልሰማችሁም? “ኢህአዴግ አስር ዓመት ሙሉ ሶሻሊስት ነኝ ሲል ቆይቶ ድንገት ተነስቶ “ነጭ ካፒታሊዝም” ተከታይ ነኝ አለኝ” ብለው ክህደት እንደተፈፀመባቸው ተናግረዋል እኮ፡፡ ስለዚህ እንደሳቸው “ሰርፕራይዝድ” እንዳትሆኑ! ወዳጆቼ--- የስነልቦና ዝግጅት ማድረግ እኮ ቀላል በረከት አይደለም፡፡ እንደው ሌላው ቢቀር ድንገት ፌንት ከማድረግ ይታደጋል፡፡ እኔ የምለው--- ባለፈው ሳምንት ሲሲቲቪ በኢቴቪ ያሰራጨውን ዜና ሰማችሁልኝ? አንደኛው የቻይና ዳያስፖራዎች ወደ አገራቸው እየተመለሱ ነው የሚል ነበር፡፡ ሁለተኛው ዜና ደግሞ የቻይና ኮሙኒስት ፓርቲ 18ኛ ጉባኤውን እያካሄደ መሆኑን የሚገልፅ ነው፡፡ ባይገርማችሁ ---- ሁሉ ነገሩ ከኢህአዴግ ጉባኤ ጋር አንድ እኮ ነው /ማን ይሆን የኮረጀው?/ ወደ ሌላ አጀንዳ ከማለፌ በፊት አንድ ጥያቄ ጣል ላድርግ - የኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን አሁንም የህዝብ ንብረት ነው ወይስ ---? /ለጠቅላላ እውቀት ያህል ነው!/  አሁን ወደ ዋናው ወጋችን መግባት እንችላለን፡፡ የዛሬ ወጌን የምጀምረው “ኮንግራ” ብዬ ነው - ኦባማ ዳግም በማሸነፋቸው! (ምርጫው ጦቢያ ቢሆን ኖሮ “ኮንግራ”ም አይቻልም ነበር) በነገራችሁ ላይ እኔ እኮ ኦባማን እንጂ ፓርቲያቸውን ብዙም አልወደውም (መለስን እንጂ ኢህአዴግን ብዙም እንደማልወደው ማለት ነው) እኔ የምለው --- የኦባማ ፓርቲ ምን ልሁን ብሎ ነው ምልክቱን “አህያ” ያደረገው? /ምልክትስ ማለት ንብ ነው!/ እነዚህ አሜሪካኖች ግን የምርጫ ምልክት መምረጥ አያውቁበትም፡፡ የሪፐብሊካኖች  ምልክትም እኮ “ዝሆን” ነው /የባሰ አለና አገርህን አትልቀቅ!/  ትዝ ይላችኋል--- እዚህ አገር  አንዷ የግል ተወዳዳሪ  “ምልክቴ ኮንዶም ነው” ብላ ነበር /የዲኬቲ ማስታወቂያ አስመሰለችው እኮ!/ ለነገሩ ኦባማ ምልክታቸው ምንም ይሁን ምን ምርጫውን በድል ተወጥተዋል፡፡ ደጋፊዎቻቸው በትዊተር ላይ Four more years in the White House! በማለት በኦባማ መመረጥ የተሰማቸውን ደስታ ገልፀውላቸዋል፡፡ ወይ አሜሪካ! ተዓምረኛ አገር እኮ ናት! የዛሬ አራት ዓመት ጥቁር ተመረጠ ተብሎ ጉድ ተባለ! አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ጥቁር ተመረጠና ለሁለተኛ ጊዜ ጉድ እየተባለ ነው፡፡ ባለዝሆን ምልክቱ ሮምኒም “ለዛሬ አልተሳካልዎትም” ተብለው ተሸኝተዋል፡፡ ደግነቱ እሳቸውም ሽንፈታቸውን በፀጋ ተቀብለዋል፡፡ ደስ የሚለው ደግሞ እንደኛ ፖለቲከኞች ተጭበረበረ ብለው አልተነጫነጩም፡፡ /ሳይጭበረበር?/ ምን እንደናፈቀኝ ታውቃላችሁ? ልክ እንደሰሞኑ የአሜሪካ ምርጫ አንዳች ኮሽታ ሳይሰማ በጦቢያ ምድር ምርጫ ሲካሄድ ማየት! /ሲያምርህ ይቅር እንዳትሉኝ!/  እኔ የምለው ግን --- ነፃና ፍትሃዊ ምርጫ ያን ያህል ከባድ ነው እንዴ? /ቁርጠኝነቱ ካለ እኮ ይቻላል/ ዋናው ችግር ምን መሰላችሁ? ሁሉም ተፎካካሪ ገና የምርጫ ውድድር ሳይጀመር የአራት ኪሎን ቤተመንግስት ብቻ እያለመ እኮ ነው! /ስልጣን መመኘት ኀጢያት ነው አልወጣኝም!/ ግን ደግሞ ፕላን “ኤ” እና ፕላን “ቢ” ሲኖር ጥሩ ነው፡፡ አያችሁ --- በቅድመ-ምርጫ “ካላሸነፍኩ ሞቼ እገኛለሁ” ተብሎ ወደ ውድድር ሜዳው ሲገባ በድህረ- ምርጫ ቀውጢ ይፈጠራል፡፡ እንዴ ውጤቱን የሚወስነው እኮ እልህ ሳይሆን “የድምፅ ሳጥን (Ballot)” ብቻ ነው! እናም---  ሮምኒ ዘንድሮ እንዳልተሳካላቸው ሲያውቁ ምን አደረጉ መሰላችሁ? ቶሎ ብለው ስልክ መቱ - ወደ ዋይት ሃውስ፤ ኦባማ ጋ፡፡ ሊሳደቡ፣ ሊያስፈራሩ ወይም ሊያስጠነቅቁ እንዳይመስላችሁ - እሳቸው እቴ! “Congra!” ለማለት ነው እንጂ! “ሚ/ር ፕሬዚዳንት እንኳን ደስ ያለዎት፤ God bless America!” አሉና ስልካቸውን ጠረቀሙ፡፡ ከዚያ በኋላ የሆኑትን የሚያውቁት ፈጣሪና ራሳቸው ሮምኒ ብቻ ናቸው፡፡ ይሄ ማለት ግን አልበሸቁም ወይም አልተንጨረጨሩም ማለት አይደለም፡፡ (እንዴት አይበሽቁ!) ግን ደግሞ እንደ ጦቢያ ፖለቲከኞች እድሜ ልካቸውን ሲበሽቁ ሲቃጠሉ አይኖሩም፡፡ ደግሞም ለአገራቸው ለመስራት የግድ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት መሆን እንደሌለባቸው አሳምረው ያውቃሉ (ቢመረጡ እኮ እሰየው ነበር!) ግን ደግሞ ህዝብ ካልመረጣቸው አልመረጣቸውም ነው፡፡ የአሜሪካና የኢትዮጵያ ፖለቲከኞች ልዩነት እዚህ ጋ ነው፡፡ የአሜሪካዎቹ ህዝብ ሳይመርጣቸው ሲቀር ውሳኔውን ያከብሩለታል፡፡ ሲመርጣቸውም እንዲሁ፡፡ (እንደኛ ቂም መያያዝ የለም!) This is America! ለነገሩ  ሮምኒ ኦባማ ጋ ደውለው “Congra!” ከማለት ውጭ ሌላ ምርጫም የላቸውም ነበር፡፡ እኛ ጋ ግን ብዙ ምርጫ አለን፡፡ ከፈለግን የጐዳና ላይ ነውጥ፤ ከፈለግን ፖለቲከኞችን ሰብስቦ ወህኒ ቤት መክተት፡፡ ከፈለግን ፀረ-ልማትና ፀረ-ሰላም ብለን መፈረጅ ሁሉ መብታችን ነው፡፡ ለምን መሰላችሁ? This is Ethiopia! /ማን ነበር “አገርህ ናት በቃ” ያለው ገጣሚ?/ አያችሁ … ሮምኒ ባይደውሉ፣ ወይም ሊነጫነጩ ቢሞክሩ የአሜሪካ ህዝብ አይምራቸውም … “አፋራም” ይላቸዋል (ወይም ፋራ!) ይሄን ደግሞ ሮምኒ አይፈልጉትም፡፡ አሜሪካውያንም አይፈቅዱትም፡፡ /መታደል እንጂ መታገል አያስፈልግም/ ኦባማም እኮ ዳግም መመረጣቸው ይፋ ከሆነ በኋላ ባደረጉት ንግግር፣ ሮምኒን እና ፓርቲያቸውን አመስግነዋል (ያሸነፈው የተሸነፈውን ሲያመሰግን አልታያችሁም!) በአሜሪካ ግን ይሄም ይቻላል፡፡ አንዴ ሳይሆን በተደጋጋሚ አይተናል፤ ሰምተናል፡፡ (That’s America ብለናል በሆዳችን!) “ከሮምኒ ጋር አውርቼአለሁ፡፡ በምርጫ ዘመቻው ላደረጉት እልህ አስጨራሽ የምረጡኝ ዘመቻ አመስግኜአቸዋለሁ፤ ክፉኛ ታግለንና ተፋጭተን ሊሆን ይችላል፡፡ ያንን ያደረግነው ግን እቺን አገር በጣም ስለምንወዳትና ለመጪው ጊዜዋም በጣም ስለምንጨነቅ ነው” ይሄን ያሉት ኦባማ ናቸው! /ምነው ኢህአዴግ ያለው ቢሆን!/ አያችሁ--- እዚያ እንደኛ አገር ለሥልጣን መፎካከር በጠላትነት አያፈራርጅም፡፡ ፀረ ሰላም፣ ፀረ ልማት፣ ፀረ አገር፣ ፀረ ወዘተ… አያስብልም፡፡ “የተፎካከርነው፤ ክፉኛ የተፋጨነው አገራችንን ስለምንወዳት ነው” በቃ ይሄን ነው ያሉት ኦባማ፡፡ ምናልባት ይሄ እንዴት ተቻለ ትሉ ይሆናል፡፡ መልሱ ቀላል ነው - አገሪቷ አሜሪካ ናታ! (ኢትዮጵያ አሜሪካን መሆን አለባት አልወጣኝም!) ለነገሩ ብልም እኮ አይቻልም፡፡ ኢትዮጵያ ኢትዮጵያ ናት፤ አሜሪካም አሜሪካ፡፡ ኦባማ በንግግራቸው መጀመሪያ ያመሰገኑት ህዝባቸውን ነው - አሜሪካውያንን!! Thank you. Thank you. Thank you so much - በማለት፡፡ ግን የመረጣቸውን ብቻ አይደለም፡፡ በኢህአዴግ ቋንቋ በድምፁ የቀጣቸውንም ጭምር አመስግነዋል - “የኦባማንም ሆነ የሮምኒን ምልክት የያዛችሁ ድምፃችሁ ተሰምቷል” ብለዋል - ኦባማ፡፡ እዚያ ሁለት ዓይነት ህዝብ የለማ! (ልማታዊና ኪራይ ሰብሳቢ!) በቃ ህዝብ ህዝብ ነው፡፡ የኦባማን ዲሞክራት ፓርቲ የመረጠም ሆነ የሮሚን ሪፐብሊካን የመረጠ ለውጥ የለውም፡፡ ዲሞክራሲ ማለት ይኼው አይደለ!! በነገራችሁ ላይ እኚህ ኦባማ በአደባባይ ሚስታቸውን እንደሚወዱም ተናግረዋል፡፡ “አንቺ ባትኖሪ ኖሮ የዛሬውን ኦባማ አልሆንም ነበር” ሲሉ ባለቤታቸውን ሚሼልን አድንቀዋል፤ አሞግሰዋል፡፡ የአሜሪካ ህዝብ ሚስታቸውን ስለወደደላቸውም “ኮርቼብሻለሁ” ብለዋል፡፡ ሁለቱ ሴት ልጆቻቸው ሳሻና ማሊያም “እኮራባችኋለሁ!” ተብለዋል - በአባታቸው በኦባማ፡፡ እኔ የምለው ግን … የእኛ መሪዎች ሚስታቸውንና ልጆቻቸውን እንደሚወዱ ነግረውን ያውቃሉ እንዴ? (ኧረ በፍፁም!) የኢህአዴግም የተቃዋሚዎችም መሪዎች እኮ ስለሚስት፣ ስለልጆችና ስለቤተሰብ ትንፍሽ ብለው አያውቁም! (ያፍራሉ እንዴ?)  (እውነቴን እኮ ነው እንዲህ እንደ ኦባማ የትዳር አጋራቸውን እንደሚያፈቅሩና እንደሚያከብሩ፤ ለስኬታቸውም ትልቅ ሚና እንዳላት ቢነግሩን ቀላል ነገር አይመስለኝም፡፡ ቀላል ቢሆንማ አዳሜ ዝም አይልም ነበር፡፡ ወይስ የወንድ ትምክተኝነት ገና አለቀቀንም? (የሥልጣኔ ችግር ይመስለኛል!) አንድ ሃሳብ አለኝ - ማንኛውም የመንግስት ባለስልጣንም ሆነ የፖለቲካ ፓርቲ መሪ ሚስቱን፣ ልጆቹንና ቤተሰቦቹን እንደሚወድ ለህዝብ እንዲገልፅ የሚያስገድድ ህግና ደንብ ቢወጣስ? (ፍቅር በግዳጅ በሉት!) ነገሩ ቀላል እኮ ነው፡፡ የመንግስት ባለሥልጣናት ሃብታቸውን እንደሚያስመዘግቡት ሁሉ ፍቅራቸውንም ያስመዘግባሉ ማለት ነው - ሌላ ጣጣ ፈንጣጣ የለውም (የፓርቲያችን ባህል አይፈቅድም የሚሉ ባህላቸውን ይለውጡ!) በነገራችሁ ላይ ኦባማ ያሸነፉት ዝም ብሎ በዕድል እንዳይመስላችሁ - ብዙ ታትረውና ተግተው ነው፡፡ ስንት ተናግረውና አሳምነው መሰላችሁ ያሸነፉት፡፡ መቼም ስንት ሺ የምርጫ ሰራዊት እንዳሳለፉ ሳትሰሙ አትቀሩም (ኢህአዴግ የልማት ሰራዊት፣ የጤና ሰራዊት፣ የንግድ ሰራዊት፣ የጥበብ ሰራዊት፣ ወዘተ እንደሚለው) ቢቢሲ ሰሞኑን ባወጣው ዘገባ፤ በኦሃዮ ግዛት ብቻ ለኦባማ የሚቀሰቅሱ 32ሺ854 የበጐ ፈቃድ አገልጋዮች ነበሩ - በሦስት ሰዓት ሽፍት የሚሰሩ፡፡ የምርጫው ዕለት ደግሞ የኢህአዴግን 1ለ5 የሚመስል ስትራቴጂ ተጠቅመዋል ተብሏል፡፡ ኦባማ ወይም ፓርቲያቸው ግን አይደለም፡፡ ራሱ ህዝቡ ነው - መራጩ! ቀደም ብለው ድምፃቸውን የሰጡ የኦባማ ደጋፊዎች አምስት አምስት ባልንጀሮቻቸውን እጃቸውን ይዘው ወደ ድምፅ መስጪያ ጣቢያ እንደወሰዱ ነው ቢቢሲ የዘገበው፡፡ በኢህአዴግ “ጥርነፋ” እንደሚባለው ግን እንዳይመስላችሁ (ኧረ አይገናኝም!) ኦባማን እየደገፉ ነገር ግን ወደ ምርጫ ጣቢያው ለመሄድ የሰነፉ አሜሪካውያንን እንዲመርጡ የማድረግ ማግባባት እንጂ ሌላ ማስገደድ የለውም (ኢህአዴግ ያስገድዳል አልወጣኝም!) በ2002 ምርጫ ኢህአዴግ እንዳደረገው ቤት ለቤት እያንኳኩ ለምርጫ ማትጋትም ይቻላል፡፡ በስልክም እንዲሁ፡፡ (ቡናና ፈንዲሻ ብቻ ነው የቀረው!) እንዲያም ሆኖ ግን ኦባማ ተፎካካሪያቸውን በ99 ነጥብ ምናምን አልዘረሯቸውም፡፡ (ኢህአዴግ በ2002 ምርጫ እንዳሸነፈው!) ለነገሩ በእንዲህ ያለ ከፍተኛ ልዩነት ማሸነፍ እንኳን በአሜሪካ በሌላውም ዓለም ፋሽኑ አልፎበታል - የፋራ ነው እየተባለ ነው! (ብቻ ፉገራ እንዳይሆን!) አንዴ በአልጀዚራ የቴሌቪዥን ጣቢያ የቀረቡ አሜሪካዊ የፖለቲካ ምሁር፤ የ2002 የአራችንን ምርጫ አንስተው ኢህአዴግን ሲተቹት ሰምቼ ግርም አለኝ (“ቅ” መሆን አለባት ብያለሁ - በሆዴ!) በእንዲህ ዓይነት ሰፊ ልዩነት የሚያሸንፉት አምባገነን መንግስታት ናቸው አሉና እነ ዚምባቡዌን መጥራት ጀመሩ፡፡ ከዚህ በላይ መታገስ ስላቃተኝ አልጀዚራን አጥፍቼ የሆሊውድን ፊልም መኮምኮም ጀመርኩኝ (ለምን ልቃጠል!) ለነገሩ እኮ ኢህአዴግ ተቃዋሚዎችን በዝረራ በማሸነፉ ተጐዳ እንጂ አልተጠቀመም እኮ! አንደኛ ተቃዋሚዎች “አጭበርብሮናል” ብለው “ስመጥሩውን” ፓርቲ አሳጥተውታል፡፡ ሁለተኛ ፓርላማው በኢህአዴጋውያን ብቻ ተሞልቶ ፍዝዝ ድንግዝ ብሏል፡፡ ሦስተኛ ደግሞ “የፖለቲካ ምህዳሩ ጠቧል” ለሚለው የተቃዋሚዎች ክስ ጥሩ ማስረጃ ሆናቸው፡፡ ስለዚህ 99 በመቶ ማሸነፍ ከመሸነፍ እኩል ነው ቢባል ያስኬዳል፡፡ ለምን መሰላችሁ? 99 በመቶ ማሸነፍ እኮ አንድም ተቃዋሚ በምርጫው አልተሳተፈም ማለት ነው፡፡ ወይም ደግሞ አንድም ሰው በኢህአዴግ ኩርፊያም ሆነ ቅሬታ የለውም እንደማለት ነው፡፡ ይሄ ደግም ከእውነታው የተፋታ ይመስላል፡፡ ህዝቡ ኩርፊያ ባይኖረውም እንኳ ኢህአዴግ በግድ ማስኮረፉ አይቀርም እኮ (ነገረኛ ነው ማለቴ ግን አይደለም!) በቃ ልማታዊ ኪራይ ሰብሳቢ፤ አብዮታዊ ዲሞክራሲ ኒዮሊበራሊስት፤ የሰላም ሃይሎች የጥፋት ሃይሎች ወዘተ እያለ ህዝቡን በጐራ መክፈል አመል ስለሆነበት ሁሌም የሚያኮርፍ አይጠፋም፡፡ እናላችሁ … ይሄን አመሉን እርግፍ አድርጐ ካልተወ፣ 99 በመቶ አሸነፍኩ ቢል ጥርጣሬ ውስጥ መግባቱ አይቀርም፡፡ እኔ የምለው ግን … ኢህአዴግ በራሱ ከተማመነ ለምን የፖለቲካ ሜዳውን ለተቃዋሚዎች በሰፊው አይለቅላቸውም (ፆሙን ያደረ ሜዳ ሞልቶ የለም እንዴ?)እኔ የምለው ግን ኦባማ የፈለገ ህዝብ ቢወዳቸው አራት ዓመታቸውን ሲጨርሱ ዋይት ሃውስን ለቀው መውጣት አይቀርላቸውም አይደል … (ወደው ነው!) ያልጨረስኩት ልማት አለ … መንገድ … ኮንዶሚኒየም … ግድብ መገንባት ይቀረኛል ቢሉ ማንም የሚሰማቸው የለም፡፡ ለምን ቢባል … አዲሱ መሪ ይጨርሰዋላ! እንዲህ ያለው ምክንያት የሚሰራው ምናልባት ለልማታዊ መንግስት ብቻ ሳይሆን አይቀርም - ትኩረቱ ልማት ነዋ! ኢህአዴግ አገሪቱን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ለማሰለፍ የ40 ዓመት ሥልጣን ያስፈልገኛል አላለም? ወይም ሃሳቡን ቀይሯል?  የዛሬ ፖለቲካዊ ወጌን የምቋጨው ኦባማ ከተፎካካሪያቸዉ ጋር ስለሚኖራቸው ቀጣይ ግንኙነት በተናገሯት ዓረፍተ ነገር ነው፤ “በቀጣዩቹ ሳምንታት ከሮምኒ ጋር ተቀምጠን እቺን አገር ወደፊት ለማራመድ በምንችልባቸው ጉዳዮች ላይ ለመመካከር በተስፋ እጠብቃለሁ” (እርግጠኛ ነኝ ለአፋቸው ያህል አይደለም!)ኢህአዴግ ሚዲያውን ለምርጫ ቅስቀሣም ሆነ ፖሊሲውን በስፋት ለህዝቡ ለማድረስ እየተጠቀመበት እንደሆነና በፓርቲው ንብረትና በኢትዮጵያ ህዝብ ንብረት መካከል ያለው ልዩነት እንደማይታወቅ በመግለፅ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የሚያቀርቡትን አቤቱታ ተቀባይነት የለውም ያሉት ኃላፊው፤ ህዝቡ ኢህአዴግን መንግስት አድርጐ ሲመርጥ ፖሊሲውን በስፋት እንዲያስተዋውቅ እውቅናና ይሁንታ ሰጥቶታል ብለዋል፡፡ በተቃዋሚ ፓርቲዎች የሚቀርቡትን ቅሬታና አቤቱታዎች በጋራ ምክር ቤት እያዩ መፍትሔ እንደሚፈልጉና በተባለው ጉዳይ ግን የቀረበላቸው አንዳችም ቅሬታ አለመኖሩን አቶ ተመስገን ጨምረው ገልፀዋል፡፡    የምርጫ ሥነ ምግባር ህግ ከፈረማችሁ በኋላ የዚህ ዓይነት ጥያቄ ማቅረብ የሥነ ምግባር ህጉን እንደመጣስ አያስቆጥራችሁም ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ፤ በ2002 ዓ.ም ምርጫው በተካሄደ በ3ኛው ቀን ኢህአዴግ በምርጫው ማሸነፉን በመግለፅ የምርጫ ሥነ ምግባሩን በግንባር ቀደምትነት ጥሶታል ብለዋል፡፡

የምርጫ ቦርድ ለጥያቄያቸው ተገቢ ምላሽ ካልሰጣቸው ሰላማዊና እርምጃ እንወስዳለን ይህ እርምጃም ሰላማዊ ሰልፍን ጨምሮ ህዝባዊ ንቅናቄ እስከመፍጠር የሚደርስ ነው ሲሉም አክለዋል፡፡ የምርጫ ቦርድ የህዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ኃላፊ ወ/ሮ የሺ ፈቃድ፤ ፓርቲዎቹ ስላቀረቡት ጥያቄ የሚያውቁት ነገር አለመኖሩን ገልፀው፣ ጥያቄያቸው በቦርድ የሚፈታና አግባብነት ያለው ከሆነ በወቅቱ ምላሽ እንደሚሰጧቸው ተናግረዋል፡፡ ቦርዱ ለገዥው ፓርቲ የሚያዳላና ገለልተኛ አይደለም በማለት ፓርቲዎቹ ያቀረቡትን አቤቱታ አስመልክቶ ሲናገሩም የ2002 ምርጫ ሲጠናቀቅ ቦርዱ አዘጋጅቶት በነበረው የምርጫ ግምገማ መድረክን ጨምሮ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በቦርዱ ቅሬታ እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡ ተቃዋሚ ፓርቲዎች የዚህ አይነት ቅሬታ የሚያቀርቡት ሁልጊዜም ምርጫ ሲቀርብና የምርጫ ሙቀት ሲኖር ነው በማለትም አክለዋል - ወ/ሮ የሺ፡፡ የኢህአዴግ የአጋር ድርጅቶችና አደረጃጀቶች ዘርፍ ኃላፊ አቶ ተመስገን ጥላሁን በበኩላቸው፤ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ በምርጫው ሂደት ላይ የሚያነሷቸው ቅሬታዎች አግባብ ናቸው የሚል እምነት እንደሌላቸው ጠቁመው፣ ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ ምርጫ ቦርድንም ሆነ ሚዲያውን ከኢህአዴግ ጋር ለማላተም የሚያደርጉት ሙከራ ህገወጥ ነው ብለዋል፡፡የኢህአዴግ አምባገነናዊ ሥርዓት እየተባባሰ ሄዷል ያሉት የፓርቲዎቹ ተወካዮች፤ ከምርጫ 2002 በኋላ በርካታ የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮች ለእስር መዳረጋቸውንና የመናገርና የመፃፍ ነፃነትን በማፈንም የፕሬስ ሕትመቶችን እስከመዝጋት የደረሰ እርምጃ መወሰዱ፤ የሽብርተኝነት አዋጅ መውጣቱም የኢህአዴግ አምባገነንነት ውጤት ነው ሲሉም የፓርቲዎቹ ተወካዮች በመግለጫው ላይ ተናግረዋል፡፡ፓርቲዎቹ ትናንት በአንድነት ፓርቲ ቢሮ ውስጥ በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ፤ የመድረክ ፓርቲ የስራ አስፈፃሚ አባልና ለዚሁ ጉዳይ የተቋቋመው ኮሚቴ ሰብሣቢ የሆኑት አቶ አሥራት ጣሴ እንደተናገሩት፤ ምርጫ ቦርድ በግንቦት ወር በሚካሄደው የአካባቢ ምርጫ አፈፃፀም የጊዜ ሰሌዳ ላይ ለመወያየት በአዳማ ከተማ ጥቅምት 15 ቀን 2002 ዓ.ም አዘጋጅቶት በነበረው ስብሰባ ላይ ከጊዜ ሰሌዳው በፊት በምርጫው ፍትሃዊነት ላይ በቅድሚያ ሊወያዩ እንደሚገባ ለቦርዱ ጥያቄ ማቅረባቸውን ገልፀዋል፡፡ ምርጫ ቦርድ በወቅቱ ጥያቄያቸውን ተቀብሎ ተገቢ ምላሽ ሊሰጣቸው ባለመቻሉ በስብሰባው ላይ ከነበሩት የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጋር የጋራ ምክክር አድርገውና ፒቲሽን ተፈራርመው ጥያቄያቸውን በጋራ ለምርጫ ቦርዱና ለጠቅላይ ሚ/ር ፅ/ቤት ማቅረባቸውን ተናግረዋል፡፡ምርጫ ቦርድ ለጥያቄያችን ተገቢና በቂ ምላሽ ሰጥቶን ባያውቅም ጥያቄዎቻችንን ከማቅረብ ወደኋላ አንልም ያሉት የፓርቲዎቹ ተወካዮች፤ ቦርዱ ከፈረሱ በፊት ጋሪውን በማስቀደም ከምርጫው ነፃ መሆንና ከፍትሃዊነቱ አስቀድሞ በምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ላይ  ለመወያየት መሞከሩ አግባብነት የሌለው ነው ብለውታል፡፡ ከምርጫ ቦርድ መልካም መልስ የማግኘት የዋህነት ባይኖረንም ጥያቄያችንን ከማንሳት ወደ ኋላ አንልም ያሉት ፓርቲዎቹ ለጥያቄያችን ተገቢና በቂ ምላሽ እስካላገኘን ድረስ ምርጫውን ለማጀብ ፍቃደኞች አይደለንም ብለዋል፡፡ በመጪው ግንቦት ወር የሚካሄደውን የአካባቢና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምርጫ አስመልክቶ ከምርጫው ጊዜ አስቀድሞ በምርጫው ፍትሃዊነት፣ ዲሞክራሲያዊነትና ነፃ መሆን ላይ ውይይት መካሄድ እንደሚገባው በማሳሰብ ሰላሣ አራት ተቃዋሚ ፓርቲዎች ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ ማቅረባቸውን ገለፁ፡፡ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፅ/ቤት ያቀረቡት ጥያቄ ደብዳቤው ማህተም የለውም በሚል ምክንያት ተቀባይነት ሣያገኝ መቅረቱንም ተናግረዋል፡፡ ምላሽ የሚሰጠው ተገቢ ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ ነው - ምርጫ ቦርድ ምርጫ ቦርድን ከኢህአዴግ ጋር ማላተማቸው አግባብ አይደለም - ኢህአዴግ  ለጥያቄያችን ምላሽ ካልተሰጠን ምርጫውን ለማጀብ ፍቃደኞች አይደለንም -  ፓርቲዎች
http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=5187:34-%E1%89%B0%E1%89%83%E1%8B%8B%E1%88%9A-%E1%8D%93%E1%88%AD%E1%89%B2%E1%8B%8E%E1%89%BD-%E1%89%A0%E1%88%9D%E1%88%AD%E1%8C%AB%E1%8B%8D-%E1%8D%8D%E1%89%B5%E1%88%83%E1%8B%8A%E1%8A%90%E1%89%B5-%E1%88%8B%E1%8B%AD-%E1%8C%A5%E1%8B%AB%E1%89%84-%E1%8A%A0%E1%88%88%E1%8A%95-%E1%8A%A0%E1%88%89&Itemid=20