POWr Social Media Icons

Wednesday, November 7, 2012

በወረዳው ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ 1ዐዐ በላይ ሰዎች እንዲሁም ከሀይማኖት መሪዎች ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመከላከል ዙሪያ ሰሞኑን ውይይት ተካሂዷል፡፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ ሮማን ማሞ እንደገለፁት መንግስታዊ ካልሆኑ በጎ አድራጊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ያለ እድሜ ጋብቻ፣ ጠለፋና አሰገድዶ የመድፈር ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡
ከዚሁ በተያያዘም የቤተሰብ ምጣኔ፣ በሴት ልጅ ግርዛትና በተዛማጅ ችግሮች ዙሪያ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ትምህርት እየተሰጠ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
በአለታ ጩኮ ወረዳ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኡየሱስ የምግብ ዋስትናና ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ አቶ አብርሃም ቲራሞ በበኩላቸው ቤተክርስቲያኗ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ከመከላከል ጎን ለጎን የጤና ለማት ሠራዊት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩሏን ድርሻ እየተወጣች እንደምትገኝ መግለፃቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡
የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ታሪኩ ታደሰ አንዳስታወቁት በወረዳው የሰለጠኑ ሞዴል ቤተሰቦችን በ1 ለ5 ቁርኝት በማደራጀትና የየግላቸውን እቅድ እንዲያዘጋጁ በማድረግ ህብረተሰቡ የግልና የአካባቢ ንፅህናን እንዲጠበቅ መደረጉን ገልፀዋል፡፡
በተያዘው የበጀት ዓመትም ጽህፈት ቤቱ ተላላፊ በሽታዎችን በመከላከል ረገድ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የተጠናከረ የማህበረተሰብ ውይይቶች በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ የጠቆሙት ኃላፊው በተለይም ከወረዳው ወባማ በሆነ 6 ቀበሌያት ለእያንዳንዱ ቤተሰብ እስከ 5 አጎበር ከመከፋፈሉ በተጨማሪ የኬሚካል ርጭትም መከናወኑን ተናግረዋል፡፡
የጤና ተቋማት ተደራሽነት ለማስፋፋት በወረዳው አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙ 5 ጤና ጣቢያዎች በተጨማሪ በመንግስት በጀት በ2ዐዐ4 ግንባታቸው እየተገነቡ ካሉ ሁለት አዳዲስ ጤና ጣቢያዎች የአንደኛው ግንባታ ተጠናቆ ርብርብ መደረጉንና በወረዳው ዋና ከተማ በቀባዶ አንድ ሆስፒታል በመገንባት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች እንደዘገበው፡፡
በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ የሴታሞና አካባቢው መሠታዊ ሁለ ገብ የገበሬዎች አገልግሎት ህብረት ስራ ማህበር ግማሽ ሚሊዮን በሚበልጥ የገንዘብ ድጋፍ በሁለት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ሁለት የመማሪያ ክፍሎችን እያስገነባ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የማህበሩ ሊቀመንበር አቶ ቢፋቶ ብሬ አንደገለፁት መንግስት የትምህርት ተደራሽነትን ለማስፋፋት እያደረገ ያለው ጥረት ስኬታማ እንዲሆን ማህበራትም የራሳቸውን ድርሻ ማበርከት ይኖባቸዋል፡፡
በዚህ መነሻ ማህበሩ ሴታሞና ሾእቾ በተባሉ ሁለት ቀበሌያት የሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ለማስፋፋት በተያዘው እቅድ መሠረት ለእያንዳንዳቸው ደረጃቸውን የጠበቁ አንዳንድ ብሎክ እያስገነባ ይገኛል ብለዋል፡፡
ትምህርት ቤቶቹ በተጀመረው የትምህርት ዘመን አገልግሎት እንዲሰጡ ግንባታቸውን እየተፋጠነ መሆኑን የተናገሩት ሊመቀንበሩ ከ2ዐ ሺህ በላይ ብር ከማህበሩ ወጪ በማድረግ በ4 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ 1 ሺህ 354 ተማሪዎች የትምህር ቁሳቁስ ድጋፍ መደረጉንም ጠቁመዋል፡፡
የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት እንደዘገበው፡:
http://www.smm.gov.et/_Text/26TikTextN805.html

አዋሳ ጥቅምት 28/2005 ከተለያዩ የገቢ አርእስቶች ከ52 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የሲዳማ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን አስታወቀ። በመጀመሪያ ሩብ ዓመት የተሰበሰበው ይኸው ገቢ ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር በ6 ሚሊዮን ብር ብልጫ ያለው ነው። ገቢዉ የተሰበሰበው ከቀጥተኛና ቀጥተኛ ካልሆኑ ታክሶች ፣ከማዘጋጃ ቤት ገቢና ከሌሎች የገቢ አርእስቶች መሆኑን የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ተሻለ ቡላዶ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ገልጠዋል ። ጽህፈት ቤቱ ከሩብ ዓመቱ ዕቅድና ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ብልጫ ያለው ገቢ ለመሰብሰብ የቻለዉ በዞኑ ለሚገኙ ግብር ከፋዮች የግንዛቤ ማጎልበቻ ስልጠናዎችን በመስጠት፣ የታክስ ስርዓቱን በዞኑ ወረዳዎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ በማድረግና ዘመናዊ የታክስና ቀረጥ መረጃ ስርዓት በመዘርጋት መሆኑን አስታዉቀዋል ። በዞኑ በሚገኙት የይርጋለምና አለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደሮች ያሉ ግብር ከፋዮች የሽያጭ መመዝገቢያ መሣሪያ መጠቀም እንዲችሉ ለማድረግ የኔት ወርክ ዝርጋታ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝና ለግብር ከፋዩ ማህበረሰብ ስለመሣሪያው ስልጠና በመስጠት በሁለት ወራት ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አቶ ተሻለ ገልጸዋል። ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ አዳዲስ ግብር ከፋዮችን ወደ ታክስ ስርዓቱ በማስገባትና ቀድሞ የነበሩ ግብር ከፋዮችን ደረጃ ገምግሞ በማሳደግ በተያዘው የበጀት ዓመት 344 ሚሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ መሆኑን አስታውቀዋል። በሩብ ዓመቱ 1ሺ600 አዲስ የደረጃ ሐመሩ ሐ ግብር ከፋዮች ወደ ስርዓቱ መግባታቸውንና 923 የደረጃ ሐመሩ ሐ ግብር ከፋዮች ወደ ደረጃ ለ ግብር ከፋይነት ማሳደግ መቻሉን አስታውቀዋል።
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=3224&K=1
አዋሳ ጥቅምት 28/2005 በሀዋሳ ከተማ ለዘንድሮ በጀት አመት በተመደበ ከ700 ሚሊዮን ብር በጀት ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች እየተካሄዱ መሆናቸውን የከተማው አስተዳደር ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ገለጸ ። 
ለፕሮጀክቶቹና ፕሮግራሞቹ ማስፈፀሚያ የሚዉለዉ ወጪ በአብዛኛው በከተማው አስተዳደር ገቢ የሚሸፈን መሆኑ ተመልክቷል ። 
የመምሪያው ምክትል ሃላፊ አቶ አሻሬ ኡጋ ዛሬ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት እየተካሄዱ ካሉት የልማት ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞቹ መካከል አስፓልት መንገድ ግንባታን ጨምሮ የመጠጥ ውሃ፣ የተቀናጀ የቤቶች ልማት፣ የጤና፣ የትምህርት፣ የግብርናና ሌሎችም ይገኙበታል፡፡ 
በተለይ በመንገድ ልማት ዘርፍ የ6 ነጥብ 4 ኪሎ ሜትር አዲስ አስፓልት ግንባታና የ4 ኪሎ ሜትር የነባር አስፓልት ጥገና፣ የ160 ኪሎ ሜትር አዲስ የጠጠር ምንገድ ስራና የ144 ኪሎ ሜትር የነባር መንገዶች ደረጃ የማሻሻል ተግባራት እንደሚከናወኑ አስረድተዋል፡፡

እንዲሁም የከተማው የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ለማሻሻል ከ253 ሚልዮን ብር በላይ የስድስት ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች ቁፋሮ ፣ የፓምፕ ተከላ ፣ የዉሀ ቧንቧ መስመር መዘርጋትና ሌሎች ተጓዳኝ ስራዎች እየተከናወኑ መሆናቸዉን አቶ አሻሬ አስታዉቀዋል ። የመኖሪያ ቤት እጥረት ለማቃለል ቀደም ብለው የተጀመሩ የ1ሺህ 890 ቤቶች ግንባታ በማጠናቀቅ ለህብረተሰቡ የማሰረከብ ስራ እንደሚካሄድም ተናግረዋል፡፡

 የከተማው ጤና አገልገሎት ሽፋንም አሁን ካለበት 70 በመቶ ወደ 92 በመቶ ለማሳደግ የአንድ አዲስ ጤና ጣቢያና ሌሎች ቀደም ብለው የተጠናቀቁ ጤና ጣቢያዎችን በሰው ሃይልና በቁሳቁስ በማደራጀት ለአገልገሎት የማብቃት ስራ እንደሚከነወንም ገልጠዋል ። በከተማው አስተዳደር በየደረጃው የሚሰጠው ትምህርት ጥራቱን ለማስጠበቅ ውስጣዊ ብቃቱንና ተገቢነቱን ለማሻሻል እንዲሁም ፍትሃዊ የትምህርት አቅርቦት እንዲረጋገጥ የሚያስችሉ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስረድተዋል ። 
የከተማው የመሬት አጠቃቀም ስርዓት ዘመናዊ በማድረግ የነዋሪውን እርካታ ለማሳደግ የከተማው ዕድገት በዘመናዊ የከተማ ፕላን እንዲመራ ይደረጋል ብለዋል፡፡ በከተማው ስምንቱም ክፍለ ከተሞችና 32 ቀበሌዎች ያለው ሲቪል ሰርቪሱ የልማት ሃይልነቱን ለማጎልበት በመንግስት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂ ላይ ስልጠና በመስጠት የማስፈፀም አቅሙን ለመገንባት ትኩረት መሰጠቱንም አስረድተዋል፡፡ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ መነሻ በማድረግ በ2005 የበጀት ዓመት የተቀመጡ ግቦችን ለማሳካት በስራ ዕድል ፈጠራ፣ በመሰረተ ልማት አቅርቦት፣ በቱሪዝምና ኢንቨስትመንት፣ በመልካም አስተዳደር ሁሉ ህብረተሰቡን በማሳተፍ የሚደረገው የተቀናጀ ርብርቦሽ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡ በዘመኑ ለሚካሄዱት ለእነዚህ ዘርፈ ብዙ የልማት ፕሮጀክቶችና ፕሮግራሞች ማስፈጸሚያ ወጪ በአብዛኛው በከተማው አስተዳደር የውስጥ ገቢ የሚሸፈን ቢሆንም በተወሰነ ደረጃ የመንግስት ድጎማ፣ የውጭ ብድርና ዕርዳታ እንደሚታከልበት አቶ አሻሬ አመልከተዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=3235&K=1