POWr Social Media Icons

Sunday, October 7, 2012
(የሲዳማ ተወካዮች እነማናቸው?)
ካለፈው የቀጠለ
ለመሆኑ በተለይ በዚህ ሳምንት ያወጡት የኣቋም መግለጫም ሆነ ወሳኔዎቹ በርግጥ የሲዳማን ህዝብ ይጠቅማሉ? ወይስ የሲዳማን ህዝብ ጥቅም ባያስጠብቁም የደኢህዴን ፖሊስ ለማስፈጸም ያህል የተወሰዱ እርምጃዎች ናቸው?
ይህ የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር ከሲዳማ ተወላጆች ለመንጠቅ ታስቦ የተዘጋጀው ጽሁፍ ሆነ እቅድ በቀላሉ ልሳካ እንደማይችል ኣዛጋጆቹ ጠንቅቀው ስለምያውቁ ነበረ ሃሳቡን ለውይይት ኣዘጋጅተውት የነበሩት።


ብዙዎቻችን እንደምናውቀው ደኢህዴን የዛሬ ሶስት ወራት በፊት የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር በጋር ለማስተዳደር በምል ያዘጋጀው የውይይት ጽሁፍ ከሰፊው የሲዳማ ህዝብ እጅ ቀድሞ ገብቶ ለእቅዳቸው ኣለመሳካት ለጊዜውም ብሆን ሳንካ ሆኗል። በጊዜው የክልል ባለስልጣናት ስለ የውይይት ጽሁፉ የተለያዩ መግለጫዎችን መስጠታቸው የምታወቅ ሲሆን በደቡብ መገናኛ ብዙሃን ቀርበው የበሬ ወለደ ወሬ ነው በማለት ህዝብ ለመዋሸት መሞከራቸው እንዲሁ የምታወስ ነው።

በወቅቱም ብሆን ኣንዳንድ ውስጥ ኣዋቂ ምንጮ እንዳሉት የክልሉ ባለስልጣናት በሬ ወለደ ወሬ ነው በማለት ያስወሩት የሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር የመበረዝ ኣካሄድ ድርጅቱ ጊዜ ወስዶ ተዘጋጅቶበት መክሮ እና ዘክሮ ያዘጋጀው የውይይት ጽሁፍ መሆኑን ነበር። ይህ የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር ከሲዳማ ተወላጆች ለመንጠቅ ታስቦ የተዘጋጀው ጽሁፍ ሆነ እቅድ በቀላሉ ልሳካ እንደማይችል ኣዛጋጆቹ ጠንቅቀው ስለምያውቁ ነበረ ሃሳቡን ለውይይት ኣዘጋጅተውት የነበሩት። ታዲያ ያን ጊዜ የሲዳማ ህዝብ ባሳየው ህዝባዊ ንቅናቄ ተደናግጠው ሀሳቡን ለማድበስበስ ጥረት ኣድርገው ህዝቡን በማረጋጋቱ ረገድ ተሳክቶላቸው ማለት ይቻላል።

ነገር ግን የወቅቱ የሲዳማ ህዝብ ንቅናቄ ለደኢህዴን ኣመራሮች ኣንድ ትምህርት የሰጣቸው ሲሆን ይህን መሰል በሲዳማ ህዝብ ዘንድ ሰንሴቲቪ የሆነ ጉዳይ እንዲሳካላቸው ካሰፈለገ ጉዳዩን በቀጥታ ከህዝብ ጋር መክሮ ና ዘክሮ ከመወሰን ይልቅ የራሳቸውን ኣመራሮችን ሰብስቦ እንድወሰኑ በማድረግ ካዛም ውሳኔ የተሰጠበትን ጉዳይ ወደ ህዝቡ ማውረድ እንደ ብቸኛ ኣማራጭ እንድወስዱ ኣድርጓል። ይህም ታላቅ ስህተት እንዲፈጽሙ ኣድርጓቸዋል። ስለዚህም ኣሁን ጊዚያቸውን ጠብቀው ኣካሄዳቸውን ቀይረው በራሳቸው መወሰን የማይችሉትን የሲዳማ ኣመራሮችን ስብስበው ያለ ህዝቡ ፍቃድና ፈላጎት በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ ሌሎች ብሄሮችን ለመቀላቀል ወስነዋል። በአቋም መግለጫቸውም የሀዋሳን ከተማ የአመራር ስምሪት ከኪራይ ሰብሳቢነት የጸዳና ብቁ አመራር ከየትኛውም መዋቅር ቢመደብ ትግሉን ለማስቀጠል ቃል ገብተዋል፡፡

ከላይ ከኣዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚወርድላቸውን ጸረ ሲዳማ ኣጀንዳ ነው እያስፈጸሙ እንጂ ያሉት ከመቼ ወዲህ ነው በራሳቸው ኣጀንዳ ኖሯቸው ለኣጀንዳቸው መተግበር ሰርተው የምያውቁት?

ደኢህዴን እንደሞኝ ተረት እየደጋገመ የሃዋሳን ከተማ ከሲዳማ ኣስተዳደር ለመንጠቅ የምዶልተው ጉዳይ የሲዳማ ህዝብ በመንገሽገሹ የተነሳ የሃዋሳ ከተማ ጉዳይ ብሎም ደኢህዴን በሲዳማ ህዝብ ላይ የምፋጽመው ደባ ለኣንደና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንድያገኝ በምል የራሰ የሆነ የክልል ኣስተዳደር ይገባኛል ጥያቄ ኣንግቦ ያደረገውን ከዳር እስከ ዳር ያናወጠ ህዝባዊ ንቅናቄ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ሳይሆን የጸረ ሰላም ኃይሎች ጥያቄ ነው በማለት ሰፊውን የሲዳማ ህዝብ ጸረ ሰላም ኃይል በማለት የክልሉ ባለስልጣናት ተሳልቀዋል።

የድፍረታቸው ድፍረት እንደፈለጉ በሚያዙት ሚዲያ ቀርበው የሲዳማ የክልል ጥያቄውን ያነሱት ግለሰቦች ናቸው እነርሱም ብሆኑ የኪራይ ሰብሳቢ እና የጸረ ሰላም ኃይሎች የህብረተሰቡን አቅጣጫ ለማስቀየር ያደረጉት ጥረት ያለመሳካቱንና ህልማቸው ቢሳካ ኖሮ በውስጠ ድርጅቱ ላይ የሚፈጥረው ተጽእኖ የከፋ ይሆን ነበር ብለዋል፡፡ እዚህ ላይ ደኢህዴን የምባለው የጥቅት የሲዳማ ኣመራሮች ድርጅት እንጅ ለሲዳማ ህዝብ የቆሞ ድርጅት ኣለመሆኑን የረሱት ይመስላል።

የኪራይ ሰብሳቢነት አስተሳሰብ በታየባቸው አንዳንድ አመራሮች ላይም በየደረጃው በተካሄደው የሂስ ግለሂስ መድረኮች ላይ የእርምት እርምጃ መወሰዱንም የገለጹት ርዕሰ መስተዳደሩ በቀጣይም የኪራይ ሰብሳቢነትን አስተሳሰብ ከምንጩ የማድረቁ ተግባር ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡እዚህ ላይ ሌላው የረሱት እና ልያውቁት የምገባው ነገር ኣብሯቸው ያሉት ኣመራሮች ቢሆኑ ለሆዳቸው ብለው እንጂ በነጻ ኣዕምሮኣቸው ማሰብ የምችሉ መሆናቸውን ነው። በራሳቸው የምያስቡትንም እና ለሲዳማ ህዝብ ጥቅም መከበር የታገሉ የደኢህዴን ኣመራሮችም ቢሆን በክራይ ስብሳቢነት ልኮነኑ እንደማይገባ ብሎም ዋነኛ ኪራይ ሰብሳቢዎች ጸረ ሲዳማ የሆነት በውሳኔው ላይ የተሳተፉት የሲዳማ ኣመራር ተብዬዎች መሆናቸውን ነው።

በመሆኑም በየጊዜው የሚፈጠሩ የጥገኘነት እና የጸረ ሰላም ኃይሎች የማደነጋገሪያ አጀንዳ የማይበገር አብዮታዊ ስብዕና የተላበሰ የህዝበ መሪነት ሚናችንን እንወጣለን ብለዋል የምሉት ማንን ለማለት እንደፈለጉ ለራሳቸውም ቢሆን ግልጸ የሆነላቸው ኣይመስልም፡፡ ምክንያቱም እነዚሁ ኣመራሮች የጸረ ሲዳማ ኃይሎች ጥገኛ ኣመለካከት ኣራማጆች ናቸውና። ከላይ ከኣዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር የሚወርድላቸውን ጸረ ሲዳማ ኣጀንዳ ነው እያስፈጸሙ እንጂ ያሉት ከመቼ ወዲህ ነው በራሳቸው ኣጀንዳ ኖሯቸው ለኣጀንዳቸው መተግበር ሰርተው የምያውቁት?
ለመሆኑ ይህ መግለጫ የወላይታው ሰውዬ ጠቅላይ ሚኒስትር መሆኑን ተከትሎ ወደ ወላይታዎቹ ጠጋ በማለት ኣንጄታቸውን ለመብላት ተፈልጎ ይሁን የምል ጥያቄም ጭሮብኛል።በኣቋም መግለጫው ላይ ካነሷቸው ጉዳዮች መካከል ሌላው እኔን በተለይ የገረመኝ ጉዳይ የሲዳማ ህዝብ ከሌላቸው ህዝብ ጋር ያለውን ተፋቅሮ የመኖር ባህል በተመለከተ ያነሱት ነጥብ ነው። የሲዳማ ህዝብ ከየትኛውም ብሔር እና ብሔረሰብ ጋር ተፋቅሮ እና ተከባብሮ የኖረ ወደፊትም የሚኖር ስለመሆኑ የእነርሱን ምስክርነት ኣያሻውም ነገር ግን ለዘመናት ተከባብሮና ተዋዶ የኖረውን የሲዳማንና የወላይታን ህዝብ ለማጋጨት ብሎም ለማለያየት ሲንቀሳቀሱ... በማለት በኣቋም መግለጫቸው ያነሷት ነጥብ ወዴት ወዴት እንድል ኣስብሎኛል። ምክንያቱም በሲዳማ እና ወላይታ ህዝቦች መካከል የተለየ ግጭት የለም ኖሮም ኣያውቅም፤ ባይሆን ሆኖም ግጭት እንዳለ ኣስመስለው መግለጨ ስጥተዋል።

ከላይ እንዳነሳሁት የሰሞኑ ውሳኔው የሲዳማን ህዝብ ልጠቅም የምችልበት ሁኔታ ምን እንደሆነ በግልጽ እነኝሁ የሲዳማ ኣመራሮች መግለጽ ኣልቻሉም። እንዳውም ከግል ጥቅም ኣንጻር ካልሆነ በስተቀር የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር የሲዳማ ህዝብ በመንጠቅ ለሌላው መስጠት እንዴት ሲዳማን ልጠቅም እንደምችል ለማብራራት እነሱም ብሆኑ ትንሽም ብሆን ረቀቅ ያለ ኣእምሮ ሳያስፈልጋቸው ኣይቀርም፤ በኣጠቃላይ የፍቅር ከተማዋን መነጠቅ ለሲዳማ እንዴት ነው የምጠቅመው? የራሱን ለሌላው ኣሳልፎ እየሰጠ እንዴት ነው ተጠቃሚ የምሆነው?

የሲዳማ የክልል ጥያቄ እነርሱ እንደምሉት የግለሰቦች ጥያቄ ሳይሆን የሰፊው የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ መሆኑን በግልጽ ኣይደለም ባሉበት ሚዲያ ቀርበው የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ መሆኑን እስክያረጋግጡ ድረስ የሲዳማ ህዝብ ከእነርሱ ጋር ምንም ኣይነት ውይይት የምያደርግ ኣይመስለኝም።

እንደምናውቀው የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ እና ፍላጎት የኣስተዳዳር ኣከባቢውን በክልል ደረጃ ማስተዳደር ነው። የሲዳማ ህዝብ ለዚሁ ዓላማ ላለፉት ከሰላሳ በላይ ዓመታት ልጆቱን መስዋዕት ኣድርጓል በማድረግም ላይ ነው። ታዲያ የህዝቡ ፍላጎት የሃዋሳን ከተማ ኣስተዳደር መነጠቅ ሳይሆን ከዛም ባለፈ የራሱን ክልላዊ ኣስተዳደር መመስረት ነው። የህዝቡ ፈላጎት ይህ በሆነበት በኣሁኑ ወቅት ይህ መሰል የህዝቡን ፈላጎት ያላገናዘበ ውሳኔ መውሰድ የሲዳማ ህዝብ ፋላጎት እና ጥቅም ከማስጠበው ይልቅ የደኢህዴንን ፈላጎት ማስጠበቅ ነው።

ደኢህዴን የሲዳማን ህዝብ ፍላጎት እና ጥቅም ካላስጠበቀ ለሲዳማ ህዝብ ምኑ ነው? እኔ እንደማስበው ከሆነ በየትኛው ዓለም የምገኙት መንግስታት እና የፖለቲካ ድርጅቶች የቆሙላቸውን ህዝብ ፈላጎት እና ጥቅም ለማስጠበቅ ቀን ለሌት ስሰሩ ነው የምታዩ እንጂ በየትኛውም ኣጋጣም ከወከለው ህዝብ በተቃራኒ የቆሞ ድርጅት በታሪክ የለም ከደኢህዴን በስተቀር ማለት ነው። ደኢህዴን ከውሳኔ በኃላ ህዝቡን በውሳኔያቸው ላይ ለማወያያት ዳርዳር እያለ ነው። ተሳክቶላቸው እንኳን ህዝቡን ማሰባሰብ ከቻሉ፤ እኔ ኣሁን እያጓጓኝ ያለው የሲዳማ ኣመራሮች ያሳለፉት ውሳኔ የሲዳማን ህዝብ እንዴት ልጠቅም እንደምችል ለህዝቡ ቀርበው የምያብራሩበት ጊዜ ነው።በገዢው ሰፈር ጎራ ለይቶ ከተለኮሰው የቡድን ፖለቲካዊ ፍጥጫ እና ሴራ ጀርባ አገር እና ህዝብን የሚጎዳ አደገኛ ተግባር በግልጽ እና በስውርእየተካሄደ እንዳለ ከተለያዩ የፓርቲው ምንጮች የተገኙ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በተለይ በብአዴን እና በህወሃት ቱባ አመራሮች መካከል ስር ሰዶ የቆየው እና የአቶ መለስን ህልፈት ተከትሎ ያገረሸው የውስጥ ሽኩቻ ሁለት ቡድኖች የሃይል አሰላለፋቸውን ለማጠናከር «ይረዱናል » የሚሏቸውን የሌሎች ፓርቲ ሹማምንት እና የመከላከያ የጦር አዛዦች ከጎን የማሰለፉን ተግባር ቀጥለውበታል።ለግንዛቤ እንዲረዳ የሃይል አሰላለፉን በጥቂቱ በመዳሰስ ወደ ዋናው ነጥብ እናምራ።

ከበረከት እና ዓዜብ ጎን በመሰለፍ ቀዳሚ የሆኑት አቶ ተፈራ ዋልዋ እና አዲሱ ለገሰ ናቸው።አቶ አዲሱ በይፋ ከሚታወቀው የአየር መንገድ የቦርድ ሃላፊነታቸው ባሻገር ኮተቤ መስመር በሚገኘው እና «የአቢዮታዊ ዲሞክራሲ ማኔጅመንት ት/ቤት »ተብሎ በተከፈተው ተቋም ዋና ሃላፊ እና ለባለስልጣናት እንዲሁም ካድሬዎች መምህር ጭምር ናቸው። ከመለስ መታመም ወዲህ የህወሃት ካድሬ ላልሆኑ በአቶ አዲሱ እየተሰጠ ያለው ፖለቲካዊ ትምህርት ሳይሆን የበረከትን አቋም የሚያቀነቅን እና ህወሃትን የሚያጥላላ ቅስቀሳ ሆኖአል።
በሌላ በኩል ዓዜብ ከጎኗ ማሰለፍ የቻለችው ጄነራል ሰአረ መኮንን እና እንዲሁም በእርሳቸው የሚመራውን ጦር ነው ።በተጨማሪም ቴዎድሮስ ሃጎስ ይገኛሉ ።የዓዜብ አስገራሚ “አቋም” በሶፊያን አህመድም ላይ ተንጸባርቋል።”ለኤርትራ ካሳ “በሚል 2.1 ቢሊዮን ብር ለሻብያ በሚስጥር እንዲሰጥ በፊርማቸው ጭምር ከወሰኑት መካከል አቶ መለስ ዜናዊ፣ሙሉጌታ አለም ሰገድ ፣ሟቹ አቃቤ ህግ መስፍን እና ሶፊያን አህመድ ይገኙበታል።ዓዜብ ከዚህ በመነሳት “መለስን የማይክዱ ታማኝ “ካለቻቸው አንዱ ሶፊያን ናቸው ።
በተቃራኒው በነስብሃት በኩል ያለው የሃይል አሰላለፍ ለየት የሚያደርገው በነ በረከት ቂም የቋጠሩ “ተገፊ እና አድፋጭ”አመራሮችን እያቀፈ መቀጠሉ ነው ።ስዩም መስፍን ፣ሃይለኪሮስ ገሰሰ፣አባዲ ዘሞ ፣ቢተው በላይ . . . .. .በከፊል ይጠቀሳሉ ።
ስዩም ከስልጣን ተነስተው የቻይና አምባሳደር መሆናቸው ከተገለጸ በኋላ በውጭ ጉዳይ ቢሮ የተመደቡ ሰባት አባላት በሂልተን ሆቴል የምሳ ግብዣ አድርገውላቸው የነበረ ሲሆን በወቅቱም “ከስልጣን እንደምነሳ ምንም የማውቀው አልነበረም።አስቀድሜ ባውቅ ኖሮ ለእናንተም ብዙ ነገር አደርግ ነበር፤ አዝናለሁ። የበረከት ፣መለስ እና አዜብ ስራ ነው “ብለው ስዩም በቁጭት እንደነገሯቸው በስፍራው ከነበሩ ማወቅ ተችሏል። በሌላም በኩል ሃይለኪሮስ ለበረከት ከፍተኛ ቂም አላቸው ።ከቻይና ቀጥሎ የሱዳን አምባሳደር ተደርገው ነበር ።በኋላም በቃኝ ብለው ከፓርቲው በመውጣት የግል ንግድ ውስጥ ተሰማርተው ቆይተዋል ።አሁን ደግሞ ለበቀል ሲሉ የስብሃትን ቡድን ተቀላቅለዋል ።እንዲሁም በመለስ/በረከት የማይወደዱት እና ሃይለኪሮስን ተክተው በሱዳን አምባሳደር እንዲሆኑ የተመደቡት አባዲ ዘሞ ሌላው የፍልሚያው ተሳታፊ ናቸው ።ድፍረት የተሞላበት የተቃውሞ ሃሳብ በመሰንዘር እና መለስን ጭምር በመጋፈጥ የሚታወቁት ብቸኛው አባዲ ከዚህ በተጨማሪ በህወሃት ካሉ ባለስልጣናት ሙስና ውስጥ ካልገቡ ሁለት ሰዎች አንዱ ናቸው በማለት ምንጮች ይመሰክራሉ ።ሁለተኛው ደግሞ አባይ ወልዱ ናቸው ሲሉ ያክላሉ ። ከህወሃት የተባረሩት አምባሳደር አውአሎም ወልዱ ወንድም ናቸው አቶ አባይ ወልዱ ።ቢሆንም አባይ በጣም ደረቅ እና አምባገነናዊ ስብእናም እንዳላቸው ምንጮቹ አልሸሸጉም።
በዚሁ ወደ ዋናዎቹ ሁለት ርእሰ ጉዳዮች እናምራ፤ የበረከት እና ስብሃት ጎራዎች አንዱ የሆነው የልዩነት ፍጥጫ የአቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ እና የአቶ ደመቀ መኮንን ሹመት ይገኝበታል። ጠ/ሚ/ር ሃይለማርያምን በተመለከተ የተገኙ ተጨባጭ መረጃዎችን ለጊዜው እናቆያቸው ፤ትችት እና ወቀሳውንም እንዲሁ።ነገር ግን አቶ መለስ ማንኛውንም የፓርቲ አመራር ሲመለምሉ እና ሲያስመለምሉ የጀርባ ታሪኩን የሚያራምደውን አቋም . . . .መነሾ በማድረግ እንደሆነ የሚጠቁሙት ምንጮቹ አያይዘውም ፤ ተምሯል ፣ለሃገር እና ህዝብ ይሰራል. . .ወ.ዘ.ተ የሚለው በጭራሽ መስፈርት ሆኖ አይገባም ይላሉ ።የምልመላው ጥናት ቀንደኛ ተሳታፊ በረከት ሲሆኑ በመቀጠል የህወሃት አመራሮችም ይካፈላሉ ።ህወሃት ከበረሃ አንስቶ የተማረ አይወድም ፣ጠላቱ ነው ሲሉ የፓርቲው ምንጮች ያሰምሩበታል።
አቶ ሃይለማርያም ገና በጠዋት ለፓርቲው የተመለምሉበት የነመለስ-በረከት “መስፈርት”እንደተጠበቀ ሆኖ የመለመላቸው ተ/ማርቆስ ተ/ማርያም የተባለ እና አሁንም ድረስ ከጀርባ ሆኖ የደቡብ ክልል ባለስልጣናትን እንዲሁም መስተዳድሩን እያሽከረከረ ያለ ካድሬ ነው።ተ/ማርቆስ በደርግ ዘመን በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስ ምሩቅ የነበረ እና በአስተማሪነት የተመደበ ፣እንዲሁም ወደ አርባምንጭ ዩኒቨርሲቲ ተዛውሮ ሲሰራ ከቆየ በኋላ በ1982 አመተ ምህረት ገደማ የተባረረ ነው። ኢህአዴግ ወደ ስልጣን ሲመጣ በአቶ ቢተው በላይ አማካይነት ተመለሰ ።ከዚያም በይፋ ያልተገለጸ ቁልፍ ስልጣን እንዲጨብጥ ተደረገ ፤በአጭሩ ሃይለማርያም ዛሬ ለደረሱበት የስልጣን ደረጃ ተ/ማርቆስ ለአቶ መለስ ያደረሰው የስለላ-ጥናት ውጤት ሲሆን ከዚሁ ጎን የባለቤታቸው ወ/ሮ ሮማን አቋም በነ መለስ “መስፈርት “ አሟልተው በመገኘታቸው ጭምር ነው ። በተመሳሳይ የበረከት ምልምል የሆኑት ደመቀ መኮንን በኢሰፓ አባልነት ይታማሉ ።
እነ ስብሃት ራሳቸው ሲከተሉት እና ሲያስፈጽሙት የነበረ በመሆኑ የሃ/ማርያም እና የደመቀ ሹመት በበረከት በኩል መከወኑ እጅግ አበሳጭቶአቸዋል።የጠቅላይ ሚንስትሩ ቀጣይ “አቋም” ይቀየራል ? ወይስ ከአሁኑ ማንጸባረቅ በጀመሩት የመለስ/በረከት አጥፊ መስመር ጉዞ ይቀጥላሉ ?የሚለው በተለያዩ ወገኖች ድብልቅልቅ ስሜት ፈጥሮአል ፡፤ለምሳሌ በቅርቡ በሰጡት መግለጫ ላይ “ቀይ መስመር፣ሰላማዊ እና ህጋዊ ባርኔጣ” በማለት ንጹሃን የህሊና እስረኛ ጋዜጠኞችን እና በሰላማዊ መንገድ የፖለቲካ እንቅስቃሴ በማድረጋቸው ብቻ ለእስር የተዳረጉ ወገኖችን ያለ ሃፍረት በጅምላ ወንጅለዋል።በዚህ ሳያበቁ “ከሻብያ ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ መነጋገር እንፈልጋለን “ሲሉ የመለስ ፣በረከት እና ስብሃት… አቋም ቃል በቃል አንጸባርቀዋል።በረከት፣መለስን የተኩት የህወሃት ሊቀመንበር አባይ ወልዱ “ከተቃዋሚዎች ጋር ድርድር የማይታሰብ ነው “እያሉ በጥላቻ የታጠረ አቋማቸውን ሲገፉበት በሚስተዋልበት ተጨባጭ ሁኔታ ዛሬም ሻእቢያ እግር ስር በመደፋት ልምምጥ እና ልመናው መቀጠሉ ፣በአንጻሩ በአገር ውስጥ እና በውጭ ያሉ የተቃዋሚ ሃይሎች የድርድር ጥያቄ መገፋቱ እና አፈናው ተጠናክሮ መቀጠሉ ሲታይ ፦በእርግጥም ከሃ/ማርያም ጀርባ ያለው “ሹፌር”ለኢትዮጵያ እና ህዝቧ ጥቅም ምንም ግድ የሌለው እንደሆነ በቀላሉ ያሳያል ይላሉ እነዚሁ ወገኖች ።
ወደተከታዩ ነጥብ ስንሻገር በአስደንጋጭ ሁኔታ በሃገሪቱ ተጠናክሮ የቀጠለውን የሙስና ዘመቻ እናገኛለን ። በግልጽ እና በስፋት የሙስናውን መንደር ከተቀላቀሉት እና “ተከታይዋ ወይም ግልገሏ አዜብ”የሚል ቅጽል የወጣላቸው የበረከት ስምኦን ባለቤት አሰፉ በቀዳሚነት ትጠቀሳለች ።በረከት “አሲ”እያሉ በቁልምጫ የሚጠሯት አሰፉን ጨምሮ 6 የቤተሰብ አባላት በፓርቲው አባላት “ደቂ ማዘር” በሚል መጠሪያ ይታወቃሉ ።የታምራት ላይኔ ባለቤት የዚሁ ቤተሰብ አባል ስትሆን ከብአዴን የወጣችው (ከ6ቱ)እሷ ብቻ ናት ።የታደሰ ጥንቅሹ ባለቤት እንዲሁ የአሰፉ ቤተሰብ አካል ናት ።
የበረከት ባለቤት አሰፉ የመንግስት ስራ በመተው ወደ ከፍተኛ ንግድ መግባቷ ምንጮቹ አረጋግጠዋል። በአስመጭና ላኪ ንግድ የተሰማራችው አሰፉ በተለይ ወደ ዱባይ እና ሳኡዲ የተዘጋጁ የከብት ስጋ እና ቡና በመላክ እንዲሁም ከዱባይ እና ቻይና የሞባይል ቀፎዎችን የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን እና የተለያየ ይዘት ያላቸውን ጄነረተሮች በማስመጣት ንግዷን አጧጡፋለች ።አብዛኞቹ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው በጉምሩክ ሰትት ብለው እንደሚያልፉ ሲታወቅ የአዜብ ቀጥተኛ ድጋፍ እና ትእዛዝ እንዳለበት ተጠቁሞአል። አብዛኛውን ጊዜ ሁለቱም አብረው እንደሚያሳልፉ ምንጮቹ ገልጸዋል። በአስር ሚሊዮኖች የሚገመት ዶላር በመዛቅ ላይ የምትገኘው የበረከት ሚስት አሰፉ ለህወሃት ስር የሰደደ ጥላቻ እንዳላት የገለጹት እነዚህ ወገኖች በተደጋጋሚ ይህን አቋሟን በይፋ ስታንጸባርቅ መታየቷን አስታውቀዋል።
በሌላም በኩል አባይ ፀሃዬ ለበርካታ ባለሃብቶች በመቶ ሚሊዮን የሚቆጠር ብድር በመፍቀድ በቅርብ ስጋ ዘመዶቻቸው በኩል ሃብት እንዳካበቱ ታውቆአል ። ቀደም ሲል የነበራቸውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የቦርድ ሃላፊነት ተገን አድርገው የፈጸሙት ዘረፋ ነው።የሙስናው ተዋናዮች አምስት የአባይ ጸሃይዬ የቅርብ ዘመዶች ናቸው ። ባለሃብቶችን በማግባባት ደላላ ሆነው እየቀረቡ በተፈለገው መጠን የገንዘብ ብድር ማሰጠት እንደሚችሉ ከገለጹ በኋላ ያለምንም ውጣ ውረድ አባይ ጸሃዬ እንዲፈቅዱ ይደረጋል። ከብድሩ እስከ 50 ሚሊዮን ኮሚሽን ይወስዱ እንደነበር ተጠቁሞአል ።ተመሳሳይ ተግባር አቶ ግርማ ብሩ ይፈጽሙ እንደነበር ምንጮቹ አያይዘው ገልጸዋል። በተለይ “ራዲሰን”የተባለው እና ካዛንችስ አካባቢ የተገነባው ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ለግንባታ ተብሎ የተፈቀደለት 400 ሚሊዮን የብድር ገንዘብ እንደሆነ ሲረጋገጥ ከዚህ ገንዘብ ባለስልጣናቱ በኮሚሽን መልክ 150 ሚሊዮን ኪሳቸው እንደከተቱ ተረጋግጦአል። በጣም የሚገርመው ሸራተን ሆቴል እንኳን በአንድ መቶ ሰባ ሚሊዮን እንደ ተገነባ በይፋ እየተነገረ ለዚህኛው ሆቴል ግን ሁለት እጥፍ በብድር ስም ተፈቅዶ ሲመዘበር አቶ መለስ ጭምር ያውቁ ነበር ።በማያያዝም በባንክ ብድር የተሰራው ሸራተን ላለፉት 15 አመታት ብድሩን ያለመክፈሉና ባለፈው አመት ባንኩ የመሰረተው ክስ እንዲቆም መደረጉ አስገራሚ ሆኖአል ።ይህ እዳ ሳይከፈል በባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አቶ በረከት ስምኦን ትእዛዝ 942 ሚሊዮን ብር ለሼሁ ድርጅቶች መፈቀዱ እና በቅርቡ ደግሞ ታግዶአል መባሉ እንቆቅልሽ ከመሆኑም ባሻገር ምን ያክል የተበላሸ እና ከቁጥጥር ውጭ የሆነ ስርአት አልበኝነት በሃገሪቱ መንገሱ አመላካች ነው ተብሎአል ።በነገራችን ላይ አቶ በረከት ወደ ደቡብ አፍሪካ በሼሁ ቻርተር አውሮፕላኖች እንደሚመላለሱ ምንጮቹ አረጋግጠዋል።
በሌላም በኩል በቃሊቲ- አቃቂ በ7 ቢሊዮን የተቋቋመው ግዙፍ የብረት ማቅለጫ ፋብሪካ ሲጠቀስ ከጀርባ የአንበሳው ድርሻ ባለቤቶች ስዩም መስፍን እና አዲሱ ለገሰ ይገኛሉ ። ከዚህ በማስከተል በተለያዩ ባለስልጣናት የተገነቡ እና እየተገነቡ ያሉ የሙስና ውጤቶች እንመልክት ።በትግራይ መቀሌ ከተማ “ለአካባቢ የአየር ጥበቃ “በሚል ተተክሎ የነበረውን ደን በመጨፍጨፍ መሬቱን የተቀራመቱት ስብሃት ነጋ ፣ቴዎድሮስ ሃጎስ ፣ሃለቃ ጸጋይ፣ጎበዛይ ፣ኪሮስ ቢተው፣ተክለወይኒ፣… ዋና ዋናዎቹ ናቸው ።”አፓርታይድ መንደር”በሚል በነዋሪው በተሰየመው በዚህ ቦታ የተደረገው የአደባባይ የመሬት ቅርምት የተቃወመ የማዘጋጃቤት ሃላፊ ከስልጣን ተነስቶ እስካሁን የደረሰበትም አይታወቅም ።የተጠቀሱት የህወሃት ሹማምንት እጅግ ምርጥ እና ዘመናዊ ቪላ በጥድፊያ እያስገነቡ እንዳሉ ሲታወቅ ባለ ሁለት እና ሶስት ፎቅ የሆኑት ቪላዎች ከአስር ሚሊዮን ብር በላይ ለእያንዳንዱ ቤት ግንባታ መድበው ስራውን ወደ ማጠናቀቅ መድረሳቸውን ማረጋገጥ ተችሎአል ። በስምንት ሚሊዮን ብር የተገነባው የኪሮስ ቢተው ዘመናዊ ባለ ሁለት ቪላ ግንባታው በቅርቡ እንደተጠናቀቀ ታውቆአል።
ሽማግሌው ስብሃት በቀድሞው የአየር ሃይል ም/አዛዥ ጄነራል ሰለሞን እና በአሜሪካ በሲያትል እና በዋሽንግተን ዲሲ በሚኖሩ ስምንት የስብሃት የአጎት እና የአክስት ልጆች ስም በአክሲዮን ሽፋን የከፈቱት “ሉሲ አካዳሚ”ከሙስና የተገኘ ትልቅ የገቢ “ዘረፋ” ምንጭ ሆኖአል ።አካዳሚው በገርጂ እና ሳር ቤት – ባለ ስድስት ፎቅ ህንጻ አቅፎአል። የፌደራል ፖሊስ ም/ኮሚሽነር ሃሰን ሺፋ በቦሌ ያስገነቡት ባለሁለት ቤት ቪላ ተጠናቆ በየወሩ 25 ሺህ ብር መከራየት ጀምሮአል። የጄነራል ሳሞራ ቪላ ከለንደን ካፌ ፊት ለፊት ሲገኝ ከ1997 አመተ ምህረት ጀምሮ በየወሩ 30 ሺህ ብር ይከራያል። ባለ ሶስት ፎቅ የአባዱላ ቪላ ከሳሞራ ቪላ ቀጥሎ ሲገኝ ከሚያዚያ 97 አመተ ምህረት ጀምሮ በየወሩ 4 ሺህ ዶላር ለነጮች ይከራያል። ቦሌ ኤርፖርት መግቢያ ከኖክ ማደያ ጀርባ የብርሃነ ገ/ክርስቶስ እና የአዲስአለም ባሌማ ተወዳዳሪ ያልተገኘለት ባለሶስት ፎቅ ምርጥ ቪላዎች ይገኛሉ።በ1988 አመተ ምህረት የተገነቡት የሁለቱ ቪላ ሁለት የአሜሪካ ከፍተኛ መኮንኖች እያንዳንዳቸው በአራት አራት ሺህ ዶልር ተከራይተውታል። ከኢምፔሪያል ሆቴል አጠገብ የተገነባው እና በሰባት ሚሊዮን ብር ወጪ የተሰራው የተፈራ ዋልዋ ባለ ሦስት ፎቅ ቪላ በወር 30 ሺህ ብር መከራየት የጀመረው በ97 አመተ ምህረት መጨረሻ ነበር።የሙስናው ዝርዝር እና ስፋት በጣም ሰፊ ነው ።ወደ ውጭ እየሸሸ የሚገኘው የሃገር እና ህዝብ ሃብት ሳይካተት ማለት ነው ።
በዚህ አጋጣሚ ሳይጠቀስ የማይታለፈው በታይላንድ ባንኮክ የሚጸመው አሳዛኝ የሙስና ድራማ ነው። በርካታ የህወሃት ጄነራሎች እና ሌሎች ባለስልጣናት ከራሳቸው አልፈው የቅርብ ዘመዶቻቸውን እና ውሽሞቻቸውን ጭምር በከፍተኛ ወጭ ማሳከምን ተያይዘውታል። ከህወሃት ጀነራሎች መካከል ጄነራል ሰአረ እና ጀነራል ተስፋዬ በዋናነት ይጠቀሳሉ ።የሆስፒታሉ የህክምና ወጭ እንዲሁም የሚያርፉባቸው ባለ5 ኮከብ ሆቴሎች (ኢንተር ኮንቲኔታል እና ቻል ዲፖሎ )ናቸው ። በየሶስት ወሩ በሚቀርበው የክፍያ ዝርዝር ሪፖርት ከሰባት እስከ አንድ ሚሊዮን ዶላር እንደሚከፈል የቅርብ እማኞች ያስረዳሉ።
ከፍተኛ ክፍያ የተፈጸመው ለአባዱላ ገመዳ ልጅ ነው ።የሶስት አመቷ ህጻን ዲቦራ አባዱላ ስትወለድ የአንጀት ፣የሳምባ እና የአእምሮ ችግር ነበረባት ።ለሁለት አመት ተከታታይ ህክምና ተደረገላት ።የአባዱላ ባለቤት ራሄል ልጇን ያን ያክል ጊዜ ስታስታምም ባለአምስት ኮከብ ሆቴል ቪላ ተከራይታ ነበር ።የሁለት አመት የተከፈለው አጠቃላይ ወጪ 2.5 ሚሊዮን ዶላር እንደነበር ተረጋግጦአል። በአሁኑ ወቅት አባዱላ ሼሁን ተገን አድርገው ከበረከት ጎን ተሰልፈዋል።
በመጨረሻም አዜብ መስፍንን ከኤፈርት ለማስነሳት ሰፊ ዘመቻ በህወሃት አመራር ውስጥ መከፈቱን ለማወቅ ተችሎአል። የፓርቲው ሰዎች “የአዜብ ጸሃይ እየጠለቀች ነው “ብለዋል ።በቅርቡ አሜሪካ የቀሩት የአዜብ ምክትል ጌታቸው በላይ ለሽማግሌው ስብሃት ነጋ የቅርብ ዘመድ ሲሆኑ ከአቶ መለስ ጋር ደግሞ አብሮ አደግ ጎረቤቶች እንደነበሩ ታውቆአል። በኤፈርት የአዜብ ፈላጭ ቆራጭነት ያስመርራቸው እንደነበር ሲታወቅ ከነበራቸው የሚንስትርነት ስልጣን ወደታች መንሸራተታቸው ቅሬታ አሳድሮባቸው እንደቆየ የቅርብ ምንጮች ጠቁመዋል ። የሙስናው ጉዳይ እንዲጣራ አንድ ፖለቲከኛ ጥቆማ ስጥተዋል።

ከፖለቲካ ፍጥጫው በስተጀርባ (ከኢየሩሳሌም አርአያ)

http://minilik-salsawi.blogspot.com/2012/10/blog-post_3356.html?spref=fb


Irgalem (also spelled YrgalamYrgalem and Yrga Alem; alternate names include AbostoDalle) is a town in southern Ethiopia. Located 260 kilometers south of Addis Ababa and 40 kilometers south of Awasa in the Sidama Zone of the Southern Nations, Nationalities, and Peoples Region (or kilil), the town has a latitude and longitude of6°45′N 38°25′E / 6.75°N 38.417°E and an elevation of 1776 meters. It is the largest settlement in Dale woreda.
Postal service is provided by a main branch; electricity and telephone service are also available.

History

Irgalem was occupied by the Italians 1 December 1936 during their campaign against the remaining Ethiopian Army of Sidamo under Ras Desta Damtew. The town was capital of Sidamo Province until after the 1975 takeover by the Derge regime, when it was moved to Awassa.
Around 1957 there was no telephone landline connecting Irgalem; telecommunications were provided by a radio station. The next year, the town was one of 27 places in Ethiopia ranked as First Class Township. Installation of the landline between Irgalem and Addis Ababa was completed in late 1960. By that time a branch of the Ethiopian Electric Light and Power Authority had started operation at Irgalem.
The Mekane Yesus Church held its Eighth General Assembly at Irgalem in 1973. The Assembly passed a resolution requesting land reform in Ethiopia - a reform which was in fact put into action a couple of years later, as a result of the Ethiopian Revolution.

Demographics

Based on figures from the Central Statistical Agency of Ethiopia published in 2005, Iragalem has an estimated total population of 43,815 of whom 21,840 are men and 21,975 women. The 1994 national census reported this town had a total population of 24,183 of whom 12,092 were men and 12,091 were women.
http://en.goldenmap.com/Irgalem


Postgraduate Scholarship Grant Announcement of IDRC Project
College of Agriculture at Hawassa University (HwU) announces full scholarship for 12 female and 8 research grants for female and male MSc students in Human Nutrition, Soil Science and Plant Breeding as part of the collaborative project entitled: "Improving Human Nutrition in Ethiopia through Plant Breeding and Soil Management" with University of Saskatchewan, Canada. The MSc research work will be carried out on farmers' fields and Professors from Hawassa University and University of Saskatchewan jointly supervise the students. The project is financed by International Research Center (IDRC) and Canadian International Development Agency (CIDA) through Canadian International Food Security Research Fund (CIFSRF).
Deadline Date - Until October 7, 2012
Hawassa University, School of Graduate Studies
http://www.hu.edu.et/hu/index.php/85-hawassa-university/events/announcements/243-postgraduate-scholarship-grant-announcement-of-idrc-project


አዲስ አበባ፣ መስከረም 27፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) ዛሬ በመላው ሀገሪቱ የተካሄደው የኢትዮጵያ ኡላማዎች የፈትዋና ዳዕዋ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤቶች ምርጫ በሰላም ተጠናቀቀ።

በምርጫው በርካታ የእምነቱ ተከታዮች ከማለዳ  ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማና በተለያዩ የክልል ከተሞች በየምርጫ ጣቢያዎቹ በመገኘት፥ ይወክለናል ያሉትን እጩ ሀይማኖታዊ ስነ ሰርአቱ በሚያዘው መሰረት ሲመርጡ አርፍደዋል።

በየምርጫ ጣቢያው 25 እጩዎች የተጠቆሙ ሲሆን ፥ ከመካከላቸው አብላጫ ድጋፍ ያገኙ 20ዎቹ የምክር ቤት አባላት ሆነዋል። አብላጫውን ድጋፍ ያገኙትና በከፍተኛ ድምጽ የተመረጡት አምስቱ የምክር ቤቱ ስራ አስፈጻሚ በመሆን፤ የስራ ድርሻቸውን እዚያው በህዝቡ መካከል የስራ ድልድል በማድረግ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

የእምነቱ ተከታዮችም በምርጫው ንቁ ተሳታፊ በመሆን ፥ ዕምነቱ የሚፈቅደውንና የአመራር ስርዓቱን  አጠናክረው ያስቀጥላሉ የሚሏቸውን እጩዎች ነጻ፣ ፍትሃዊ፣ ዲሞክራሲያዊ እና አሳታፊ በሆነ መልኩ መርጠዋል።

በምርጫው ወቅት የምርጫ ካርድ ያልወሰዱ መራጮች በመመዝገብ የመረጡ ሲሆን ፥ የመራጩ ቁጥርም ከተጠበቀው በላይ እንደነበር ነው የምርጫ አስፈጻሚዎቹ የጠቆሙት።

በአዲስ አበባ የተለያዩ ክፍለ ከተሞችና በጅማ፣ በሃረር፣ በደሴ፣ በሻሸመኔ፣ በጎንደር እና በመቀሌ ሪፖርተሮቻችን በተዘዋወሩባቸው የምርጫ ጣቢያዎች ፥  ያነጋገሯቸው ድምጽ ሰጭዎች አፍራሽ ሃይሎች ያደርጉት የነበረው ቅስቀሳና በምርጫው ወቅት ያዩት ነገር የተለያየና ፍጹም ሰላማዊ እንደነበር ነው የገለጹት።

ተመራጮቹ የእስልምና ምክር ቤቶች አባላት የመረጣቸውን ህዝብ በቅንነት እና በታማኝነት እንዲያገለግሉ መራጮቹ የጠየቁ ሲሆን ፥ ተመራጮቹም የተጣለባቸውን ሃላፊነት ለመወጣት በአላህ ስም ቃል እንገባለን ማለታቸውን የተለያዩ የምርጫ ጣቢያዎችን የጎበኙ ባልደረቦቻችን ዘግበዋል።

በሌላ በኩል የዛሬው ምርጫ ፍጹም ሰላማዊ እና ዲሞክራሲያዊ እንዲሁም ውጤታማ እንደነበር ፥ የኢትዮጵያ ኡላማዎች ምክር ቤት ዋና ጸሃፊ ሸህ ኢዘዲን ሸህ አብዱልአዚዝ ተናግረዋል።

መንግስት የሙስሊሙ ተቋም ሰላማዊ ሆኖ እንዲቀጥል ላደረገው አስተዋጽኦ እና ፤ ሙስሊሙ ህብረተሰብ በምርጫው ወቅት ላሳየው ዲሞክራሲያዊ እና ሰላማዊ ተሳትፎ በምክር ቤቱ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።


የፓርቲው ልሳን ጋዜጣ ወደ መጽሔት ሊቀየር ነው
መንግስት በፕሬስ ላይ የሚያደርሰው አፈና እንዲቆም ያሳሰበው አንድነት ለዲሞክራሲና ለፍትህ ፓርቲ፤ ከህትመት የታገዱት የፓርቲው ልሳን “ፍኖተ ነፃነት” እና “ፍትህ“ ጋዜጣ ለህትመት እንዲበቁ ጠየቀ፡፡ የፓርቲው አመራሮች ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ፤ “ፍኖተ ነፃነት” ወደ ህትመት እንድትመለስና የፕሬስ አፈናው እንዲቆም ለጠ/ሚኒስትር ኃ/ማርያም ደሳለኝ፣ ለመንግስት ኮሙኒኬሽን ሚኒስትር ለአቶ በረከት ስምኦን እንዲሁም ለብሮድካስት እና ለብርሃንና ሰላም ማኔጂንግ ቦርድ ደብዳቤ ቢጽፉም ምላሽ አላገኘንም ብለዋል፡፡ ልሳን ጋዜጣው ፓርቲው አባላቶቹንና ደጋፊዎቹን የሚያነቃበትና ከህዝቡ ጋር የሚገናኝበት ድልድይ እንደሆነ ጠቁሞ፤ መንግስት ይሄን ድልድይ ነው የናደው ብሏል፡፡
መንግስት ጋዜጣውን የዘጋው ሆን ብሎ ፓርቲውን ለማፍረስና በመጪው የአዲስ አበባ ማሟያ ምርጫ እንዳይሳተፍ ለማድረግ ነው ሲልም አክሏል፡፡ የጋዜጣውን መታገድና የፕሬስ አፈናን በመቃወም በቅርቡ ሠላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርጉ የገለፁት የፓርቲው አመራሮች፤ ህጋዊ ሠውነት ስላለን የሠላማዊ ሠልፍ ጥያቄያችን ተቀባይነት ያገኛል ብለን ተስፋ እናደርጋለን፤ ፈቃዱን ካላገኘን ግን የራሳችንን የትግል መንገድ እንከተላለን ብለዋል፡፡ አንድነት ፓርቲ የታገደውን ጋዜጣ ለመተካት ሁለት አፋጣኝ እርምጃዎችን ለመውሰድ መወሰኑን ገልፀው፤ አንዱ ጋዜጣዋን ወደ መጽሔት በመቀየርና ከግል ማተሚያ ቤቶች ጋር በመነጋገር በቀጣዩ ሳምንት ለገበያ ማቅረብ ሲሆን ሁለተኛው ፓርቲው የራሱን  የማተሚያ ማሽን በመግዛት ጋዜጦችን እራሱ ለማተም ውሳኔ ላይ መድረሱንም አመልክቷል፡፡
http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=2946:%E1%8A%A0%E1%8A%95%E1%8B%B5%E1%8A%90%E1%89%B5-%E1%8D%93%E1%88%AD%E1%89%B2-%E1%8B%A8%E1%8D%95%E1%88%AC%E1%88%B5-%E1%8A%A0%E1%8D%88%E1%8A%93-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B2%E1%89%86%E1%88%9D-%E1%8C%A0%E1%8B%A8%E1%89%80&Itemid=20