POWr Social Media Icons

Monday, October 1, 2012

በኣደጋ ምክንያት በግንባራቸው ላይ የደረሰባቸውን ጉዳት ፎቶውን ኣጉልተው ይመልከቱ


55 ዓመት እድሜ ባለበት የሆኑት እና በአሁኑ ወቅት በማረሚያ ቤት ሆነው በስኳርና የደም ግፊት እየተሰቃዩ የሚገኙት ካላ ዱካሌ ላሚሶ፣ በነሐሴ 10/2004 .ም ከስራ ቦታቸው ታፍነው እስር ቤት የተወረወሩት፣ እስከዛሬ መስከረም 15/2005 .ም ድረስ ክስ ሳይመሰረትባቸው በማረሚያ ቤት የሚገኙት እና ለሲዳማ ሕዝብ መብት ሕይወታቸውን ሙሉ ሲታገሉ የኖሩ፣በግብርና ዘርፍ ማስተርሳቸውን በእንግሊዝ ሀገር በ1980ዎቹ ያገኙት አቶ ዱካሌ ላሚሶ መስከረም 14/2005 .ም ከጠዋቱ 4 ሰዓት ላይ በቴክኒክና ሞያ ት/ቤት አካባቢ ከወህኒ ቤት በፖሊስ ታጅበው ለደም ግፊት ህክምና ወደ ሃዋሳ ሬፈራል ሆስፒታል ሄደው ሲመለሱ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከተጫኑበት ባጃጅ ጭምር ታርጋ በሌለው መኪና ተገጭተው 4 ሜትር በሚረዝመው የአስፋልት ጠርዝ ገደል ውስጥ ጥለዋቸው ለጊዜው ተሰውረዋል፡፡በዚህም አደጋው በደረሰበት አካባቢ ህብረተሰብ ርብርብ ሕይወታቸው የተረፈ ሲሆን ታርጋ የሌለው ተሸከርካሪም ለጊዜው ተሰውሯል፡፡ 

ቀን፡15/01/2005
ቁጥር፡ቄለተድሮ01/2005
በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞከራሲዊ ሪፐብሊክ
ለጠቅላይ ሚኒስተር ጽ/ቤት
አዲስ አበባ፡-
ጉዳዩ፡-ስለ ፍትሕ መጓደል አስቸኳይ መፍትሔ እንዲሰጠን መጠየቅ ይሆናል::


ከላይ በመግቢያው ላይ እንደተጠቀሰው በኢ...ሪ ሕገ-መንግስት አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ ሕገ-መንግስት የህጎች የበላይ ህግ መሆኑን ይደነግጋል፡፡ ማንኛውም የመንግስት አካል ወይም ባለሥልጣን ውሳኔ ከዚህ ሕገ-መንግስት ጋር የሚቃረን ከሆኔ ተፈፃሚነት እንደማይኖራቸው ይገልፃል፡፡ (The Constitution is the supreme law of the land. Any law, customary practice or a decision of an organ of state or a public official that contravenes this Constitution shall be of no effect)፡፡
በተጨማሪም በዚህ ህገ-መንግስት በአንቀጽ 8 ንዑስ አንቀጽ 1 ላይ በኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የኢትዮጵያ ሉአላዊ ሥልጣን ባለቤቶች መሆናቸውን ይደነግጋል (All sovereign power resides in the nations, nationalities and peoples of Ethiopia)፡፡
ይሄ ሕገ-መንግስት ከደነገገው ውጪ የደቡብ ብሔሮች በሔረሰቦችና ሕዝቦች ከልል የሚገኙ አንዳንድ ከፍተኛ አመራሮች ለሕዝብ መልካም አስተዳደርና ልማት ማረጋገጥ ካለመቻላቸውም በላይ በሕዝብና በመንግስት መካከል ያለውን አመኔታ የሚሸረሽሩ ድርጊቶችን፣ ክራይ ሰብሳቢነትንና ምግባረ-ብልሹነትን ለረጅም ጊዜያት ከመፈፀማቸው ጋር አያይዞ ሕዝቡ አኝኮ ስለተፋቸው ይህንን ለማስለወጥ የህዝብ አገልጋይ የሚያስመስል ጭንብል በማጥለቅ ነገር ግን ህዝቡን የሚጎዱና የሚቀሰቅሱ አጀንዳዎችን አንስተው በሕዝቡ መካከል እንደነዙ ይታወቃል፡፡
ነገር ግን ያሰቡትና የዶለቱት ሁሉ በህዝብ ዘንድ ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱ ምክንያት ላያገግሙ በመንገዳገዳቸው ያንኑ ህዝብ መልሰው እንሸንገል በሚል አጀንዳ ህዝቡን እያመሱ፣ ሰራተኞች ተረጋግተውና ውጤታማ በሚያደርግ አኳኋን እንዳይሰሩና የታለመውን የልማት ግብ እንዳያሳኩ በማሸማቀቅ ማነቆ እየሆኑ ይገኛሉ፡፡ ከዚም በተጨማሪ በተመሳሳይም ሁኔታ ተማሪዎች ተረጋግተው በመማር ፋንታ የሚያስተምሯቸው ቤተሰቦቻቸው በተለያየ ተጨባጭ ባልሆነ ምክንያት እየታሰሩና እየተሰደዱ በመሆኑ ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ ቤታቸው ለመመለስ ተገደዋል፡፡በሌላ በኩል ደግሞ አርሶ አደሮችና ነጋዴዎች ልጆቻችሁን ከልል እንዳይጠይቁ ማድረግ አልቻላችሁምና በብራችሁ ህዝብን የመቀስቀስ ሥራ በመስራት ላይ ናችሁ በሚል ሰንካላ ምክንያት ንጹሐን ዜጎች የእንግልት ጽዋ እየቀመሱ ይገኛሉ፡፡
በተሣሣተ መንገድ የመንግስትን ታአማንነት ለማግኘት ስሉም የህዝብንና የመንግስትን ውስን ሀብት በከፍተኛ ደረጃ በማባከን ላይ ታች ሲሉና የሥልጣን እድሜ ሲያራዝሙ ቆይተዋል፤ ለመቆየትም እየዳዳቸው ይገኛል፡፡
እንደማነኛውም ኢትዮጵያዊ ብሔረሰቦች ህገ-መንግስቱ ለሲዳማ ህዝብ ካጎናፀፈለት መብቶች አንዱ ባህሉንና ትውፊቱን ማሳደግ ነው፡፡ በዚህ መነሻም የብሔሩን ዘመን መለወጫ ባህል የሆነውን የፍቼ-ጫምባላላ በዓል በአደባባይ (ጉዱማሌ) ለዘመናት ሲያከብር እስከዛሬ ደርሷል፡፡ በነቂስ የሚወጣው ህዝብም በዚህ በዓል በባህላዊ ጭፈራ(ቄጣላ) የሚወደውን አወድሶ፣ ያልተመቸውንና ህግጋትን (ሴራን) የተላለፈውን ግለሰብ ወይም ድርጅት ወቅሶና እንዲታረም አስጠንቅቆ በሰላም ወደቤቱ ይመለሳል፡፡
ከነሐሴ 8-9/2004 .ም የዋለው የፍቼ-ጫምባላላ በዓልም በሲዳማ ዞን አስተዳደር ጋባዥነት በዓሉን አከብሮ በዋለበት ወቅት በዲሞክራሲያዊና በጨዋ ሁኔታ ከማክበሩም በተጨማሪ እንደተለመደው ባልተመቸውና ህገ-መንግስታዊ መብታችን ነክቶብናል፣ ፍላጎታችንን አልጠበቀም፣ የልብ ምታችንን አላዳመጠም፣ በሙስናና ምግባረ-ብልሹነት አዋርዶናል ያለውን ወቅሶ መንግስትን ግን አሞጋግሶ ወደየቀዬው በሰላም ተመልሷል፡፡ ይህ ሰላማዊነት ደግሞ የሲዳማ ባህልም ስለሆነ በነቂስ የወጣው ህዝብ በዓሉን በሰላም አከብሮ ተመልሷል፡፡ ይሁንና እነዚህ የመልካም አስተዳደር ሽታ በአጠገባቸው ያላለፈባቸው መንግስትንና ህዝቡን የሚያጣላ ሥራ የሚሠሩ አመራሮች በለመዱት የአምባገነትና የአፈና ባህርያቸው በመጠቀም ተንኮል በወለደው (አንድ ባለሥልጣን ተሰደበ የሚል) የድርሰት ክስ በማዘጋጀት በሰላማዊ መንገድ መደበኛ ኑሮውን አየመራ ይህች አገር ለተያያዘችው ልማትና እድገት የበኩሉን አስተዋጽኦ ለማበርከት ደፋ ቀና የሚለውን የሲዳማ ህዝብ በፍቼ-ጫምባላላ በዓል ላይ ተገኝታችሁ የክልሉን ርዕሰ መስተዳደር የሚነካ(የሚወቅስ) ሐሳብ አንፀበርቃችኋል በሚል ሰንካላ ምከንያት ህዝቡን በማሸበር፣የገጠርና የከተማ ነዋሪዎችን ሁሉም ይታሠራል የሚል ሽብር በመንዛት ህዝቡ መንግሥት ከተያያዘው የልማት አንቅስቃሴ ጎዳና ውጪ የማድረግ ሥራ እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
ከማሸበርም አልፈው የሲዳማ ብሔር አባላትን ከሽማግለዎች፣ ከተማሪዎች፣ ከነጋደዎች ከመንግሥት እና ከግል ድርጅት መሥሪያ ቤት ሰራተኞች ብዙ ሰዎችን ኢ-ሕገመንግስታዊ በሆነ መልኩ በሁሉም ወረዳዎችና በሐዋሳ ከተማ በእስር ቤት በማጎር ከመደበኛ ሥራዎቻቸው በማስተጓጎል በዚህ ኑሮ ውድነት ቤተሰቦቻቸውን የመበተን አደጋ ላይ ጥለዋል፡፡ ከዚህም ባሻገር ህዝቡን በከፍተኛ ምሬት ውስጥ የመክተት ሥራ እየሠሩ በመቆየታቸው የሀገር ሽማግሌዎች ከዚህ እኩይ ተግባራቸው እንድመለሱ እና ታሣሪዎቹን እንድፈቱ ብጠይቋቸውም “እኔን 18 ሚሊዮን ህዝብ የማስተዳድረውን ንጉስ ስሜን በክፉ ያነሱትን እበቀላቸዋለሁ፣ ገና አደኀያቸዋለሁ፣ በእግሬ ሥር እስኪንበረከኩ ድረስ በወኂን ቤት አወርዳቸዋለሁ” እና ወ..ተ ብሎ እሰከመዛት የለየላቸውና ፍፁም አምባገነን ሆነው በአሁኑ ሰዓት ያለክስ ታሰረው በበሽታና እንግልት እየተሰቃዩ የሚገኙት ምሁራን ወንድሞቻችን በርካታ ናቸው፡፡
እነዚህ ወገኖች ወደ ፍርድ ቤት ቀርበው ከሚነገርባቸው የክስ ሁኔታ እና ክስ የተመሰረተባቸው ርዕስ ለመረዳት እንደሚቻለው ሕገ-መንግስቱን በኃይል ለመናድ፣ መንግስትን በኃይል ለመገልበጥ፣ ሕዝብን በመንግስት ላይ በማነሳሳት ወዘተ በሚሉ ሐሰተኛ የክስ ርዕሶች የተከሰሱ ቢሆንም በወንጀል እንጂ በፖለቲካ አመለካከታቸው እንዳልታሰሩ በተለያዩ ሚዲያዎች ይገልፃሉ፡፡ ነገር ግን እኚህ ዜጎች የፖለቲካ እስረኞች መሆናቸው ከላይ የገለፅነውን የክሱ ርዕስ መረዳት ቀላል ነው፡፡
ዘመኑ ሲዳማ በሙሉ የሚታሰርበት ነው እስኪባል ድረስ ፍርድ ቤት በነፃ ያሰናበታቸው ግለሰቦች ሁሉ እንደገና እየታደኑ ወደ እስር ቤት እየታጎሩ ይገኛሉ፡፡ የነዚህን ሰዎች ስም ዝርዝር በቀጥታ መንግስት ከማረሚያ ቤቶችና ፍርድ ቤቶች ማግኘት የሚችል ሲሆን ፍርድ ቤቶችም የባለስልጣናት ተላላኪዎች በመሆን በስልክ ትዕዛዝ ተጨማሪ ቀጠሮዎች እንዲሰጡ በማድረግና በግልፅበችሎት ላይ በስልክ እየተነጋገሩ የሚወስኑ ሆነዋል፡፡
እንግዲህ ሕዝብን የማፈን ስራ እስከመቼ እንደሚዘልቅ ማወቅ አልቻልንም፡፡ ምን ያህልና ለምን ያህል ጊዜ ማስተንፈስ እንደሚችልም አላወቅንም፡፡ ዜጎችን በስልክ ትዕዛዝ ብቻ እንደ እንሰሳት አፍኖ ማሰር እስከመቼ እንደሆነም አልገባንም፡፡ ማሰርና መግደል መፍትሄ የሚያመጣ ቢሆን ደርግ ባልወደቀ ነበርና ይህ መንግስት የሚያስተውልና ከታሪክ የሚማር ከሆነ ይህንን ማወቅ የሚሳነው አይመስለንም፡፡ ሕዝቡ መሰረታዊ የሚባሉ ሕገ-መንግስታዊ ጥያቄዎቹን ባነሳ ቁጥር መገደሉ፣ መታሰሩ፣ መሰደዱ እና መታፈኑ ከኢህአዴግ ምን ያህል እየራቀ መሆኑን ማወቅ ለማንም አያዳግትም፡፡
ስለሆነም የተሻለ የህገ-መንግስት መተግበር በምንጠብቅበት በዚህ አዲስ ዓመትና አመራር የሚከተሉት ቁልፍ ጉዳዮች ለዚህ ጭቁን ሕዝብ ምላሽ እንዲሰጠው በትህትና እንጠይቃለን፡፡
  1. በቅድሚያ ያለ ክስ እና ድርሰታዊ በሆነና ሆን ተብሎ በተቀነባበረ ክስ ታፍነው የታሰሩ የፖለቲካ እስረኛ ዜጎቻችን ቁልፍ የምንላቸው ምሁራንና የለውጥ ተስፋዎቻችን ናቸውና ያለምንም ቅድመ-ሁኔታ ከእስር እንዲፈቱልን፣
  2. የሲዳማን ሕዝብ "እሾህን በእሾህ" እንዲሉ በራሳችን እጅግ ደካማ ሰው እንዲጠቃ የሚሰራው ሴራ እንዲመክን እንዲደረግ፣()በራሱ የቆመ፣ ቆራጥ የልማት፣ የዴሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደርና የትምህርት ዝግጅት ያለው ለራሱ ሳይሆን ለሕዝቡ የሚሰራ በዚህም የሲዳማን ሕዝብና መንግስትን የሚያቀራርብ አመራር እንዲተካልን፣
  3. የሲዳማ ብሔር በኢትዮጵያ ታላላቅ (በቁጥር) ከሚባሉ 5 ብሔሮች ውስጥ አንዱ ሆኖ ሳለ በፖለቲካው፣ ኢኮኖሚው፣ ማህበራዊና ቁሳዊ የመጨረሻ ሆኖ የሚኖርበት ዘመን እንዲያበቃና ራሱን ችሎ በክልል ደረጃ እንዲዋቀር፣ በዚህም ከሌሎች ብሔሮችና ብሔረሰቦች ጋር የበለጠ ተከባብሮ፣ በራሱ ጉዳይ ላይ ራሱ እየወሰነ፣ መንግስትን በልማትና መልካም አስተዳደር ረገድ እያገዘ እንዲኖር እንዲደረግ፣ በዚህም በደቡብ ክልል ውስጥ እንደዚህ ዓይነት ነፃነት ሲጠይቅ የመጀመሪያው ብሔር እንዳልሆነና ከዚህ ቀደም በሌሎች ብሔሮች ላይ ተፈፃሚ የተደረገው ሕገ-መንግስት ወደ ሲዳማ ብሔር ድንበርም ዘልቆ እንዲገባ እንዲደረግ፤ ለምሳሌም ወጋጎዳ (ሰሜን ኦሞ) ዞን የነበረው አሁን 4 ዞኖች የሆነው (ወላይታ፣ ዳውሮ፣ ጋሞ እና ጎፋ)፣ ስልጤና ጉራጌ፣ አዲሱ የሰገን ሕዝቦች ዞን፣ ከንባታ ጠንባሮና ሀዲያ ወዘተ.
በመጨረሻም መንግስት በተለይም ጽ/ቤታችሁ ከላይ በግልፅ ያስቀመጥነውን ጥያቄያችንን እንዲመልስልን በመጠየቅ ጉዳዩን በአንክሮ በመመልከት ምላሽ በአጭር ጊዜ እንደሚሰጠን ተስፋ እናደርጋለን።()
ከሰላምታ ጋር
ህገ-መንግስታችን ይከበር!
ግልባጭ፡-
  • ለፌዴሬሽን ም/ቤት
  • ለኢህአዴግ ጽ/ቤት
  • ለኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን
  • ለሁሉም በኢትዮጵያ የሚገኙ ዲፕሎማቲክ ሚሽኖች
አዲስ አበባ፡-

የማመልከቻውን ሙሉ ቃል


አዲስ አበባ፣ መስከረም 20፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) በ2005 ዓ.ም በሁሉም የሀገሪቱ ክልሎችና በሁለቱ የከተማ መስተዳድሮች የሚካሄደው ምርጫ ነፃ ሰላማዊ ዴሞክራሲያዊ ለማድረግ ፥የፍትህ አካላት ቅንጅታዊ ስራ ተጠየቀ።

የቦርዱ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና ለኦሮሚያ ክልል የፍትህ አካላት የተዘጋጀውን ስልጠናውን ሲከፍቱ እንዳስገነዘቡት ፥ በአካባቢ ምርጫ በሚወዳደሩ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል ሊከሰት የሚችለውን ቅሬታ ፍትሀዊ መፍትሔ መስጠት እንዲቻል ፥ ተሻሽሎ የወጣውን የምርጫ ደንብና ህግ ፥ የፍትህ አካላት ጠንቅቀው ማወቅ ይጠበቅባቸዋል።

ባለፉት ምርጫዎች እየተሻሻለ የመጣውን ዴሞክራሲያዊ ምርጫ በያዝነው አመትም ይበልጥ እንከን የለሽ ለማድረግ በየደረጃው የሚገኙ የፍትህ አካላት በቦርዱ የተዘጋጀውን የምርጫ ሕግና ደንብ ተግባራዊ ማድረጋቸው የጎላ ድርሻ ይኖረዋል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

ሕገ-መንግስታዊ መብቶቻችን እንዲከበሩና በተግባር እንዲውሉ ስንጮህ ኖረን ዛሬ ሰሚ ጆሮ በማግኝታችን ጥሪው የሚወደስ ነው፡፡  ይህም ሆኖ   ጅማሮው እንዳይደናቀፍ የዴሞክራሲ ጠላቶች  ጆሮ ይደፈን በሚል መፈክር ሁሉን ዘግቶ ወደ እንቅስቃሴ መሸጋገር ግን የተሟላ መፍትሔ ነው ብዬ አላምንም፡፡ኢህአዴግም ሆነ ተቃዋሚዎችን ጨምሮ መላው ሕብረተሰብ  በችግሮቻችንን መንስኤዎቻቸውንና መፍትሄዎቹ ላይ ዘለቅ ብለን፣ ከተቻለ በጋራ ካልሆነም የተገኘውን መገናኛ ብዙሃን ተጠቅመን መፈተሽ አለብን ብዬ አምናለሁ፡፡ በችግሮቹ ላይ መግባባት ሳይፈጠር በመፍትሔዎቹ ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ መጣር መፍትሔውን ግማሽ ልጩ ግማሽ ጎፈሬ ከመሆን አያድነውም፡፡የዛሬ ሃያ አንድ ዓመት አካባቢ ተከታታይ ሽንፈቱን ተከትሎ ጥርጣሬ፣ ስጋትና ፍርሃት የገባውን የደርግ ሽለላና ፉከራ አሸንፎ ኢህአዴግ ስልጣንን ከደርግ እጅ ሲረከብ የተገጠመ የማስታውሰው ስነ-ቃል አስታውሳለሁ፡፡ “ኢህአዴጎ ኢህአዴጎ፤ ገና ትበላለህ ወተትና እርጎ፡፡” መባሉን፤
በወቅቱ ኢህአዴግ ንዑስ ከበርቴ ከሚለው ከተሜው ይመንጭ  ወይም ከአርሶ አደሩ እርግጠኛ  አይደለሁም፡፡  ስነ-ቃሉ ተረት ተረት ሊመስል ይችላል፡፡ እውነታው ግን ወዲህ ይመስለኛል፡፡ “እናንተስ ማን ትመስሉ፡፡” የሚል መሰረታዊ ጥያቄን ያቀፈ መሆኑ ግን ጥርጥር የለውም፡፡
በሕዝብ  ጥቅም ስም ተደራጅተናል፣ አምላክ ቀብቶናል፣ በወታደሩ ተወክለናል በማለት ሕዝብን ነጻነቱን ለይስሙላ አረጋግጠው ሚሊኒክ ቤተ መንግስት ከገቡ በኋላ እራሳቸውን ተግተው የሚያገለግሉ በርካታ አምባገነኖችንን መታዘቡ  የፈጠረበት ስጋት እንደሆነ  አምናለሁ፡
ከሃያ አንድ ዓመት በኋላ ጥርጣሬው ጥርጣሬ ሆኖ ቀረ ወይስ የተጠረጠረው ደረሰ ለሚለው ጥያቄ መልስ ለመስጠት ወቅታዊ ነው፡፡  እውነቱና እውነቱን ብቻ መዳሰስ አስፈላጊም ግድም የሚል ነው፡፡ በመረጃና በእውነታ ላይ ሳይመሰረቱ መተቸት ሮሮ ከመሆን አይዘልቅም፡፡ መፍትሔም አያመጣም፡፡
ሃያ አንድ ዓመት ለፖለቲካዊና ኢኮኖሚዊ ለውጥ ታጥቆ ለተነሳ ቀላል የሚባል ጊዜ አይደለም፡፡ በሃያ ዓመታት ውስጥ ስር ነቀል ለውጥ  በማካሄድ  ጥቂት  የማይባሉ የአፍሪካም ሆነ የኤስያና የካረቢያን ሃገሮች በኢህአዴግ የሚጠቀሱትን ጨምሮ መልካም አስተዳደርና ዴሞክራሲን ማስፈን ችለዋል፡፡ ኢኮኖሚያዊ እድገትንና ልማትንም ማረጋገጥ ችለዋል፡፡ ሃያ አንድ ዓመት በትውልድ ሚዛን ሲለካ ሙሉ ሰውነትንና ሕይወትን ለመምራት ብቁ  መሆን የሚቻልበት ጊዜ ነው፡፡  ከዚህ አኳያ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ስንመዝነው ከአስራ ሰባት ዓመት በፊት ተወልዶ በጫካ ትጥቅ ትግል ጎልብቶ  ሃያ አንድ ዓመት በስልጣን መንበር ላይ ቢቆይም ዛሬም እልህ አስጨራሽ ሰላማዊ ትግል የሚካሄድበትና፣ አዝጋሚ ልማታዊነት የሚሰበክበት ዘመን ላይ እንገኛለን፡፡ የብዝሃነትና የመድብለ ፓርቲ መገለጫ የሆኑት የተለየዩ ሃሳቦችን በነጻ የማንሸራሸር ጥያቄዎችን ለመመለስ   የሕትመትና የኤሌክትሮኒክስ መገናኛ ብዙሃን አይነተኛ ሚና አላቸው፡፡ በኢትዮጽያ ውስጥ የመገናኛ ብዙሃን አጠቃቀም ሕገ-መንግስታዊ እውቅናና ጥበቃ ከማግኘትም በላይ ለአፈጻጸሙ ሕጎች የተደነገጉ ቢሆንም ዛሬም አፈጻጸሙ ከእቅድና ከሕግጋት አልፎ ወደ ተግባር መለወጥ አልተቻለም፡፡ በመገናኛ ብዙሃን አማካኝነት አማራጭ የማዳመጥ /የማቅረብ /  ሕዝባዊ መብት መሆኑ ላይ ብዥታ ባይኖርም፣ ተጠቃሚው ሕዝብ በጥርጣሬ ስለሚታይና የመገናኛ ብዙሃን ባለቤትነት በሕዝብ ከሚታመነው ከመንግስት ውጭ የማንም እንዲሆን አልተፈለገም፣ አልተፈቀደም፡፡
መብቶች ዛሬም በመታመንና ባለመታመን መካከል እየተመዘኑና እየተቆጠቡ የሚሰጡ ናቸው፡፡ ሕዝብ መብቱን መጠቀም ይችላል ወይም አይችልም የሚሉ መቆጣጠርያ ተቀጽላዎች ተበጅተውለታል፡፡ ሕገ-መንግስቱ የሰብአዊ፣ የዴሞክራሲያዊና የነጻ አስተሳሰብ መገለጫዎችን በተሟላ መልኩ ቢያጎናጽፍም መብቶቻችንን በተግባር ለመተርጎም እንዳይቻል በየእለቱ በሚጸድቁ ጎታች መመርያዎችና ደንቦች አይነተኛ ደንቃራዎች ሆነዋል፡፡  ያለፉት ሃያ አንድ ዓመታት ከዴሞክራሲና ከመልካም አስተዳደር አኳያ አድሮ ጥሬ ሆነው ቢያልፉም ሰሞኑን ከኢህአዴግ በኩል ተከታታይነት ያላቸው ጥሪዎችና ጅማሮዎችን እየሰማንና እያያን ነው፡፡ እሰየው ያስብላል እንበል ይሆን? ኢዴፓ  ለረጅም ጊዜ የታገለለት የጠቅላይ ሚኒስትሩን የስራ ዘመን የመገደብ ጉዳይ ጆሮ  አግኝቷል፡፡ ኢዴፓ ላለፉት አስራ አምስት አመት ሲጮህለት የኖረው የጠቅላይ ሚኒስትሩን የስልጣን ዘመን የመገደብ አስፈላጊነት፤ ሕገ-መንግስታዊ እውቅና እንዲያገኝ ማድረግ ውጤቱ የማያዳግም መተማመኛ ስለሚሆን በቅጡ ሊታሰብብት ይገባል፡፡
ሕገ-መንግስታዊ መብቶቻችን እንዲከበሩና በተግባር እንዲውሉ ስንጮህ ኖረን ዛሬ ሰሚ ጆሮ በማግኝታችን ጥሪው የሚወደስ ነው፡፡  ይህም ሆኖ   ጅማሮው እንዳይደናቀፍ የዴሞክራሲ ጠላቶች  ጆሮ ይደፈን በሚል መፈክር ሁሉን ዘግቶ ወደ እንቅስቃሴ መሸጋገር ግን የተሟላ መፍትሔ ነው ብዬ አላምንም፡፡ ኢህአዴግም ሆነ ተቃዋሚዎችን ጨምሮ መላው ሕብረተሰብ  በችግሮቻችንን መንስኤዎቻቸውንና መፍትሄዎቹ ላይ ዘለቅ ብለን፣ ከተቻለ በጋራ ካልሆነም የተገኘውን መገናኛ ብዙሃን ተጠቅመን መፈተሽ አለብን ብዬ አምናለሁ፡፡ በችግሮቹ ላይ መግባባት ሳይፈጠር በመፍትሔዎቹ ላይ ስምምነት ላይ ለመድረስ መጣር መፍትሔውን ግማሽ ልጩ ግማሽ ጎፈሬ ከመሆን አያድነውም፡፡   በመልካም አስተዳደር አማካኝነት ፍትሕና ርትእ የማግኘት፣ ያለአድሎ የመዳኘት፣ ያለመገለልን አስመልክቶ በመብትና ነጻነት ዙርያ የሚነሱ እንደ መደራጀት፣ መሰብሰብ፣ ሃሳብን የመግለጽ፣ የመቃወም፣  የማምለክ፣ በሰላም የመኖር፣  በኢኮኖሚያዊ መብቶች  ዙርያ ሃብትን ያለገደብ የማፍራት፣ የመሸጥ፣ የመለወጥ፣በስጦታ የማስተላለፍ፣ የማውረስና ሌሎችም መሰረታዊ ጥያቄዎች የዴሞክራሲ ሀ ሁ መሆናቸውን በሁላችንም ዘንድ በቅጡ መግባባት አለ፡፡ በዚህም ምክንያት እነዚህን  ሁለንተናዊ መብቶች መሰረት ያላደረገ ዴሞክራሲ ሌላ ነገር እንጂ  ዴሞክራሲ ሊሆን አይችልም፡፡
ከላይ የተዘረዘሩትና በሂደት እያደጉ የመጡትን ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ መብቶች ባለቤት የሌላቸውና በተፈጥሮ የተሰጡ ጸጋዎች ናቸው ከሚለው  ጽንሰ ሃሳብ በመነሳት ፍልስፍናቸውን ከሚያራምዱት ዓለም አቀፍ ምሁራን ጀምሮ፣ መብቶች ከሕግ ማዕቀፍና ከስርዓት  ብቻ የሚመነጩ የስምምነት ውጤቶች ናቸው የሚሉትን  በርካቶችን  አካትቶ፣ መብት የግለሰብ ሳይሆን ከቡድንና ከማህበረስብ ወይም ከብሄሮች ማህበራዊ  ግንኙነት ነው የሚሉትን ኮሚኒስቶች ይዞ የዘለቀው  የፍልስፋና ግብግብ ዛሬም ነባራዊ ግጭቱን ይዞ እንደቀጠለ ነው፡፡
ፍልስፍናዊ እሰጣገባው ከላይ የቀረበውን ቢመስልም በሁለንተናዊ መልኩና ቅርጹ የሕግ ውጤት የሆነው ናዚዝም ጥሎልን ያለፈው እጅግ አሰቃቂና አሳፋሪ፤ ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት መብትን፣ ነጻነትን፣ እኩልነትን ከሞራልና ከተፈጥሮ ዘለግ ካለም ከሃይማኖት ለማፋታት ያለሙ በርካታ ፍልስፍናዎችን በከባዱ ጥያቄ ውስጥ ጥሎ አልፎአል፡፡ በዚህም ምክንያት የመብት፣ የእኩልነትና የነጻነት ጥያቄዎች  መነሻ ፍልስፋና  ሃይማኖታዊም ይሁን ሞራላዊ አሊያም ሕጋዊ  ቢያንስ ቢያንስ ግን የሰው ልጆችን እኩልነት ከማክበርና ከማስከበር አኳያ ሚዛናዊነት ከጎደለው ከጅምሩ ትርጉም የሌለውና አደገኛ ዝንባሌ ከመሆን እንደማይድን ከናዚዝም በተጨማሪ በርካታ የታሪክ ሂደቶች  አረጋግጠዋል፡፡
በዘመናችን መንግስታት ዘንድ ሰብአዊና ተፈጥሮአዊ መብቶች  በተለየ ፍልስፍናዎች እየታገዘ  ማዕቀብ የሚጣልባቸው በመንግስታት ሲታመንበትም ሊነጠቁ፣ በተመሳሳይና ተቀራራቢ ሕጎች ሊተኩ የሚችሉ  ወይም ተቆንጥረው ሊሰጡና ከቶውንም ሊነፈጉም የሚችሉ ሆነዋል፡፡ ከዚህ አኳያም ሕዝቦች  ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን ለመነጠቅ  መጠርጠራቸውና  አለመታመናቸው በቂ መነሻ ምክንያት ነው፡፡
ለዚህ የሚመጥኑና የሚያግዙ ኢኮኖሚያዊ፣ ፖለቲካዎና ማህበራዊ በላኤ ሰቦችን (bogeyman) የሃያኛውና የሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመናት በበቂ መጠን መቀፍቀፍ ችለዋል፡፡ እንደ አለም አቀፍ ሽብርተኝነት፣ ብሔራዊ ጥቅም (national Interest) የመሳሰሉት የተጋነኑ ማስፈራሪያዎች ለአምባገነን መንግስታት መብትን ለማፈንና በጥቅሉ ለመንፈግ መነሻ ሆነው እያገለገሉ ነው፡፡ ታቅደውና ተቀነባብረው የሚገባባቸው ጦርነቶች፣ በነዳጅና በከበሩ ማዕድናት ፍለጋ ስም የሚቀነባበሩ ግጭቶች፣ ልማትን ታከው ነባር ነዋሪዎች  የሚያፈናቅሉ የመሬት ወረራዎች፣ አገር በቀል ሕዝባዊ ድጋፍ መሰረት ያደረጉ እምቢተኛ ንቅናቄዎችን፣ መንግስታትንና ስርአቶችን ለማስፈራራትና ለማሸማቀቅ የሚመሰረቱ ዓለም አቀፍ ተቋማት ለአፈናውና ለረገጣው አይነተኛ መሳሪያ ሆነው ቀጥለዋል፡፡ በሃያኛው ክፍለ ዘመን ያቆጠቆጠው አለም አቀፍ ኢምፔርያሊዝም የወለዳቸው የቀድሞው ኮንጎ መሪን ሞቡቶ ሴሴኮን፣ “ምንም ያህል ብትሮጥ ከጥይት አታመልጥም” በሚል መፈክር  የተቃወሙትን የፍትሕ አካላትና አስፈጻሚዎችን ለቅሞ የበላውን ኢዲ አሚንን አይነት አለም አቀፋዊ ሶሻሊዝም የወለዳቸው አምባገነኖች “እያንዳንዱ የፈጸምኩት ድርጊት ለሃገሬ ስል ነው” በሚለው መፈክር ከአንድ ሚሊዮን በላይ ዜጎቹን እያጋዘ የገደለውን የካምቦዲያው ፖል ፖት ሃሳብ “ከጦር መሳርያ በላይ አደገኛ ነው፡፡ ጦር መሳርያ የከለከልናቸውን ጠላቶቻችንን ሃሳብ እንዲኖራቸው አንፈቅድም፡፡”በማለት በመቶ ሚሊየን የሚቆጠሩ የቀድሞዋን ሶቪየት ሕብረት ዜጎችን እስረኞቹና ምርኮኞቹ ያደረገውን ጆሴፍ ስታሊን አለማችን አስተናግዳለች፡፡
የዘመናችን ኢ-ሊብራሎች መሪዎች (illibrals) ደግሞ ሕዝቦች ምርጫ መኖሩንና ዴሞክራሲ በሕግ መደንገጉን ካወቁ በቂያቸው ነው የሚሉ ናቸው፡፡ መራጩ ሕዝብ ስለምርጫና ስለመብቱ ከማወቁ ውጭ አንዳችም የሚወስነው ነገር የለም፡፡ ምርጫን  አስመልክቶ ውጤቱን የሚወስነው  ቆጠራውን የሚያደርገው  ሃይል ነው፡፡ የመብት ጥያቄ ከሆነ ደግሞ ሽብርተኝነትን የመሳሰሉ “በላኤ ሰቦችን” መደርደር ነው፡፡  መብታችንን ለመግፈፍና መጠቀሚያ ለማድረግ ያሰፈሰፈው ሃይል ቁጥር ጨምሯል፡፡ ሕገ-መንግስቱ ላይ ብናሰፍርልህም አጠቃቀሙ ግር ስለሚልህ ለአጠቃቀሙ መመርያ ያስፈልግሃል፡፡ ስለዚህ መብትህን መጠቀም እስክትችልና የጋራ ጠላቶቻችን እስኪጠፉ ድረስ መብቶቻችን በቁጠባና በገደብ ሆነዋል፡፡ የዘወትር ጥሪውም ይሄው ነው፡፡
በተለያየ ምክንያት የሚቀፈቀፉ  የገዢዎች ጥቅምን ያማከሉ ጎታችና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎች ከያሉበት  ተቀድተው  ከአምባገነንነትና ከስልጣን ጥም ጋር ተዳቅለው በማደግ ላይ ወዳሉ አገራት ሲዛመቱ መላ ቅጥ የጠፋው፣ ልክና መስፈርት የሌለው አፈናና የመብት ረገጣን አርግዘው እንደሚወለዱ በተለይ እኛ አፍሪካውያን ቋሚ የታሪክ ታዛቢዎች ነን፡፡ የዚምባቡዌውን “የእድሜ ልክ” ገዢ ሮበርት ሙጋቤን፣ የግብጹና የቱኒዚያውን ዘመናዊ አምባገነኖችና  ሌሎቹንም እልፍ አእላፍ የአፍሪካ መሪዎች መጥቀስ ይቻላል፡፡   ወደ ሃገራችን ተጨባጭ ሁኔታ ስንመጣ፣ የዴሞክራሲያና የሰብአዊ መብቶች ጥያቄዎች ከ1987 ዓ. ም. ጀምሮ ሕገ-መንግስቱ ላይ በሰፈሩበት ልክ ቆመው የቀሩ አጀንዳዎች ሆነዋል፡፡ አንዳንዶቹም ጭራሽ ተሸርሽረዋል፡፡ እነዚህ በሕገ- መንግስቱ ላይ የሰፈሩ  ዓለም አቀፍ የዴሞክራሲና የመብት ድንጋጌዎች ከሃያ አንድ አመት ጉዞ በኋላ ዛሬም ወደ መሬት መውረድ አልቻሉም፡፡ አፈጻጸማቸውና ትርጓሜያቸው ከባድ እክል ገጥሞታል፡፡ በተከታታይ የሚወጡ  እንደ ፀረ-ሽብርተኝነት፣ የፕሬስና የመያዶች ሕግጋት በነጻነት የማሰብን፣ የመደብ ጀርባ ሳያጠኑ በነፃነት የመወያየትና መረጃ የመለዋወጥን፣ የመደራጀትንና የመቧደንን መብቶች ጥርጣሬና ጥያቄ ላይ ጥለውታል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ አጣዳፊና መጠነ ሰፊ የልማት ጥያቄዎች፣ ኢኮኖሚያዊ መብቶቻችንን ሕገ-መንግስታዊ ከለላ እንዲያጡ አድርገውታል፡፡ በዚህም ምክንያት ጥረን ግረን ባፈራነው ሃብት የገዛነው ነባር የመሬት ይዞታችንና በላዩ ላይ ያሰፈርነው ሃብትና ንብረት  ማጋራትና ማከፋፈል  በሚል ስም “በፍትሐዊ  አከፋፋይነት” አጀንዳ  የመንግስት ሃብት ሆኗል፡፡ ቀሪ ሃብታችንንም የኔ ነው ብለን ለመናገር  መድፈር አቅቶናል፡፡
ምርጫዎች ከሃያ አንድ ዓመት እልህ አስጨራሽ ውጣ ውረድ በኋላ ውጤታቸው መድብለ ፓርቲን የማይወክሉና ዴሞክራሲዊ ተግዳሮቶች የወጠራቸው ሆነዋል፡፡ በእርግጥም ገዢው ፓርቲ ደጋግሞ እንደሚለው “ተመራጭ ፓርቲ” ሆኖ ሊሆን ይችላል፡፡ ዴሞክራሲ በሰፈነበት ሃገር አሸናፊ ወይም ተሸናፊ ፓርቲ መሆን በችግርነት ሊነሳ አይችልም፤ ነገር ግን 99.9 ፐርሰንት ማሸነፍ ሌላው ቢቀር  የሚነገርለትን የመድበለ ፓርቲ ስርዓት ትዝብት ላይ መጣሉ አይቀሬ ነው፡፡ የተቃዋሚዎች ድክመት እንዲሁ በባዶ ሜዳ የሚፈጠር ችግር ሊሆን አይችልም፡፡ ኢትዮጵያ ከሌላው አለም ስለማትለይ፣ ችግሩ የጋራ መሆኑን መጠራጠር ለፈተናው አይነተኛ ማነቆ ነው፡፡ ከዚህ አኳያ የመንግስት እዳ ከሃላፊነትም ሆነ ከስልጣን አልያም ከተገባው ቃለ መሃላ ጋር ተዳምሮ እዳው ታሪካዊና የትየለሌ  ነው፡፡ የሃገሪቱ ዴሞክራሲ ተቃዋሚን መውለድ እንጂ ማሳደግ ለምን አልቻለም ሲባል ሕዝባዊ አጀንዳ ስለሌላቸውና ጠንክረው ስለማይሰሩ የሚለውን ጉንጭ አልፋ ክርክር ማንሳት ዘመን ያለፈበት ይመስለኛል፡፡ ጠንክሮ ለመስራት ቢያንስ ምህዳሩ አማራጭ ሃሳብን ለመፈተሽ በቂ እድል የሚሰጥ መሆን አለበት፡፡ እንደ  መጥምቁ ዮሐንስ በበረሃ መጮህ በመንፈሳዊው ዓለም መልስ ያስገኛል፣ ውጤትም አለው፡፡ በፖለቲካ አለም ግን ፍየል ወድያ ቅዝምዝም ወዲህ ከመሆን አያልፍም፡፡  ተቃዋሚዎች በምርጫ ታሪክ ቀላል የማይባል መራጭ ድምጽ እንደሰጣቸው አሌ ሊባል የማይችል እውነታ ነው፡፡ ተቃዋሚዎች ቢያንስ እንኳን በተመረጡ ሰሞን በሙስናና በአቅም ማነስ ተገምግመው የሚባረሩትንና በሕዝብ ተቀባይነት ያጡትን የገዢ ፖርቲ ተመራጮች  ማሸነፍ እንዳቃታቸው ለማሳመን መሞከር፣ በሆድ ይፍጀው ብቻ ሊታለፍ የሚችል አይደለም፡፡ የሚቀሰቅሰውም ጥያቄ የቼኮዝሎቫኪያ ተወላጅና እንግሊዛዊ ጸሐፊ ተውኔት ቶም ስቶፓርድ   “የዴሞክራሲ መለኪያው መመረጡ ላይ ሳይሆን ቆጠራ ላይ ነው፡፡” ያለውን ነው፡፡
በመጨረሻም በጆርጅ ኢሊየት ጥቅስ ጽሑፌን ላጠልቃል፤ “ምርጫ ግም አለ፡፡ አለም አቀፍ ሰላምም ታወጀ፣ ተኩላዎችም የጫጩቶቹን እድሜ ለማስረዘም ቁርጠኝነታቸውን ገለጹ፡፡” እንዳይሆን ዛሬም ሊታሰብበት ይገባል፡፡
 http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=2914:%E1%88%9D%E1%88%AD%E1%8C%AB%E1%8B%8D-%E1%8C%8D%E1%88%9D-%E1%8A%A0%E1%88%88%E1%8D%A4%E1%89%B0%E1%8A%A9%E1%88%8B%E1%8B%8E%E1%89%B9%E1%88%9D-%E1%8B%A8%E1%8C%AB%E1%8C%A9%E1%89%B6%E1%89%B9%E1%8A%95-%E1%8A%A5%E1%8B%B5%E1%88%9C-%E1%8A%A5%E1%8A%95%E1%8B%B2%E1%88%AB%E1%8B%98%E1%88%9D&Itemid=21

Written by  አለምሰገድ አ.
ኢህአዴግና ፌስቡክ
የኢህአዴግ ካድሬዎች በተለይ ሚዲያው አካባቢ የተሰማሩቱ እንደ ፌስቡክ “አቢዩዝ” ያደረጉት የቴክኖሎጂ ውጤት ያለ አይመስለኝም፡፡ ፌስቡክን አያውቁትም ግን ይፈሩታል፣ ይሸሹታል፣ ተጠቃሚዎቹንም “አብዮተኞች” በሚል ድፍርስ ስም ይጠራሉ፡፡ ስለዚህ ኢህአዴግ በፌስቡክ አማካኝነት ማግኘት የሚገባውን ጥቅም መቶ በመቶ ሳያገኝ ቀርቷል፡፡  ኢህአዴግ የፌስቡክንና የኢትዮጵያን ዝምድና አያውቅም። በዚህም የተነሳ የፌስቡክ አብዮት ይነሳብኛል ብሎ ሰግቶ ነበር፡፡ (የምዕራብ አፍሪካ ህዝባዊ አብዮት የተቀሰቀሰ ሰሞን) በማህበራዊ  ድረ-ገጾች ላይ በጃሚንግ ዘመተ፡፡
በመጨረሻም “የፌስቡክ አብዮተኞች” ሲል አደገኛ ታፔላ ይለጥፏል፡፡ እስቲ በሞቴ ይታያችሁ… ይቺ ሀገር በፌስቡክ አብዮተኞች ኢህአዴግን ከስልጣን ስታባርር? ይሄ ብዥታ እና የእውቀት ማነስ ኢህአዴግን እንደፓርቲ፣ ኢትዮጵያንም እንደ ሃገር ከማህበራዊ ድረ-ገጾች ማግኘት የሚገባቸውን ጥቅም እንዲያጡ አድርጓቸዋል፡፡ (ወይ ነዶ!) እናም ኢህአዴግን ልመክረው እፈልጋለሁ፡፡ ፌስቡክን እንዳይፈራ!
የፌስቡክ አብዮተኞች ከየት?
ይኸውልህ ውዱ መንግስታችን… በፍጹም አትስጋ! ኢትዮጵያውን በፌስቡክ አብዮት ያነሳሉ፣ ጐዳናውን በአመጽ ያሸብሩታል ብለህ በአስቂኝ የቀትር ብርድ እራስህን አትምታ፡፡ “አብዛኛው” የፌስቡክ ተጠቃሚ ኢትዮጵያዊ ያንተ ቢጤ ነው። የፌስቡክን ጥቅም በቅጡ አልተረዳም፡፡ ምናልባትም የጅንጀና አብዮት፣ የሽሙጥ አብዮት፣ የወሲብ አብዮት፣ የስድብ አብዮት ወዘተ ከቀሰቀሰ እንጂ የፖለቲካውንስ ነገር ተወው! (ያውም የኢትዮጵያ?)
ኢህአዴግ… የምሬን ነው የምነግርህ፡፡ ከፈለግህ እገሌ እባላለሁ ብለህ “ቆንጅዬ” የአራዳ ስም ለራስህ ስጥና (ዴቭ፣ ናሂ፣ ኤቢ፣ ጃ፣ . . ምናምል ልትለው ትችላለህ) አካውንት ክፈት። ከዚያም የአንድ ሸበላ ጐረምሳ (ፀጉሩን ፈረዝረዝ ያደረገ) ፎቶ ፈላልግና “ኘሮፋይል ፒክቸር..”ህ አድርገው፡፡ ከዚያ ቢያንስ 1000 ለሚሆኑ የሃገርህ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች .. “ፍሬንድ ሪኩዌስት” ላክላቸው፡፡ ያው ያልተፃፈው የሃገራችን የፌስቡክ  ህግና ደንብ እንደሚያዘው፤ አንድ እንደ አንተ ያለ ሸበላ ኢትዮጵያዊ የፌስቡክ ተጠቃሚ፤ 90 በመቶ ጓደኞቹ ሴቶች መሆን አለባቸው፡፡ እናም “ፍሬንድ ሪኩዌስት” ከምትልክላቸው 1000 ሰዎች 900ዎቹ ሴቶች እንደሚሆኑ አትጠራጠር፡፡ መቶ ወንድ አይበቃህም? (ያውም ከተገኘ ነው) ከዚያ በኋላ በቃ ቻትህን ማጧጧፍ ነው። በተአምረኛው የፌስቡክ መስኮት በኩል ከ20 እና ከ30 የሃገርህ ልጃገረዶች ጋር በአማር-ላቲኖ (በላቲን በሚፃፍ አማርኛ) አሊያም በዝርክርክ እንግሊዝኛ ጨዋታህን ማድራት ነው፡፡ ስልክ ቁጥር መለዋወጥ፣ ኬክ ቤት መቀጣጠር ፣ በሃሜት መቦጫጨቅ፣ ተረብ መወራወር፡፡
ደሞም አትርሳ በሞቀው የቻት ወግህ ከልጃገረዶቹ ጐን ለጐን በሰፊው “ዎል”ህ ላይ ልጆች የሚያስቁ ፎቶዎችን በብዛት ፖስት አድርግ፡፡ ወዲያው መአት ኮሜንቶች ይጐርፉልሃል፡፡ ትደነቃለህ፣ ትሞገሳለህ፡፡ ፖስት ያደረካቸው ፎቶዎች እኮ ምን አይነት መሰሉህ… የአርሰናሉ አሰልጣኝ የሙሽሪትን ቬሎ ለብሰው፣ የማንቼው ደግሞ በሙሉ ሱፍ አጊጠው በሰርግ ሲጋቡ፣ ሮኒ ቫንበርሲን እንደህፃን አዝሎት፣ ቴዲ አፍሮ እጮኛውን ቀና ብሎ ሲያያት ወዘተ… አይነት ናቸው፡፡ ኢህአዴግ ሆይ… ይሄ ትውልድ የትኛውን መንበርህን ይሆን በአብዮት የሚያንቀጠቅጠው?
ግድየለህም ኢህአዴግ እመነኝ አብዛኛው የሃገርህ የፌስቡክ ተጠቃሚ ..አብዮተኛ.. የሚባል ከባድ ስም የሚሰጠው አይነት አይደለም፡፡ ዘርፈ ብዙውን የፌስቡክ ቴክኖሎጂ፣ ሁነኛ የመረጃ እና የእውቀት ማእድ የሆነውን ገበታ፣ ኢትዮጵያውያን ደንበኞቹ እንደ ጉድ እያሰቃዩት ነው፡፡ “አቢዩዝ” እያደረጉት ነው፡፡
ግን ልብ በል ኢህአዴግ!
እስከአሁን የሰነዘርኩት ወቀሳ አብዛኞቹን እንጂ ሁሉንም ኢትዮጵያዊ የፌስቡክ ደንበኞች አያጠቃልልም፡፡ በፍፁም! ጥቂቶች አሉ- ፌስቡክ የገባቸው፡፡ ድንቅ የመረጃ ምንጭ የሆናቸው፡፡ ለእነዚህ ሰዎች ፌስቡክ እና ሌሎች ማህበራዊ ድረ-ገጾች የእውቀት የመረጃ ገበያ ናቸው፡፡ ይሰጡባቸዋል። ይቀበሉባቸዋል፡፡ ቁምነገረኛ ወዳጅ ያፈሩባቸዋል፡፡ የባህል ማስተዋወቂያ፣ የፍልስፍና መሞገቻ፣ የፖለቲካ መከራከሪያ መድረካቸውም ነው፡፡
እነጊዜሽወርቅ ተሰማ እነማን ናቸው?
ጊዜሽወርቅ ተሰማ ይላል የፌስቡክ አካውንቷ ስም፡፡ ፕሮፋይል ፒክቸሯ ብስል ቀይ፣አፍንጫ ሰልካካ ፣ ደመ ግቡ ሴት መሆኗን ያሳያል፡፡ ሌሎቹ ፎቶዎቿም ተመሳሳይ እውነት አላቸው። “ጊዜ ሃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር” የተሰኘ ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ መሆኗን እና ከ2000 በላይ የፌስቡክ ጓደኞች እንዳሏት ከገጿ ላይ ሰፍሯል፡፡
ከአንድ አመት በፊት ይመስለኛል በሬዲዮ ፋና ቃለመጠይቅ ተደርጐላት ሰምቼ ነው “ፍሬንድ ሪክዌስት” የላኩላት፡፡ ወዲያው ተቀበለችኝ፡፡ ትዝ ይለኛል ሬዲዮ ጣቢያው በስኬታማ  የንግድ ሰውነቷ ነበር እንግዳ ያደረጋት፡፡ ሙዚቃ እየመረጠች ለአድማጮች ተሞክሮዋን አካፈለች፡፡ የምር ሁሉ ነገሯ ቀልብ ይይዝ ነበር፡፡ ጥያቄዎቹን የምትመልስበት መንገድ፣ የምታነሳቸው ሃሳቦች እና ድፍረቷ … የሚማርክ ነበር፡፡ በቃ ምን አለፋችሁ… አሪፍ ሴት ናት። እስከመጨረሻው እየጣፈጠችኝ አዳመጥኳት፡፡  ከሁሉም በላይ ግን ስለማህበራዊ ድረ-ገጾች እና ስለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ያላትን አመለካከት የገለጸችበት መንገድ ስለማረከኝ ነበር የጓደኝነት ጥያቄ በፍጥነት የላኩላት፡፡
በቃለመጠይቋ ምን አለች መሰላችሁ? “በእረፍት ጊዜ ብቻ አይደለም፤ እንደስራም የተለያዩ ማህበራዊ ድረ-ገጾችን በንቃት እጠቀማለሁ፡፡ ፌስቡክ፣ ትዊተር፣ ሊንክዲን፣ ፓልቶክ”  ወዘተ ሁሉንም በደንብ እጠቀማለሁ፡፡ የሃገሬን ባህል፣ ታሪክ እና ኪነጥበብ በተቻለኝ መጠን አስተዋውቅበታለሁ፡፡ የንግድ እንቅስቃሴዬን አቀላጥፍበታለሁ፣ ወዳጆች አፈራበታለሁ፡፡ ከሁሉ በላይ ግን የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን እንቅስቃሴዎች በሙሉ በንቃት እየተከታተልኩ ለአለም አሳውቅበታለሁ፡፡ ስለጠቅላይ ሚኒስትሩ አዳዲስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን አቀርብበታለሁ፡፡ በተለይም ንግግሮቻቸውን በትኩስነታቸው ከያለበት እየፈለፈልኩ ለፌስቡክ ጓደኞቼ አካፍላለሁ” (ልብ አድርጉ ሙሉ ቃሏን እንደወረደ አላቀረብኩም) “ለምን እንዲህ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ላይ አተኮርሽ?” ጋዜጠኛው ይጠይቃል፡፡ “በጣም ስለምወዳቸው፣ ስለማከብራቸውና ስለምኮራባቸው፡፡ ንግግራቸው በእውቀት የተሞላ ነው፡፡ በሳል መሪ ናቸው፡፡ ብልህ እና ለአገር አሳቢ ናቸው፡፡ እንደውም ባይገርምህ ከ5ሺህ በላይ ከእሳቸው ንግግሮች የተወሰዱ ማራኪ አገላለጾች አሉኝ፡፡”
ጊዜሽወርቅ ማብራሪያዋ ቀጥሏል፡፡ ኢትዮጵያዊያን የማህበራዊ ድረገጾችን ፋይዳ ገና እንዳልተረዱ፣ መንግስትም ድርሻውን እንዳልተወጣ በግልጽ ተናገረች፡፡ በወጉ ከተጠቀምንባቸው እንደ አሪፍ የመረጃ እና የእውቀት ምንጭ ልንገለገልባቸው እንደምንችል በሙዚቃ እያዋዛች ነገረችን፡፡ (ተባረኪ!)
ሴትየዋ እውነቷን ነው!
የፌስቡክ ጓደኛዬ ከሆነች በኋላ ሁሉን ነገር አረጋገጥኩ፡፡ እውነትም ይቺ ሴት በፌስቡክ በገንዘብ የማይለካ ትርፍ እያገኘችም እያስገኘችም ነው፡፡ በገጿ ላይ ..ፖስት.. የምታደርጋቸው ጽሁፎች፣ ኦዲዮ እና ቪዲዮ ክሊፖች፣ ፎቶዎች፣ ስእሎች ወዘተ… ሃገርን የሚያስተዋውቁ ናቸው፡፡ የአቶ መለስ ዜናዊ ፎቶዎችና ንግግሮች በብዛት ይገኙበታል፡፡ በተረፈ ስለሴቶች፣ ሰለህፃናት፣ ስለትምህርት፣ ስለጤና በጠቅላላው  ስለልማት የሚያትቱ መረጃዎች ከገጿ ላይ ሞልተዋል፡፡ ኪነጥበቡ ፣ ስፖርቱ፣ ፖለቲካው፣ ሚዲያው … ብቻ ኢትዮጵያዊ የሆነ ነገር ሁሉ የሴትየዋ የፌስቡክ ገጽ ላይ ሰፊ ቦታ ይሰጠዋል፡፡ ከእያንዳንዱ ፎቶ እና ቪዲዮ ስር በኢትዮጵያዊ ጨዋ ቃላት የተሞሉ መልእክቶችን ታሰፍራለች፣ የጠቅላይ ሚኒስትሩን እንቅስቃሴዎች ታደንቃለች፣ ትደግፋለች፡፡ የስኮላርሺፕ እድሎችን በብዛት ፖስት ታደርጋለች። ከታላላቅ መጽሃፍ የተወሰዱ እና ለለውጥ የሚያነሳሱ ጥቅሶችን በየሰከንዱ ታስነብበናለች፡፡ ታዲያ ቁጥራቸው እና አይነታቸው ይብዛ እንጂ መልእክቶቹ በሙሉ የሚሰጡት ትርጉም አንድ ነው። “እንዋደድ! በፍቅርና በአንድነት ተጣምረን ሃገራችንን እናሳድግ፤ በእውቀት እንደግፍ! በእውቀት እንቃወም! ኢትዮጵያ ለዘለአለም ትኑር!” (አሜን)

እናም ኢህአዴግ ሆይ፤
ከዚች ሴት መማር ያለብህን ትልቅ ጉዳይ አስረግጬ ልንገርህ፡፡ እስቲ… ሴትየዋ ደከመኝ ሰለቸች ሳትል በፌስቡክ የምታስተላልፋቸውን መልእክቶችና አስተያየቶች በጥሞና ለመመልከት ሞክር፡፡ አንዳንድ ዳያስፖራዎች በዘለፋና በጥላቻ ሊያስመርሩህ ይችላሉ፡፡ ቢሆንም ግን ግዴለም አትበሳጭ! ዘለህ “የፌስቡክ አብዮተኞች..” እያልክ ታፔላ አትለጥፍ! እስቲ የሴትየዋን መልሶች የበለጠ ትኩረት ሰጥተህ ተመልከታቸው፡፡ ለማን ምን እንዳለች፣ ለስድቦቹ ምን እንደምትመልስ እየደጋገምክ አንብብ፡፡ ከዚያ  ይገለጥልሃል፡፡ እውቀት እና ቅንነት ምን ያህል  አሸናፊ እንደሆነ ትረዳለህ፡፡ ሴትየዋ እና መሰሎቿ ምን አይነት ትውልድ እየቀረጹ እንደሆኑ ተገንዝበህ ትደነቃለህ፡፡ በአንተ በመንግስት ደረጃ እንኳን ያልተሰራውን ስራ አንዲት ግለሰብ በሃገር ፍቅር ተነሳስታ (ፖለቲከኛ ትሆን እንዴ? ትሁና!) ስትሰራው አይገርምም! አንተ በሩቁ የምትሸሸውን “ዲያስፖራ” እና “የፌስቡክ አማጺ ቡድን” እሷ ፊት ለፊት ስትጋፈጠው ታያታለህ፡፡
እስቲ በሞቴ ስማኝ!
የዚህችን ሴት አይነት ተግባር የሚያከናውኑ 1000 የፌስቡክ ካድሬዎች ብታሰለጥን ምን ሊፈጠር እንደሚችል? (መቼም ከዚህ ሁሉ የልማት ሰራዊት 1000 በእንግሊዘኛ የሚግባባ አይጠፋም አይደል?) በነገርህ ላይ አንድ የምታስቅም የምታናድድም መረጃ ሹክ ልበልህ (ያ ጋዜጠኛ ወዳጄ ነው ያጫወተኝ) ምን መሰለህ… የማታ ተረኛ የሆኑ የኢቴቪ ሰራተኞች እንደቀኑ አይበዙም አይደል! “ግን ምን የሚሆንበት ሁኔታ አለ” መሰለህ? የማታው የሰራተኞች ሰርቪስ ጢም ብሎ ከመሙላቱ የተነሳ ቦታ ሁሉ ይጠፋል አሉ፡፡ ለምን መሰለህ? ያለስራ የሚያመሹ የቀን ሰራተኞች ስላሉ ነው (አሉ ነው) ምን ሲሰሩ በለኛ … ፌስቡክ ላይ ተጐልተው እልሃለኋ! ይሄ “ልማታዊ ጋዜጠኛህ” ሁሉ አንዲት የቢቢሲ ዜና “እንደነገሩ” ተርጉሞልህ፣ በቀጥታ ወደፌስ ቡክ ቺኮቹ ይወረውርልሃል፡፡
ከዚያ እስከ ማታ “ሰርቪስ ሲሄድ ጥሩኝ” እያለ መጀናጀን ነው፡፡ ግራ ከገባቸው ዲያስፖራዎች ጋር አንተኑ ሲያማህ ይውላል፡፡ ለኢሳት መረጃ ልኮ ከኢቴቪ ደሞዝ ይቀበላል፡፡ (መረጃ ነው ስብቀት?)
እሺ ይሁን ልማታዊዎቹን ጋዜጠኞችህን ተዋቸው፡፡ ቆይ ባለስልጣናቱስ ምንድን ነው የሚሰሩት?፡፡
እስቲ በስሙ የፌስቡክ አካውንት ከፍቶ ስለፓርቲው የፖለቲካ አቋም የሚሰብክ፣ የሚሟገት እና ለፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሥራ የሚሰራ ባለስልጣን ካለህ አስተዋውቀኝ፡፡ የለህም፡፡ ወይም አላገጠመኝም። ግን አትድከም አታገኝም፡፡
እነጊዜሽወርቅ ደሞ አሉልህ … በራሳቸው ወጪ ያንተን ስራ የሚሰሩልህ! ስራችን ነው ብለው ስላመኑ ግን ትጋታቸው ለጉድ ነው፡፡ ኧረ ንቃ ኢህአዴግ!

እናም ኢህአዴግ ሆይ እባክህን ምክሬን ተቀበለኝ!
ግብሩ ክፉኛ በተመሳቀለው፣ ፋይዳው ሲበዛ በተንሸዋረረው የኢትዮጵያችን የፌስቡክ ሜዳ ላይ ስድቡን፣ ዘለፋውን፣ ዛቻ እና ማስፈራሪያውን ተቋቁመው ስለዚች ሀገር መልካምነት የሚተጉትን፣ የሚለፉትን እንደ ትምህርት ቤትህ እያቸው፡፡
ተማርባቸው! አይዞህ…ፌስ ቡክ አትፍራ! ድረገፆችን ጃም አታድርግ፡፡ መረጃ ሃይል ነው!!
Published in ፖለቲካ በፈገግታ
 http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=2886

በበላይ ዓለሙ
ይህችን አጭር ጽሑፍ እንድጽፍ ያነሳሳኝ ጳጉሜን 3 ቀን 2004 ዓ.ም. ማታ በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ጣቢያ የተላለፈው የአቶ ተስፋዬ ሐቢሶና የቅንጅት አባል የሆኑ ግለሰብ ውይይት ነው፡፡ ከጳጉሜን 3 ቀን በፊት ሁለት ግለሰቦች ያደረጉት ውይይት ካለ አልሰማሁምና አስተያየት መስጠት አልችልም፡፡

በዕለቱ በተደረገው ውይይት ሁለት ተፃራሪ ስሜቶች ናቸው የተሰሙኝ፡፡ አንደኛው መልካም ስሜት ሲሆን፣ ሌላኛው ግን ተቃዋሚዎቻችን እነዚህ ናቸው? እነዚህ ናቸው የአገራችን ተስፋዎች? የሚል የተስፋ መቁረጥ ስሜት ነው፡፡ በእርግጥ የቅንጅቱ አባል የተናገሩት የግል አቋማቸውን ይሁን የድርጅታቸውን መለየት ቢያስቸግርም፣ የሳቸውን የሚመስል ተመሳሳይ አቋም ከሌሎችም አንቱ ከተሰኙ ተቃዋሚዎች የሰማሁ ስለሆነ፣ የድርጅቱ አቋም ሊሆን ይችላል የሚል ኃይለኛ ጥርጣሬ ጭሮብኛል፡፡

የምሽቱ ውይይት ያተኮረው በቅርቡ በሞት የተለዩንን የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን አመራርን በተመለከተ ነበር፡፡ በእርግጥ አቶ መለስ ዜናዊን የሚያደንቋቸው ብዙ ኢትዮጵያውያንና የውጭ አገር ዜጎች እንዳሉ ሁሉ፣ በኃይለኛ የሚነቅፏቸውም በርካቶች ናቸው፡፡ በእነዚህ ሁለት ጽንፎች መሀል ያሉም አሉ፡፡

በምሽቱ በተደረገው ውይይት አቶ ተስፋዬ የኢሕአዴግ አባልና ደጋፊ ሳይሆኑ ስለ አቶ መለስ የሰጡት አስተያየት እጅግ አስደምሞኛል፡፡ በአንፃሩ የቅንጅት አባሉ የሰጡት አስተያየት እኚህ ሰው በእውነት የኢትዮጵያን ሁኔታ የተረዱ ሰው ናቸው ወይ? በእንደዚህ ዓይነት የተሳሳተ አመለካከት ነው ወይ አገርን መምራትና ሕዝብን ማሰለፍ የሚቻለው? አስብሎኛል፡፡ የጠራ የፖለቲካ መስመር ተጨባጩን አገር አቀፋዊና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታን በትክክል ከመገንዘብ ስለሚመነጭ፣ ምን ዓይነት መስመር ይሆን እነዚህ የተቃዋሚ ድርጅቶች የሚቀይሱልን የሚል ሥጋት አሳድሮብኛል፡፡

‹‹አቶ መለስ ዜናዊና ድርጅታቸው ኢሕአዴግ በኢትዮጵያ የብሔር ብሔረሰቦችን መብት ከሞላ ጎደል አስከብረዋል፤ በአገሪቱ አንፃራዊ ሰላም አስፍነዋል፤ ከዜሮ በታች የነበረውን የአገሪቱን ኢኮኖሚ ሊካድ በማይቻል መልኩ አሳድገዋል፤ በአጎራባች አገሮች የሰላምን ተልዕኮ ፈጽመዋል፤ በታላላቅ የዓለም መድረኮች የአፍሪካና የኢትዮጵያ አፍ ሆነው አስደናቂ ሥራ ሠርተዋል፤ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ሕገ መንግሥት እንዲኖራት አድርገዋል፤›› ሲሉ ነበር አቶ ተስፋዬ ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አመራር ያላቸውን ግንዛቤ ያቀረቡት፡፡ ‹‹ከዚህ በተጨማሪም የአቶ መለስ መንግሥት ጎደሎ የሌለው መንግሥት ነው ብዬ አላምንም፤ ሊሠሩ፣ ሊሻሻሉ የሚገባቸው ነገሮች እንዳሉ ሁነው አገር መምራት ቀላል እንዳልሆነ ልናውቅ ይገባናል፡፡ መልካም የሆኑትን መካድ ወይም አክብሮት አለመስጠት አይጠቅምም፤ የጎደለውን ደግሞ መሙላት የኢሕአዴግ ብቻ ሳይሆን የሁላችንም ኃላፊነት ነው፤›› ሲሉ ነበር ሐሳባቸውን ከሞላ ጎደል ያቀረቡት፡፡

ውይይታቸውን ያደመጠ አንድ ግለሰብ ኢሕአዴግ ዲሞክራሲያዊ ነው ብለው ያምናሉ ወይ ከሆነስ እንዴት? ካልሆነስ ለምን ሊሆን አልቻለም? ብሎ ለጠየቃቸው ሲመልሱ፣ ‹‹እኔ የኢሕአዴግ አባል ስላልሆንኩ ድርጅቱ ዲሞክራሲያዊ ይሁን አይሁን አላውቅም፡፡ በአገራችን ዲሞክራሲ እንዳይስፋፋ ችግር የሆነው ኋላቀርነታችን ጭምር ነው፡፡ ዲሞክራሲ የሕይወት ዘይቤ ነው ስለዚህ ኋላቀር በሆነ ኅብረሰብ ዲሞክራሲን ማስፈን ከባድ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የቅንጅቱ አባል ለዚህ ለአቶ ተስፋዬ አስተያየት የሚሉት ነበራቸው፡፡ ‹‹አቶ መለስ ለአገር ዳር ድንበር ግድ የማይሰኙ ኢትዮጵያዊነታቸው የሚያጠራጥር መሪ ነበሩ፡፡ አገሪቷዋንም በዘር ከፋፍለው ከአንድነትና ከሰላም ይልቅ መለያየትንና ግጭትን ያሰፈኑ፣ ከአገራቸው አልፈው በሌሎች አገሮች የውስጥ ጉዳይ እየገቡ አገርን የወረሩ መሪ ናቸው፡፡ ለሰላም የተላከውም የኢትዮጵያን ጦር በዶላር የሚያከራዩ ከመሆናቸው ባሻገር የአገሪቱም ኢኮኖሚ አደገ ለማለት አይቻልም፤ የተሠራው መንገድና ፎቅ ነው፡፡

እውነተኛ የኢኮኖሚ ዕድገት ከጠቅላይ ሚኒስትሩም እንደሰማሁት ኢንዱስትሪ በብዛት ሲኖር ነው፡፡ የዓለም መሪዎችም በተለይ የአፍሪካ መሪዎች አቶ መለስን ቢያደንቋቸው አይደንቀኝም፤ አምባገነን አምባገነንን ማድነቁ አዲስ አይደለም፤›› ብለዋል ከሞላ ጎደል፡፡

ይህን ጽሑፍ የማዘጋጀት ሐሳብ ስላልነበረኝ ውይይታቸውን በድምፅ መቅረጫ አልቀረፅኩትም፡፡ ስለዚህም አንኳር ሐሳባቸውን እንጂ ሁሉን ነገር መዳሰስ ስላልቻልኩ ይቅርታ እጠይቃለሁ፡፡

ከዚህ በመቀጠል በዚህ ላይና በተዛማጅ ሐሳቦች ላይ ያለኝን ሐሳብ በጥቂቱ አቀርባለሁ፡፡ ዓላማዬ የኢሕአዴግን ፖሊሲና ዕቅድ የማብራራት፣ ደግሞም በምሽቱ ለተነሱት ነጥቦች ሁለ አመለካከቴን ለማቅረብ ሳይሆን የፖለቲካ ባህላችንን እንድንፈትሽ በጥቂቱ ለማሳየት ነው፡፡

መቼም አቶ መለስና ድርጅታቸው ኢሕአዴግ ምንም መልካም ነገር ለኢትዮጵያ አላደረጉም የሚል ግለሰብም ሆነ ድርጅት ካለ፣ በእርግጠኝነት መናገር የምችለው እየተነጋገርን ያለነው ይህች ኢትዮጵያ ብለን የምንጠራት እኛ የተወለድንባት፣ ያደግንባትና አሁን እየኖርንባት ያለችውን በምሥራቅ አፍሪካ በምትገኘው አገር ሳይሆን፣ ሌላ ደግሞም አቶ መለስና ድርጅታቸው ይህችን አገራችን ኢትዮጵያ እያልን የምንጠራትን እየመራ ያለ ድርጅት ሳይሆን ሌላና የሌላ መሆን አለበት ብዬ አምናለሁ፡፡

አቶ መለስና ድርጅታቸው ኢሕአዴግ ፋሽስታዊ ደርግን ለመጣል በተደረገው መራራ ትግል ውስጥ ግንባር ቀደሙን ሥፍራ የያዙ ናቸው፡፡ ይህን የተከፈለ ዋጋ ማጣጣልና ለድርጅቱም የሚገባውን የክብር ሥፍራ አለመስጠት ከፍፁም ጥላቻ የሚመነጭ አመለካከት ወይም ደርግ ኢሠፓነት ነው እንጂ ሌላ አልለውም፡፡ ትውልድ እንደ ውሻ አስከሬኑ በአስፋልት ላይ ሲጣል፣ የሕዝቦች ደም በየገደሉና ሜዳው ሲፈስ፣ ወላጆች ጠዋሪ ቀባሪያቸውን በርስ በእርስ ጦርነት ሲያጡ፣ ሕዝብ ያለ ፍርድ ሲታረድ፣ ትግል ብለው የጀመሩ ድርጅቶችን በአንድም በሌላ ምክንያት ደርግ ቁርስና ምሳ ሲያደርጋቸውና ሲፈራርሱ፣ የተረፈው ኑሮውን ለማሳካት ትግል በቃኝ እያለ ወደ አሜሪካና አውሮፓ ሲያቀና፣ ከአገር መውጣት ያልቻለውም ወደ ዩኒቨርሲቲውና ወደየሥራው ገብቶ ኑሮውን ሲያሞቅ፣ በፅናትና ተስፋ ባለመቁረጥ የትግል መስመርን ቀይሶ ግዙፉን የደርግ ሠራዊት ያሽመደመደና የደርግ መንግሥትን የደመሰሰው ኢሕአዴግ ነው! ይህን መካድ ለዚህ ስኬት ለተከፈለው ዋጋ ዕውቅና አለመስጠትና የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡ የብዙዎቹ የ60ዎቹ ፖለቲከኞች ትልቁ በሽታ ይህ ነው፡፡

መልካም የሆኑትን የተቃዋሚ ድርጅት ክንውኖችን ጎሽ አለማለት፡፡ ጭፍን የሆነ ድጋፍና ጭፍን የሆነ የተቃውሞ ባህል፡፡ ይህ በሽታ ዛሬም መኖሩን ስመለከት ለልጆቻችን የምናወርሰው ባህል ይህንኑ ነው? እላለሁ፡፡

በአገሪቱና በአካባቢው አገሮች ሰላምን ለማስፈን የተደረገውን ጥረት ዶላር ለማግኘት የተደረገ ዕርምጃ ነው ብሎ መደምደም አስቸጋሪ ነው፡፡ መቼም የሰላም አስከባሪው ኃይል በነፃ ይሰማራ የሚል ጥያቄ ይኖራል ብዬ አልገምትም፡፡

‹‹የሚያበራየውን በሬ አፉን አትሰር›› ተብሎ የለ? ለምን ተኬደ የሚባል ከሆነም ያሳዝናል፡፡ ፕሬዚዳንት ቢል ክሊንተን በዘመነ ሥልጣናቸው ከሚያዝኑበት ነገር አንዱ በቱትሲና በጡቱ ጎሳዎች መካከል በተደረገው የ100 ቀን ግጭት ወደ ሚሊዮን የሚጠጉ ሰዎች ሲያልቁ መንግሥታቸው ምንም ለማድረጉ እንደሆነ እኚሁ መሪ ከሥልጣን ከወረዱ በኋላ ገልጸዋል፡፡ ለአፍሪካውያን ወገኖቻችን ሰላም የድርሻችንን ብናደርግ ሌላው ቢቀር ከሞራል አንፃር እንኳን ተገቢ ብቻ ሳይሆን የሚያኮራ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡

ሶማሊያን በተመለከተ አቶ መለስና ድርጅታቸው የወሰዱት አቋምና ዕርምጃ አግባብነት ያለው፣ ይህም ዕርምጃቸው ኢትዮጵያ በፀረ ሽብርተኝነት ላይ ያላትን ፅኑ አቋም ለዓለም ኅብረተሰብ ያሳየችበትና ደምቃ የወጣችበት ነው፡፡ በዋቢ ሸበሌ ሆቴል፣ በፖስታ ቤት፣ በየታክሲው፣ በሐረር ራስ ሆቴልና በሌሎችም ሥፍራዎች አሊትሃድ የሽብር ተግባር ሲፈጽም ችግሩን ከምንጩ ለማድረቅ ነበር ወደ ሶማሊያ የተገባው፡፡

በወቅቱም አሜሪካን ጨምሮ ሌሎች አገሮች ዕርምጃውን በፅኑ ቢቃወሙም የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ጆሮ ዳባ ልበስ በማለት ብቻ ሳይወሰን፣ ችግሩን ለዓለም ኅብረተሰብ ለማሳየት ያላሰለሰ ጥረት አድርጎ በኋላም የችግሩን እውነተኛነትና አደጋ የተገነዘበው የዓለም ኅብረተሰብ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጎን ሊቆም ችሏል፡፡ አልሸባብ የተባለው ሽብርተኛ ቡድን በኢትዮጵያ ላይ የጅሃድ ጦርነት በይፋ ሲያውጅ እንደ ኢትዮጵያዊ ይህንን ድርጅት ለመዋጋት አለመቆምና የተወሰደውን ዕርምጃ አለመደገፍ የታሪክ ስህተትን መድገም ነው (በኢትዮ ኤርትራና በደርግ ጊዜ በተካሄደው የኢትዮ ሶማሊያ ጦርነት ወቅት የአንዳንድ የፖለቲካ ድርጅቶችን አቋም ያስቧል)፡፡

የኢትዮጵያና የአፍሪካ ኅብረት ጦር አልሸባብን በመዋጋትና በሶማሊያ ሰላምን አስፍኖ ወደ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ እንድትጓዝ ለተከፈለው የደም ዋጋ የሶማሊያ ሕዝብ የኢትዮጵያና የሌሎች አፍሪካ አገሮች ውለታ አለበት፡፡

ስለ ኢኮኖሚው ዕድገት እውነተኛነት፣ በትምህርት፣ በጤና፣ በመንገድ፣ በእርሻ፣ በኢንዱስትሪና በሌሎችም የተገኘውን ዓለም ሁሉ የመሰከረው ስለሆነ እዚህ ላይ ማንሳት አያስፈልገኝም፡፡

ሌላው ያልተገጸው የአቶ መለስና ድርጅታቸው ኢሕአዴግ ሊመሰገኑበት የሚገባው ክንውን የሃይማኖት ነፃነትና ከአገር ወደ አገር የመዘዋወርን ነፃነትን ማስከበራቸው ነው፡፡ ከአገር ወደ አገር መዘዋወርን በተመለከተ የተገኘውን ነፃነት ያጣጣሙት በአሜሪካና በአውሮፓ ያሉት ወገኖቻችን ስለሚያውቁት ብተወው ይሻላል፡፡

በደርግ ዘመን እንኳን ከኢትዮጵያ ውጭ በአገር ውስጥም ጉዞ አስቸጋሪ እንደነበር አንረሳም፡፡ በደርግ ዘመን የአምልኮ ነፃነታቸውን ተነፍገው ንብረታቸው የተወረሰባቸውና ለእስር ሲዳረጉ የነበሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮችና ቤተ እምነቶች ለተሰጣቸው የእምነት ነፃነት በመጀመርያ ፈጣሪያቸውን፣ ቀጥለውም አቶ መለስንና ድርጅታቸውን ከልብ ያመሰግናሉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከሕመማቸው ድነው ወደ አገር እንዲመለሱ ማንም ሳያስገድዳቸውና ሳይቀሰቅሳቸው በፈቃዳቸው ያደርጉ የነበረውን በዕንባ የተሞላ ፀሎት የተመለከተ ሰው፣ ይህ ሕዝብ ውለታውን የማይረሳ ነው የሚያስብል ነው፡፡

በዚህ መካከል ደግሞ አቶ መለስና ድርጅታቸው ኢሕአዴግ ሊያደርጓቸው የማይገቡ፣ ደግሞም ሊሠሯቸው የሚገቡ ለአገር የሚጠቅሙ ክንውኖች እንዳሉ አለመቀበል ደግሞ የዚያኑ ያህል ጭፍን ደጋፊነትን ያሳያል፡፡ ዲሞክራሲን ከዚህ በላይ መገንባት ከኢሕአዴግ ብዙ ይጠበቃል፤ ጥቅሙ ለሁሉም ነው፡፡ ይህን ተገንዝቦ በሚያልፍ ሕይወት የማያልፍ ታሪክ ሠርቶ ማለፍ እንዴት ያስደስት ይሆን?

አቶ ተስፋዬ ዲሞክራሲ በአገራችን እንደሚገባው ያላደገበት ምክንያት በኋላቀር ባህላችን ነው ያሉትን እስማማለሁ፡፡ ይህ ደግሞ የቅንጅቱ አባል እንዳሉት ሕዝብን መናቅ አይደለም፡፡ እንዲያውም ሕዝብ ያልሆነውን ነህ ማለት ይመስለኛል ንቀት፡፡ እያሞኘኸው እንደሆነ እንደማይረዳ ቆጥረኸዋልና፡፡

በአገራችን ዲሞክራሲያዊ ባህል እንዳያድግ ካደረጉት ተጨማሪ ምክንያቶች አንዱ ፖለቲከኞቻችን በማርክሳዊ ሌኒናዊ ርዕዮተ ዓለም የተጠመቁ መሆናቸው አስተዋጽኦ አለው እላለሁ፡፡ ተቃዋሚን እንደ ጠላት የሚፈርጀው ይህ ርዕዮተ ዓለም ተቃዋሚን በጥይት እንጂ በውይይት ለመርታት አይፈጥንም፡፡ አሁንም የምናየው የስም ማጥፋትና እስር የዚህ ውልድ ነው፡፡ ለመሆኑ ዛሬ በሠለጠነው አገር የሚኖሩ የተቃዋሚና የኢሕአዴግ ደጋፊዎች እንደ አገር ዜጋ ይተያያሉ? እንዲያው እውነቱን እንነጋገርና በአሜሪካ የኢሕአዴግ ደጋፊዎች የተቃዋሚዎች ወከባ፣ ግልምጫና ስም ማጥፋት ሳይደርስባቸው በነፃነት ሐሳባቸውን ያራምዳሉ? ኢሕአዴግን የመደገፍ አዝማሚያ ያለው አርቲስት በአሜሪካና በአውሮፓ መልካም አቀባበል ይደረግለታል?

ከዚህ በተጨማሪ የሕዝቡ አለመደራጀት ዲሞክራሲያዊ ባህል እንዳይዳብርና ለዲሞክራሲያዊ መብት በፅኑ እንዳይታገል እንዳደረገው መካድ አይቻልም፡፡ ለተቃዋሚዎችም ትልቁ የቤት ሥራ ይህ ይመስለኛል፡፡ ዋጋ ከፍሎ ከቀበሌ ጀምሮ እስከ ላይ ድረስ ማደራጀት፡፡ ዋጋ ሳይከፍልና ሕዝብ ሳይደራጅ ሥልጣን መያዝ በአጋጣሚ ካልሆነ በስተቀር አይቻልም፡፡ በአጋጣሚም ቢያዝ የሚመሠረተው መንግሥት ፅኑ ዲሞክራሲያዊ መንግሥት ሊሆን ያዳግተዋል፡፡

እንዳንደራጅ ኢሕአዴግ አላሠራንም መቼም አይባልም፡፡ ለነገሩ ኢሕአዴግም ተቃዋሚውን እንደ ጠላት ስለሚያየው ይህን ለማድረግ ወደ ኋላ የሚል አይመስለኝም፡፡ ነገር ግን ለመብትና ለነፃነቴ መደራጀት አለብኝ ብሎ ዋጋ የማይከፍል ትውልድ ከሆነ ይህ ትውልድ፣ እንግዲያው ሌላው ዋጋ በከፈለበት ነፃነትን ሊጎናፀፍ የሚሻ ነውና ቆም ብሎ እንደ ሻማ ለመቅለጥ መወሰን፣ ወይም ደግሞ መተው ይሻል ይመስለኛል፡፡ እኔ ግን የመብት ረገጣ እስካለ ድረስ ለመረገጥ ፈቃደኛ ያልሆነ ሕዝብ ይኖራል ብዬ አምናለሁ፡፡ መቼም ሁሉም ለመብቱ እኩል ተቆርቋሪ ላይሆን ይችላል፡፡ ‹‹ጎመን በጤና›› የሚልም አይጠፋም፡፡ ቁምነገሩ ያለው ሕዝቡን በጠራ የፖለቲካ መስመርና ባህል በሩቅ አስቦ አሁን ሥራን በትጋት መወጣት ላይ ነው፡፡ የኢትዮጵያ አብዮት ሁሌም ችግሩ ነባራዊና ህሊናዊ ሁኔታ አለመዛመድ ነውና፡፡ ስለዚህ ሕዝቡን ማደራጀት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል፡፡ የተደራጀ ሕዝብ ምን ዓይነት ዋጋ እንደሚከፍል የቅርብ ጊዜ ትዝታችን ነው፡፡ ደርግን ለመፋለም ያንን ሁሉ ዋጋ የከፈለው ትውልድ የተለየ ትውልድ ሆኖ አይደለም፤ የተደራጀ እንጂ፡፡ የ1997 ዓ.ም. ምርጫን ተመልክቶ በአገራችን የተነሳው እንቅስቃሴ በቀላሉ የተዳፈነው በበቂ የተደራጀ ሕዝብና በሳል አመራር ባለመኖሩ እንደሆነ ይታመናል፡፡

በመጨረሻም አቶ መለስና ድርጅታቸው ለዚህ ሕዝብና አገር ታላቅ ውለታ የሠሩና እየሠሩ ያሉ ናቸው፡፡ ተቃዋሚ ነን የሚሉ ወገኖች ይህንን መካድ አይገባቸውም፤ (ለነገሩ ሁሉም ተቃዋሚ አይክድም) አለመካድ ብቻ ሳይሆን በጥሩ ክንውኖች ላይ ማበረታታትና ከጎን መቆምን ሊያስተምሩን ይገባል፡፡ ዛሬ እኛ ያላደረግነውን ልጆቻችን ከየት አይተው ያደርጉታል? ከአሜሪካ ሕዝብ ሳይሆን ከእኛው ከአባቶቻቸው ይህን እየተማሩ ማደግ አለባቸው፡፡ በተረፈ ግን የጠራ የፖለቲካ መስመር ለመያዝ ተጨባጩን የኢትዮጵያና የዓለም አቀፍ ሁኔታ በአግባቡ ማወቅ እጅግ አስፈላጊ ስለሆነ፣ ተፎካካሪዎች ይህን አጥብቀው ቢመለከቱት እመክራለሁ፡፡ (አንተን ማን መካሪ አደረገህ ካልተባልኩ!)

እግረ መንገዴን አንድ የታዘብኩትን ነገር ልንገራችሁ፡፡ ብዙዎች የኢሕአዴግ የቀድሞ አባላት ስለ አቶ መለስ አመራር፣ ብሩህ አዕምሮና ስትራቴጂስትነት ሲናገሩ፣ እንዴት አድርገው ድርጅቱን ከጠባብ ብሔርተኛነት ትግል ወደ ብሔራዊ ትግል እንደቃኙት፣ ከማርክሳዊ ሌኒናዊ (አልባኒያኒዝም) ርዕዮተ ዓለም አቀንቃኝነት ወደ ቀኝ ኃይል እንዴት ዘመም እንዳደረጉት፣ የደርግ ሠራዊትን ለመጣልና የሻዕቢያ ወረራን ለመቀልበስ ዋና ወታደራዊ ስትራቴጂስት እርሳቸው እንደነበሩ ሲናገሩ፣ ለዚህ ሁሉ ነገር በእርግጥ እርሳቸው ብቻ ነበሩ ባለ ራዕይ? ብዬ እንድጠይቅ ተገድጃለሁ፡፡ በእርግጥ ለሁሉም ጉዳይ ባለ ራዕይና ቀዳሚ ቀያሽ እርሳቸው ብቻ ከነበሩ፣ የሞቱት አቶ መለስ ዜናዊ ብቻ ሳይሆኑ ኢሕአዴግም ነው አስብሎኛል፡፡ ከዚህም ተነስቼ ኢሕአዴግ በቀደመው ጥንካሬ እንዲጓዝ ትልቅ የቤት ሥራ ከፊቱ እንዳለ መገንዘብ ያለበት ይመስለኛል፡፡ መቼም መሪን ከሁሉ ነገር በላይ ትልቅ የሚያደርገው ተተኪዎችን ማፍራት መቻሉ ነውና አቶ መለስ ተተኪዎችን አዘጋጀቱው ከሆነ በእርግጥም ታላቅ መሪ ነበሩ፡፡

አቶ ክፍሉ ታደሰ የተባሉ የኢሕአፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል ‹‹ያ ትውልድ›› በተሰኘ መጽሐፋቸው ‹‹የፓርቲው ዋና ፀሐፊ የአቶ ተስፋዬ ደበሳይን ሞት ስንሰማ የማዕከላም ኮሚቴ አባላት ሁላችንም ኢሕአፓ በቀድሞ ወቡቱና ጥንካሬው መቀጠል እንደማይችል በልባችን ተገንዝበን ነበር፤›› አሉ፡፡ ለኢሕአዴግም ሆነ ለተፎካካሪዎች ይህን አልመኝም፡፡ ኢትዮጵያ ጠንካራ መሪዎች ያሉባት ተፎካካሪ ድርጅቶች በእጅጉ ያስፈልጓታልና፡፡ ለመሆኑ መቼ ይሆን የፖለቲካ ባህላችን የሚለወጠው? እኛ ካልጀመርነው ማን ይሆን የሚጀምርልን?
ቸር ይግጠመን፡፡            

አዋሳ መስከረም 21/2005 የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደቡብ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከ18 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገዙ አምቡላንሶችን ለአምስት ዞኖች አከፋፈለ። በክልሉ ከሚገኙ ቅርንጫፍ ማህበራት አምስቱ ከህብረተሰቡ ባሰባሰቡት ገንዘብና ከማህበሩ ከ18 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ እንዲገዙ ከታዘዙት 20 አምቡላንሶች የአስሩ ትናንት ርክክብ ተደርጓል። በርክክብ ስነስርዓቱ ላይ የደቡብ ክልል ቀይ መስቀል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የቦርድ ሰብሳቢና የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታመነ ተሰማ እንዳሉት መንግስት በነደፈው ዕቅድ መሰረት የእናቶችና ህጻናት ሞትን ለመቀነስ ለሁሉም ወረዳዎች እንዲዳረስ እያደረገ ነው። መንግስት እየተገበረ ያለውን የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ እያደረገ ያለውን ጥረት መንግስታዊ ያልሆኑ ማህበራትና ህብረተሰቡ እያደረጉ ያለው ተግባር የሚያበረታታ መሆኑን ጠቁመው የደቡብ ቀይ መስቀል ማህበር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የገዛቸው አምቡላንሶች የእናቶችና ህጻናትን ሞት ለመቀነስ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነው ብለዋል። አምቡላንሶቹ ለታለመላቸው አገልግሎት ብቻ እንዲውሉ በማድረግ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡና የወረዳዎቹ ማዘጋጃ ቤቶች የነዳጅና አስፈላጊ ወጪያቸውን በመሸፈን ድጋፍ እንዲያደርጉ አቶ ታመነ አሳስበዋል። በኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር የደቡብ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መኮንን ፋራ አዲስ የተገዙት አምቡላንሶች በክልሉ የነበረውን የአምቡላንሶች ጣቢያ ከ22 ወደ 44 የሚያሳድገው መሆኑን ጠቁመው የጋሞጎፋና ደቡብ ኦሞ ካቶሊካዊት ቤተክርስትያን 944 ሺህ ብር ወጪ በማድረግ ለደቡብ ኦሞ ዞን ሀመር ወረዳ አንድ አምቡላንስ መግዛታቸውን ተናግረዋል። አምቡላንሶቹ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች አረጋውያንና ነፍሰጡር ሴቶችን ወደ ህክምና በማድረስ የሚያበረክቱት አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመዋል። የቤንች ማጂ ደቡብ ኦሞ ጋሞጎፋ ሲዳማና ጉራጌ ዞኖች ቀይመስቀል ማህበራት አምቡላንሶቹን የተረከቡ ሲሆን ቀሪዎቹም አስር አምቡላንሶች በቅርቡ እንደሚገቡ ገልጸዋል።
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=2644&K=1