POWr Social Media Icons

Monday, September 3, 2012ነሀሴ ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ወ/ሮ አዜብ መስፍን ባለቤታቸውን በሞት ካጡ በኃላ በእሳቸው እግር ተተክተው የህወሃትን የሊቀመንበርነት ቦታ ተቆናጥጦ ወደ ኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበርነት ለመሳብ ድጋፍ የማሰባሰብ ዘመቻ ላይ መክረማቸውን ምንጮቻችን ጠቆሙ፡፡
በኢህአዴግ 36 የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ውስጥ ብቸኛ ሴት ሆነው በመስከረም ወር 2003 ዓ.ም ከፍተኛውን የፓርቲ ሥልጣን በባለቤታቸው በአቶ መለስ ዜናዊ ልዩ ድጋፍ ማግኘት የቻሉት ወ/ሮ አዜብ የሰሞኑን ሐዘናቸውን ለድጋፍ ማሰባሰቢያ እንደተጠቀሙበት ምንጮቻችን ተናግረዋል፡፡
ወ/ሮ አዜብ ለድጋፍ ማሰባሰቢያ ይጠቅሙኛል የሚሉዋቸው የህወሃት ሰዎች ለቅሶ ለመድረስ ቤተመንግስት በሚመጡበት ወቅት አንገታቸውን እያነቁ በማልቀስና በማስለቀስ፣የማይፈልጉዋቸውን ደግሞ ፊት ሲነሱ መቆየታቸው በተለይ በአመራር ላይ ባሉት የብአዴን ሰዎች ዘንድ አልተወደደላቸውም፡፡
ወ/ሮ አዜብ ባለቤታቸው አቶ መለስ በ8ኛ ድርጅታዊ ጉባኤ በጡረታ ያሰናበታቸው አቶ ሥዩም መስፍን፣አቶ አባይ ጸሐዬ፣አቶ አርከበ ዕቁባይ፣አቶ ተፈራ ዋልዋ፣አቶ አዲሱ ለገሰን “የመለስን ራዕይ ለማሳካት” በሚል ስትራቴጂ ከጎንዋ ለማሰለፍ ከፍተኛ ጥረት ሲያደርጉ መሰንበታቸውን ምንጮቹ ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮዋ በአቶ መለስ ቀብር ፕሮግራም ላይ በወ/ሮ ነጻነት አስፋው የተዘጋጀላቸውን ኦፊሻል ንግግር በመተው የራሳቸውን ኃሳብ ያንጸባረቁበት ንግግራቸው “መለስ የጀመራቸው ፖሊሲና ስትራቴጂዎች እስካልተበከሉና እስካልተበረዙ ድረስ …” የሚለው ንግግራቸው በመለስ ስም ለጀመሩት የድጋፍ ማሰባሰብ ጥረታቸው ይረዳቸው ዘንድ ሆን ብለው ያደረጉት መሆኑን ምንጫችን  አስቀምጦአል፡፡
የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች ከዚህ ሳምንት ጀምሮ ጉባኤያቸውን በማካሄድ ለሁለት ዓመታት የሚቆዩ አመራሮቻቸውን የሚመርጡ ሲሆን በመጪው መስከረም ወር ኢህአዴግ በአቶ መለስ ዜናዊ ምትክ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን ሊቀመንበር አድርጎ ይመርጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በተለይም በአቶ ኃይለማርያም ተይዞ የነበረው የምክትል ሊቀመንበርነት ቦታ ህወሃት ላለማጣት ከብአዴን ጋር ፍጥጫ ውስጥ መግባቱን፣በዚህ ፍጥጫ ውስጥም ወ/ሮ አዜብ አሸናፊ ሆነው ለመውጣት እየጣሩ ነው፡፡ህወሃት ወ/ሮ አዜብ መስፍንን በሊቀመንበርነት ከተቀበለ የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበርነት ቦታ የማግኘታቸው ጉዳይ አጠራጣሪ እንደማይሆን ከወዲሁ መገመቱን ምንጫችን ጠቁሟል፡፡
በአሁኑ ሰዓት የህወሃት ሥራ አስፈጻሚ በመሆን በማገልገል ላይ ካሉት ውስጥ አቶ መለስ በሞት ሲለዩ ብዙዎቹ ከኢህአዴግ የመተካካት ስትራቴጂ ጋር ተያይዞ በአዲስ የሚተኩ ናቸው፡፡
አቶ አባይ ወልዱ የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበርና የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት፣ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም፣አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ፣አቶ ጸጋዬ በርሄ (የቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንትና በአሁኑ ወቅት የጠ/ሚኒስትሩ አማካሪ) ፣ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል፣ወ/ሮ አዜብ መስፍን፣አቶ በየነ ምክሩ፣አቶ አባዲ ዘሙ የህወሀት የስራ አስፈጻሚ አባላት መሆናቸው ይታወቃል።
በተያያዘ ዜና ከ12 ቀናት በፊት የአቶ መለስ ሞት እንደተሰማ የሚኒስትሮች ም/ቤት ተሰብስቦ አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝን በተጠባባቂ ጠ/ሚኒስትርነት እንዲሰሩ ውሳኔ ያሳለፈ ቢሆንም የም/ቤቱ ውሳኔ ከህግ አግባብ ውጪ ነው የሚል ቅሬታ በኢህአዴግ አመራር ውስጥ በመፈጠሩ ለጥቂት ቀናት “ተጠባባቂ፣ጊዜያዊ” በመባል በመንግስት መገናኛ ብዙሃን ሲነገርላቸው የነበሩት አቶ ኃይለማርያም ምክትል ጠ/ሚኒስትርና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ብቻ እንዲባሉ በተላለፈው ትዕዛዝ መሰረት ሚዲያዎቹ በዚሁ መሰረት እየሰሩ መሆኑ ታውቋል፡፡
የአቶ ኃይለማርያም ሹመት ቅሬታ ያስነሳው ጠ/ሚኒስትር(ተጠባባቂን ጨምሮ) እንዲሾምለት ዕጩ የማቅረብ ሥልጣን የገዥው ፓርቲ ኢህአዴግ እንጂ የሚኒስትሮች ም/ቤት ሥልጣን አይደለም፡፡ኢህአዴግ ዕጩ ካቀረበ በኃላ በቀጥታ ለፓርላማ ቀርቦ ሌሎችም ዕጩዎች ካሉ ተጠቁመው ተወዳድሮ ከተመረጠ በኃላ ቃለመሃላ ፈጽሞ ወደሥራ መግባት አለበት የሚል ህግ ነክ ክርክር ቀርቦ በማሸነፉ መሆኑን ምንጫችን አስታውሶአል፡፡በዚህ ውሳኔ መሰረትም አቶ ኃይለማርያም ጠ/ሚኒስትሩ በሌሉ ወቅት ተክተው ይሰራሉ በሚለው የህገመንግስቱ ድንጋጌ መሰረት በቀድሞ ማዕረጋቸው እየሰሩ መሆኑ  ነው፡፡
በፓርላማ ሊያደርጉት ታስቦ የነበረውም ቃለመሃላ እንዲሰረዝ የተደረገው ከዚሁ ምክንያት ጋር ተያይዞ መሆኑም ታውቋል፡፡ከሳምንት በፊት ይህው ጉዳይ በመግለጫ ላይ የተነሳባቸው አቶ በረከት ስምኦን የፓርላማ አባላቱ ሐዘን ላይ በመሆናቸው መራዘሙን መግለጻቸው የሚታወስ ነው፡፡
ትናንት በተካሄደው  አቶ መለስ የቀብር ሥነ-ስርዓት ላይ የውጪ አገር መሪዎችና ተወካዮች በንግራቸው መግቢያ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝን “ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር”እያሉ ቢጠሯቸውም የ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ግን በተደጋጋሚ ፦”ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር” ሲላቸው መዋሉ ይታወሳል።
የኢቲቪ ጋዜጠኞች ከ ሥነ-ስርዓቱ  መጀመሪያ አንስቶ እስከመጨረሻው ድረስ የነበረውን ሁኔታ በቀጥታ ስርጭት እያስተላለፉ በሚነጋገሩበት ወቅት በተለያዩ ጊዚያት በትንሹ ወደ 20 ጊዜ የአቶ ሀይለማርያምን ስም የጠቀሱ ሲሆን፤ ከነዚህ አጋጣሚዎች  በአንድኛቸው እንኳ ሳት ብሏቸው ፦”ተጠባባቂ ጠቅላይ ሚኒስትር”ብለው አልጠሯቸውም።
በተለይ በመስቀል አደባባይ የነበረው ዝግጅት ተጠናቆ አስከሬኑ ወደ ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል በሚያመራበት ጊዜ የኢቲቪ ጋዜጠኞች አድርጉ ተብለው የታዘዙ እስኪመስል ድረስ በተደጋጋሚ ፦”ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ” እያሉ  በተከታታይ  ሲናገሩ ተደምጠዋል።
የአቶ መለስ ቀብር በመጠናቀቁ፤ የአቶ ሀይለማርያም ሹመት መጽደቅ እና አለመጽደቁ በቀጣዮቹ ቀናት ይታወቃል ተብሎ ይጠበቃል።


የሲዳማ የክልል ጥያቄን በተደራጀ መልኩ ለማቅረብ የብሄሩን ሽማግሌዎች በመደራጀት እና የክልል ኣስፈላጊነትን በተመለከተ ለህዝቡ በማስረዳት ከፍተኛ የሆነ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ በዩኒቨርስቲ ተመሪዎች ስሰራ መቆየቱ የሚታወስ ሲሆን፤ ግንዛቤ የመፍጠር ኃላፊነት ወስደው በመስራት ላይ ከነበሩት ወጣቶች መካከል ኣንዳንዶቹ በግልጽ ባልታወቀ ምክንያት ቡድኑን በመልቀቅ ላይ ናቸው።

ስማቸው እንድገለጽ ያልፈለጉ የሲዳማ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናገሩት፤ ጸረ የሲዳማ ክልል ኣቋም ያላቸው ግለሰቦች ኣንዳንድ ተማሪዎችን በገንዘብ በመደለል እና በማስፈራራት በሲዳማ የክልል ጥያቄ ላይ ያላቸውን ኣቋም እንዲቀይሩ በማድረግ ላይ ናቸው።

እነዚሁ በገንዘብ ተደልለው ጸረ የሲዳማ ክልል ኣቋም ካላቸው ቡድኖች ጎን የተቀላቀሉት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ሌሎች ከዚህ ቀደም ኣብሯቸው ሲታገሉ የነበሩት በማጋለጥ እና በማሳሰር ላይ ናቸው ብለዋል።

ለኣብነትም የሲዳማን ሽማግሌዎች በማደረጀት ከፍተኝ ሚና ከተጫዎቱች ተማሪዎች መካከል ሁለቱ በቅርቡ መታሰራቸውን ኣመልከተው፤ የተቀሩትም በመፈለግ ላይ መሆናቸው ተናግረዋል።በወንዶ ገነት ወረዳ በፊቼ ማግስት የሲዳማን የክልል ጥያቄ የሚያወድሱ ግጥሞችን እየገጠሙ ቄጣላ የወጡ ወጣቶች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች ታፍሰው መታሰራቸው የሚታወስ ሲሆን፤ ከታሰሩት ወጣቶች መካከል 12ቱ እስከ ኣሁን ኣልተፈቱም።

ወጣቶቹ እስከ ኣሁን ድረስ ለምን እንደታሰሩ የሚገልጽ ምንም መረጃ የሌላቸው ሲሆን፤ የታሰሩበትን ምክንያት በይፋ እንደማያቁ እና ዛሬ ነገ ትፈታላችሁ እየተባሉ በእስር ላይ እንደምገኑ ገልጸዋል።

በሙስና ተጠርጥረው ለሰባት እና ስምንት ወራት ከታስሩ በኃላ ባለፈው ወር ውስጥ የተመሰረተባቸው ክስ ውድቅ ተደርገው የተፈቱ ግለሰቦች በክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ለፍርድ ልቀርቡ ነው።

ጉዳያቸው ያይ የነበረው የከተማዋ ፍርድ ቤት በነጻ የለቀቃቸውን እነዚሁ  የሙስና ተጠርጣሪዎችን በተመለከተ ኣቃቤ ህግ ለክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይግባኝ በማስገባቱ የተነሳ መዝጋባቸው ለሁለተኛ ጊዜ ይከፈታል ተብሏል።
ጉድ ሳይሰማ መስከረም ኣይጠባ ኣይደለም? መለስ ዜናዊ የሚባለውን ሀይማኖት አማኖች ኣይጋ ፎረም ላይ ያወጡትን መግለጫ ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ያንቡ

I am a born-again believer & my religion is Meles Zenawi
Adal Isaw
adalisaw@yahoo.com
September 2, 2012
By the will of the Goddess of Ethiopia, I believe, Meles Zenawi was born for reasons other than the ordinary ones that you and I were born for.  Meles was born to lead and help build a modern, sovereign, and a free Democratic Republic of Ethiopia. I have a reason to revert back to the religion that I have abandoned early in life.  Things were trite and nothing was out of the ordinary then, and, I had to walk away from my religion as a result.  But now, and after many years of abandoning my religious belief, I am a born-again believer and my religion is Meles Zenawi. I believe in Meles Zenawi and he is my religion from now on till the end of my time.  This I believe is not the result of stretching my emotion.  Instead, it is the result of seeing the tangible change in the life of Ethiopia—in part, by way of my newly found religion; I aver.
Meles Zenawi is my religion for he is not the ordinary Ethiopian that I can ordinarily relate to.  He is my religion and hence a singularity that I would not dare to humanize.  To humanize Meles is to imbue him with the trite and the redundant—it is as if to equate him with a stiff person who may need to relax to be himself by therapy of some kind.
Meles is beyond humanizing.
To lionize Meles is not that different either; it is  equally trite and mundane, and it
depletes his deeds to equate them with the deed of a general who had won a battle over an enemy that he may end up befriending in later days.  Meles is beyond lionizing and he is my religion for being so.  Meles is not a hero either, for a hero these days connotes among many things the deeds of those who manage to save cats and dogs from the grinding tires of a city bus.  Meles is the savior of an entire nation and beyond whose deeds are beyond the deeds of a hero; his 
deeds emanate from his extra ordinary life—a life that is worth worshiping at any cost.
Indeed;  Meles Zenawi is my religion for he is a rarity—a gift from the Goddess of 
Ethiopia.  And hence, he is the religion that I have now—a religion that is not that 
disparate from customary religions whose Gods rarely come as saviors with the flesh, bone and blood of our kind.  Yes; Meles Zenawi is a rarity and our kind, but he is not as ordinary as we are even in the minuscule sense of how we manage to live our lives with respect to the life of Ethiopia.  It is his life that defines and separates Meles Zenawi from us.  His life is not ordinary and no one believes in the power of the life of the ordinary.  
By extension, therefore, Meles Zenawi is my religion for I believe in the life of the extra ordinary.I believe in Meles Zenawi, because, as a proud Ethiopian by no other than my own claim, I have nothing to show for as a matter of proof otherwise.  My tears; my tears of several days cannot be my witness for I know for sure that they are guilt-induced for most part.  My tears if any are the manifestations of my guilt over not having the gut to be as selfless as an Ethiopian as the martyrs that paved the way for me to be a very proud Ethiopian.  
Believe me; I am so aware not to kid myself and insult my conscience.  If I am short of the gut and the commitment that mimics the commitment and gut of our martyrs, I should be held in contempt for claiming to be a proud Ethiopian.  Where did I go wrong and for what reason?  How is it possible for my single life ith few others to become the premise for me to draw back from a commitment of the kind that our martyrs paid for millions of our kind?    
After the  “passing” of Meles, especially, I shiver while asking myself a very simple 
question: what have I done lately to make me feel a very proud Ethiopian?    And the answer:  nothing; nothing compared to our selfless martyr Meles Zenawi whose very deeds are now the basis of my religion for action.  Believe me or not,  I am a born-again believer for this precise reason and Meles Zenawi is my religion.  What is yours?  And what have you done lately to induce in yourself the feeling of a very proud Ethiopian?

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 28 (ኤፍ ቢ ሲ) የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት www.meleszenawi.gov.et   በሚል ስያሜ ይፋ ያደረገው ድረ ገጽ አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በእንድ ቋት ላይ ለማግኘት ያስችላል።

ድረ ገጹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በህይወት ዘመናቸው በውጭና በሃገር ውስጥ ያከናወኗቸውን ተግባራት በቃለ መጠይቆች፣ በንግግሮች፣ በጽሁፍና በምስል መረጃዎችን ለድረ ገጽ አንባብያን የሚያቀርብብት ነው።

እንዲሁም በየትኛውም ሀገራት ያሉ ተጠቃሚዎች የሃዘን መግለጫቸውን ባሉበት ቦታ በመሆን መላክና የላኩትንም መልዕክቶች ማየት ያስችላለቸዋል።

እንግሊዝኛን ጨምሮ በአራት የውጭና በሶስት የሀገር ውስጥ ቋንቋንዎች የተዘጋጀው ይኸው ድረ ገጽ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ታሪክ ዙሪያ ጥናት ለማድረግ ለሚፈልጉ ሰዎችና አካላት ትክክለኛ መረጃን ይሰጣል።


Welcome to P.M Meles Zenawi

MelesMeles Zenawi was born on 8th May 1955 at Adwa in northern Ethiopia. He received elementary education at the Queen of Sheba Junior Secondary School and completed High School in 1972 at General Wingate School in Addis Ababa. He then joined the Medical Faculty of Addis Ababa University where he studied for two years.
Meles interrupted his studies in 1974 to join the Tigrai Peoples Liberation Front (TPLF). He was elected to the Leadership of the Leadership Committee of the TPLF in 1979 and to its Executive Committee in 1983. He is chairman of both the TPLF and the Ethiopian Peoples Revolutionary Democratic Front (EPRDF) since 1989. EPRDF is a political alliance of the four main political organisations in the country.http://www.meleszenawi.gov.et/en/