POWr Social Media Icons

Monday, August 27, 2012

የሲዳማ ሕዝብ የሀገር ኩራት በሆነው በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት የተሰማውን መሪር ሀዘን ሲገልጽ ለመላዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲሁም ለቤተዘመዶቹ መጽናናትን በመመኘት ነዉ !! ይሁንና በርካታ የሲዳማ ብሔር ተወላጆች በማይታወቅ ምክንያት ታስረዉ ይሄን ብሔራዊ ሀዘን ለመካፈል ባለመቻላቸዉና የዋስ መብት እንኳ በመነፈጋቸዉ እሮሮአቸዉን በማሰማት ላይ ይገኛሉ፡፡ 

በሕገ-መንግስቱ በአንቀጸ 39 ላይ የተደነገገውን መብት እስክንጎናጸፍ ድረስ የማንነት ጥያቄአችን ከምንም ጊዜ በላይ ተጠናክሮ ይቀጥላል፤ በምንም ዓይነት ሁኔታ አይቆምም!!!

ውድ የሲዳማ ብሄር ተወላጆች በሀገር ውስጥና ከሀገር ውጭ የምትገኙ በሙሉ እንኳን በዓይነቱ ልዩ ለሆነውና በሲዳማ ታሪክ የመጀመሪያ ሊባል ለሚገባው ለ2005 ዓ.ም ሲዳማ የዘመን መለወጫ fichee cambalaalla በዓል ለማየት፣ለመስማት አበቃችሁ/ በሰላም አደረሳችሁ/ን/!! 
የሲዳማ ዘመን መለወጫ የfichee cambalaalla በዓል ነሐሴ 9/2004/ በሲዳማ ቀን አቆጣጠር መስከረም 1/ 2005 ዓ.ም በአስገራሚ ሁኔታ ከዚህ ቀደም በታሪክ ታይቶና ተሰምቶ በማይታወቅ መልኩ በዓሉን ለማክበር ከየአቅጣጫዉ ወደ ሀዋሳ የመጡት የብሔሩ ተወላጆች ብቻ ሌሎች ታዳሚዎችን ሳይጨምር በጥቂቱ ቁጥራቸው ወደ 2.5ሚሊየን የሚጠጉ በባህላዊ አጋጌጥ ተውበው ጦርና ጋሻቸውን አንግበው በዋና ከተማቸው በድምቀት ለማክበር በቄጣላ በመግባታቸው የከተማውን ሕዝብ ጉድ ያስባለና ያስደነቀ ታሪካዊ በዓል መሆኑ ይታወሳል፡፡ 
በዕለቱም ሰፊው የሲዳማ ሕዝብና የበዓሉ ታዳሚዎች/ተጋባዥ እንግዶች በዓሉን እንደጓጉለት ለማክበር አልታደሉም፡፡ በዓሉን ለማክበር የወጣውን የሕዝብ ብዛት ከሩቁ የተመለከቱና ከየአቅጣጫው በቄጣላ የዘመኑ የሙዚቃ ቅንብር በማይተካ መልኩ በተፈጥሮ ድምፅ ብቻ በተቀነባበረ ጣዕመ- ዜማ ከሩቁ እያስተጋቡ የሁሉንም ስሜት ስኮረኩርና የሁሉንም ስሜት ያማከለ ቄጣላ የሁሉም ቀልብ ሲገዛ የሲዳማ ሕዝብ ከጫፍ እስከ ጫፍ ድረስ አንድ መሆኑን በማየታቸው ብቻ የኢህአዴግ አመራሮች በቀን ምድር ሲቃዡ ተስተውሏል፡፡ 

በዕለቱም በህይወታቸው ታሪካዊ ፍርሓትና ድንጋጤ ያስተናገዱ ከፍተኛ አመራር የተሰኙ ካድሬዎች መላው የሲዳማ ሕዝብ በጉጉት/በናፍቆት የጠበቀውን በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚያከብረውን ከሩቅና ከቅርብ በዓሉን ለመታደም የመጡ እንግዶች በሙሉ ሰፍ ብለዉ በመጠበቅ ላይ ሳሉ የመንግስት አካላት ከፍርሓት የተነሳ ብቻ ገና ሕዝቡ ወደ ጉዱማሌ መግባት እንደጀመረ ምንም ይሉኝታ ሳይዛቸው በዓሉ እንዳይከበር በማድረግ ሕዝቡን ከጣዋቱ 3፡30 ከመንገድ ወደኋላ እንዲመለሱ በማድረጋቸውና መግለጫ በማስተላለፋቸው ግማሹ እያዘነ ወደየቄኤያቸው ሲመለስ ሌሎች በዋና ከተማቸው ሀዋሳ ሀገር ሰላም ብለዉ በቄጣላ በማክበር ላይ እያሉ ፖሊስ ከከተማው ሂዱ ውጡ በማለት ክፉኛ ደብድቦአቸዋል፡፡ ለአብነትም በቀድሞው የሲዳማ ህዝብ የትግል ጀግና ታጋይና አታጋይ በነበሩ በአቶ ወልደአማኑኤል ዱባለ ሀውልት አከባቢ እና በከተማው ውስጥ ለውስጥ መንገድ ላይ የነበሩት በጥቂቱ 250 የሚጠጉት በፖሊስ ተደብድበዋል፡፡ 
የዚህ ሁሉ መነሻ የሆነውን ጉዳይ ይህ ዓምድ ቁልጭ አድርጎ ያስቃኛችኋል፡፡ ነገሩ እንዲህ ነው፡-
ከዚህ ቀደም የሲዳማ ዘመን መለወጫ የfichee cambalaalla በዓል ሲከበር ሕዝቡ የልቡን በልቡ ይዞ(ሸሽጎ) በቄጣላ ለኢህአዴግ መንግስትና መሪዎች ሲቸረው የነበረውን ክብርና ሙገሳ(GUWEENYA) በየወረዳ፣ በዞንና በክልል ያሉ አመራር አካላት በብሔሩ ህልውና በማንነት ጉዳይ ላይ ከመቀለዳቸውም ባለፈ ከጊዜ ወደ ጊዜ ንቀታቸው እያየለ ስለመጣ በጉዳዩ የተከፋ መላው የሲዳማ ሕዝብ በአንድነት ተነስተው ከዚህ ቀደም ያስለመዱትን የሙገሳ ግብር ዳግም ላይከፍላቸው ሕዝቡ ወደ ማይናጋ አቋም በመድረሱ ብቻ ነው፡፡

የሲዳማ ብሄር እንዲህ በአንድነት ተባብሮ የመንግስትን ድርጊት እንዲጠየፍ ያደረገዉ ፡- 
የሲዳማ ሕዝብ ህገ-መንግስታዊ እራስን በራስ የማስተዳደር መብት ለዛውም በ1994ዓ.ም የነፍስ ግብር የከፈለበትን የማንነት ጥያቄ ለመቀልበስ ክልል ከመሆን“ልማት”ይሻላችኋል በማለት ህፃናትን ለማባበል እንደሚጠቀሙት “ከረሜላ” እያደረጉ ነገር ግን በተግባር ጥፋት እየሰሩ ህዝቡን ለመሸንገል ከመሞከራቸውም ባለፈ የክልል ጥያቄ የሕዝብ ጥያቄ ሳይሆን አንዳንድ ጥቅም ፈላጊ ግለሰቦች ያነሱት ጥያቄ ነው በማለት በየሚዲያዎች የሚያደርጉትን የውሸት ማስተባቢያዎቻቸውን በቄጣላ ስላወገዙ ፤ 
በየሚዲያዎች የሲዳማን ሕዝብ ስብዕና እየነኩ ክልል ለሲዳማ ሕዝብ ፋብርካ አይደለም እያሉ መግለጫ መስጠታቸው ፤
የሀዋሳ ከተማ ከሀገር አቀፍ እንዲሁም ከክልል ከተሞች በፈጣን እድገቱና በውበቱ በተደጋጋሚ ሲሸለም ባልታወረ ዓይናቸው እያዩ የሲዳማ ሕዝብ ከተማውን ለማስተዳደር ብቃት ስለጎደለው ሌሎች የዕውቀት አስተዋፅዖ በማበርከት በስብጥር ያስተዳድሩ በማለት የሕዝቡን ሞራል ከመጉዳትም ባለፈ ባልሆነ ነገር ሕዝቡን በአደባባይ በክልልና በሀገር አቀፍ ሚዲያዎች ማዋረዳቸው
ያለምንም ወንጀል ሕዝቡን እያሰሩ ማሸማቀቃቸው፣ 
የማንነት ጥያቄ ይዞ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው ያሰሙትን ወጣቶች ዘራፊዎች/ዱሪዬዎች ናቸው በማለት የወጣት ምሁራኖችን ስብዕና መንካታቸው ከብዙ ጥቂቶቹ ሲሆን ይህንን በቄጣላ ስላወገዘ ብቻ ነው፡፡
ስለሆነም ከድርጊታቸው እጅግ በጣም የተማረረው መላው የሲዳማ ብሄር ተወላጆች በሙሉ መንግስት በሲዳማ ሕዝብ ላይ እየፈፀመ ያለውን ኢ-ዴሞክራሳዊ/ኢ-ሰብዓዊ ድርጊታቸውን በfichee camballalla በዓል ክፍተት አግኝተው እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩትን ነጥቦችን ከማውገገዛቸውም ባለፈ የማንነት/የክልል) ጥያቄ የግለሰቦች ጥያቄ ሳይሆን የሰፊው ሕዝብ ጥያቄ ነው፣ መብታችን ይከበር ፣ጥያቄያችን ይመለስ ፣ ጥያቄያችንን ለመቀልበስ በጥቅማጥቅም ግለሰቦችን መደለልና ሕዝቡን በእስራት ለማሸማቀቅ/ለማስፈራራት የሚደረገው አንባገነንነት ይቁም በማለት ድምፃቻን ከፍ አድርገው አሰምቷል፡፡ 
ከዚህም የተነሳ በንዴት የተሞሉ አመራሮች ፀጉራቸውን እየነጩ በዕለቱ(በጫምባላላ) ወደ ምሽት አከባቢ አስቸኳይ ስብሰባ በመጥራት ሰላማዊ ግለሰቦችን ለማሰር ማቀዳቸውን ከውስጥ ምንጮች ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡

ስለዚህ የኢህአዴግ አመራሮች/ካድረዎች አጸያፍ ድርጊቸውን ወደ ጎን ትተው በተለይ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ለምን በቄጣላ እንደ ያነው አልተወደስኩም በማለት የተናደደው ሆነ ብሎ ምክንያት በመፍጠር በአሁኑ ሰዓት ከ200 መቶ በላይ የሆኑት ምሁራኖች፣ተማሪዎችን የሀገር ሽማግለዎችን ያለ ምንም ወንጀል በግፊ እስፘቸዋል ፡፡ከእነዘዚህም ተጨማሪ ወደ 170 የሚጠጉ ሌሎች ሰላማዊ ሰዎች ለማሰር ስለማቀዳቸውን መረጃዎች ከተለያዩ ምንጮች ለማግኘት ተችሏል፡፡ ይህም ሆነ ተብሎ ሕዝቡን ለማስፈራራትና ስነ-ልቦናዊ ፍርሐት ለመፍጠር የሚደረግ ሙከራ መሆኑን ህጻን ሳይቀር በሚገባ ተገንዝቧል፡፡ 
ስለሆነም በዚህ በድርጊታቸው እጅግ በጣም የተበሳጨው ሰፍው የሲዳማ ሕዝብ በየወረዳቸው ተቃውሞዓቸውን በሰላማዊ ሰልፍ ለመግለፅ መረጃ በመለዋወጥ ላይ የሚገኙ ስሆን ከዚህ በስም በዝርዝርና በቁጥር የተመለከቱት በአሁኑ ሰዓት ታስረው የሚገኙ ናቸው፡፡

ተ.ቁ ስም ዝርዝር የሚሰሩበት ቦታ ያሉበት ሁኔታ የታሰሩበት ምክንያት 

ረጅም መንገድ ተጉዘው ለመጠየቅ ብሎ የሚመጡ ቤተሰቦች፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸውና የሰራ ባልደረቦቻቸው የፖሊስን ደጅ ብቻ በማጥናት መሪር ሀዘን ይመለሳሉ
በጠቅላይ ሚኒስቴሩ ሞት የተማቸውን ሀዘን ለመግለጽ የዋስ መብት ጠይቀው ተከልክለው ብሔራዊ ሀዘናቸውን በእስር ቤት እያሳለፉ ይገኛሉ፡፡ 
ካላ ብርሃኑ ሀንካራ

1.አቶ ብርሀኑ ሀንካራ የሲዳማ ልማት ማህ.ኃላፊ 
2.አቶ ካሳ አዲሶ ነጋዴ 
3.አቶ ዘርፉ ዘዉዴ የሲዳማ ዞን አቅም ግንባታ 
4. አቶ ኦዋታ የሀገር ሽማግሌ
ካላ ኣባቴ ኪሞ ሆኮላ

5. አቶ አባቴ ኪሞ አለታ ወንዶ 
5. በወንዶገነት ወረዳ 50 ሰዎች ታስረዋል 
6.በጎርቸ ወረዳ 40 ሰዎች ታስረዋል 
7.ይርጋዓለም ከተማ 7 ሰወች ታስረዋል 
8. መለሰ አጋሮአ wolootuno addi addi bayicho usurante noota macciishshate dandiinoommo......... 


የዚህ አምድ የመጨረሻው መልዕክት 
1. አንድም የሲዳማ ብሔር ተወላጅ የሆነው በክልል /በማንነት ጥያቄ የተነሳ ልጅህ/ሽ፣ ወንድምህ/ሽ፣አባትህ/ሽ፣ወዳጂህ/ሽ በግፍ ስታሰር ዝም አትበል/ይ/ሉ ባለህበት ቦታ ሆነህ/ሽ/ችሁ አጥብቀህ/ሽ/ችሁ ማውገዝ፤
2. ሕዝቡ የሚጠቅመውንና የሚጎዳውን ነገር ለይቶ እንደማያውቅ አድርገው ክልል ከመሆን ልማት ይሻለናል በማለት ታች ከቀበሌ እስከ ክልል ድረስ ለሚትገኙ የተባሉት/ የተላኩበትን እለፈፉብህ አላዋቅ የሚያደርጉህን፣ማንነትህን እያዳፈኑ ታሪክህን የሚያበላሹትን ከዳር እስከ ዳር አንድ በመሆኖን በጽኑ አቋም እንታገል፤
3. ሰፊው የሲዳማ ሕዝብ መሪር ሀዘናቸውን/ ብሶታቸውን በአደባባይ ማፍረጠረጡን ተከትሎ ከላይ በስም ዝርዝራቸው የተመለከቱትን ሕዝብ የሚወዳቸውና የሚያከብራቸው በመሆናቸው ብቻ በጉዳዩ ሳይኖሩበት አይቀሩም በማለት አስፘቸዋል፡፡ ሰለሆነም መንግስት ከሳሽም ፈራጅም ሆነው ስያሻው እያሰረ ስያሻው ዕለቀቀ ብዙ ወገኖቻችንን እያሸማቀቀ አእምሮአቸውን እየጎዳ ይገኛል፡፡እንደሚታወቀው ከዚህ ቀደም ብዙ ምሁራኖች የሀገርየወገን ፍቅር ያላቸው ለትውልድ ትልቅ አሻራ ያስቀመጡ ለሲዳማ ብቻ ሳይሆን ለአለም የሚበቁ ለምሳሌ እነ ዶ/ር ወላሳ እና ሌሎችም በዚህ በተመሳሳይ ችግር የተነሳ ከሀገር ተሰደዋል፡፡ ስለዚህ መንግስት በዜጎች ላይ የሚያደርሰውን ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት ባለንበት ቦታ ሁሉ ላይ ሆነን መቃወም የግድ ይለናል፡፡
4. የሲዳማ ብሄር ተወላጆች የዩኒቨርስቲ፣ የኮሌጅ የአንደኛና ለሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች በሙሉ በእረፍት ጊዜያችሁ ለቤተሰቦቻችሁ ሰፍ ግንዛቤ በማስጨበጥ ትልቅ ለውጥ እንዳስመዘገባች ይታወቃል፡፡ ስለሆነም የህዝባችን ጥያቄ ምላሽ እስክያገኝ ድረስ ጥረታችሁን/ን ከምን ጊዜ በላይ በማጠናከር የራሳችንም ሆነ የሰፍው ሕዝብ ህልም እውን ለማድረግ እንነሳ!! 
5. የሲዳማ ታሪክ ታሪካችሁ፣ ክብር ክብራችሁና የማንነት ጥያቄ ጥያቄያቸሁ የሆነው በውጭ ሀገር በየትናውም አህጉር የሚትገኙ የሲዳማ ብሄር ተወላጆች የሆናችሁ በሙሉ ከምንም ጊዜ በላይ ከሕዝቡ ጎን ቆማችሁ የህዝቡን መብት ጥቅም እንዲታስከብሩና ህጋዊና ሕገ-መንግስታዊ የክልል ጥያቄ በመጠየቃቸው የተነሳ መንግስት በሕዝቡ ላይ እያደረሰ ያለውን በደል፣ እስራት፣ ድብደባ ፣አፈናና ሰቆቃ ከምንም ጊዜ በላይ ከህዝቡ ጎን ቆማችሁ እንዲትታገሉ፣እንዲትቃወሙ በሕዝብና በሰማዕታት ስም እንማጸናችኋለን፡፡ ይህንን መልዕክት ብያንስ ብያንስ 5 ሰው እናስተላልፍ! ሲዳማ ስምና ታሪክ አለው በአቅጣቻ ተጨፍልቆ በምንም ዓይነት አይዳፈንም!!

Qixxeessinohu: Usurtinonnte Manna
http://www.facebook.com/groups/289317227830513/permalink/323382971090605/
በትናንትናው እለት ቁጥራቸው ከሶስት ሺ በላይ የሚሆኑ የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት ለኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር ኣቶ መለስ ዜናዊ በሃዋሳ ከተማ በሲዳማ ባህል መሰረት ኣልቅሰዋል።

በሲዳማ ባህል መሰረት ለጀግና እንደምለቀሰው ሁሉ ለኣቶ መለሰ ዜናዊም እንጨት ተተክሎ ቀይ ተቀብቶ የተለቀሰላቸው ሲሆን፤  'ጎባ ባኢታ ኣና ሆጌ' እያለ በቄጣላ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሞት የተሰማውን ሀዘን ገልጿል።

በሃዘን መግለጫ ስነስርዓቱ ላይ ከሽማግሌዎች የተወከሉ እና የክልል መንግስቱ ባለስልጣናት ንግግር ያደረጉ ሲሆን፤ በንግግራቸው በኣቶ መለሰ ዜናዊ የተጀመሩ የልማት ስራዎች ከዳር እንዲደርሱ ሁሉም በጋራ እንዲሰራ ጥር ኣቅርበዋል።

በስነስርዓቱ ላይ የክልል እና የሲዳማ ዞን ባላስልጣናትን ጨምሮ የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች እና መንግስት ባዘጋጃቸው መኪኖች ባህላዊ ልብስ እንዲለብሱ ተደርገው ከየወረዳዎቹ የተጋበዙ ሰዎች መገኘታቸውን ወራንቻ ኢፎርሜሽን ኔትዎርክ ዘግቧል ።