POWr Social Media Icons

Monday, August 20, 2012


በሲዳማ ዞን ውስጥ የተነሳውን ህዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ ሰዎች ህዝብ በመንግስት ላይ በማነሳሳት በምል እየታሰሩ ሲሆን፤ ሰሞኑን ታስረው ፍርድ ቤት በመቅረብ ላይ ካሉት በተጨማር ዛሬ ምሽት ላይ ካላ ጥሩነህ ቱቀላ የተባሉ በሲዳማ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የሚስሩ የሁለት ልጆች ኣባት ከበንሳ የተሰሩ ሲሆን፤ ሌላው ደግሞ  ካላ ደሳለኝ ወልደ ሚካኤል የተባሉ በዞኑ ሴቶች እና ህጻናት ጉዳይ ቢሮ የሚሰሩ የሶስት ልጆች ኣባት ከቦና ታስረዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በርካታ ቁጥር ያላቸው ግለሰቦች ሃዋሳ ከተማ እና በሌሎች የዞኑ ከተሞች እና ወረዳዎች በመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በመታደን ላይ ናቸው።

ኣንዳንድ የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ በላኩት መልእክት፤ የመንግስት ኃይሎች በደፈናው ሰዎችን የተለያዩ  ስሞችን እየለጠፉ በማሰር እና ሰብኣዊ መብት በመረገጥ ላይ ስለሆኑ የሚመለከተቸው የሰብኣዊ መብት ተቆርቋር ዓለም ኣቀፍ ኣካላት ጠልቃ እንዲገቡ ጥሪ ኣቅርበዋል። 


በሲዳማ ዞን ውስጥ በመንግስታ የጸጥታ ኃይሎች እየተፈጸመ ያለው ሰብኣዊ መብት ረገጣ የተባባሰ ሲሆን በርካታ ሰዎች ህዝብን በመንግስት ላይ በማነሳሳት በምል በመታሰር ላይ ናቸው።

በዞኑ ውስጥ የክልል ጥያቄን ጋር በተያያዘ የተቀጣጠለውን ህዝባዊ ንቅናቄ  ለመቀልበሰ በኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ የምመራው የደቡብ ክልል መንግስት በሚያደርገው ጥረት የተለያዩ  ኣፈናዎችን በመፈጸም ላይ ነው።

ሃዋሳ ከተማ የተጀመረው ግለሰቦችን የማሰር እና የማስፈራራት ተግባር ወደ ተለያዩ ወረዳዎችም የተዛመተ  ሲሆን፤ ለኣብነት ያህል ባላፈው ቅዳሜ ከታሰሩት 46 ግለሰቦች በተጨማሪ እስከ ዛሬ ምሽት ድረስ በጎርቼ ወረዳ በርካታ ቁጥር ያላቸው ግለሰቦች  ታስረዋል።

ሰሞኑን ከታሰሩት የሲዳማ ተወላጆች መካከል ጥቅቶቹ ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፤ ጉዳያቸው ከኣስራ ኣንድ ቀናት በኃላ እንዲታይ ቀጠሮ ተሰጥቷቸው ወደ እስርቤት ተመልሰዋል።

ዛሬ ከፍርድ ቤት ከቀረቡት መካከል የቀድሞ የዳሌ ወረዳ ምክትል ኣስተዳዳሪ ካላ ዘገዬ ሀመሶ  እና ካላ ብርሃኑ ሀንካራ  ይገኑበታል።  

ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሰዎች ሙሉዝርዝር ከታች ይመልከቱ 
They were all presented to Court and appointed for 25th of August 2004 E.C (11 days from now). They are to stay there until then!!! Cry freedom!! Cry Sidama!! Innocent Elites and Intellectuals are being brutalized in front of the world in the mid of 2012!!! No

Name

Education BG

Address

Time/Date Caught

Family /Dependents under the detainees

1

Kassa Odisso

Investor/Elder

Aroressa

20/08/12

38 (Including Children)

2

Boshola Gabiso

Investor/Elder

Aroressa

20/08/12

14 (Including Children)

3

Birhanu Hankara

Msc

Gorche/Hawassa

20/08/12

7

4

Owato Damota

Elder

Malga

20/08/12

10

5.

Dukale Lamiso

Msc

Bensa/Hawassa

15/08/12

8

6

Bekele Wayu

Msc

Arbegona/Hawassa

15/08/12

4

7

Abate Kimo

MA

Aleta/Hawassa

16/08/12

2

8

Iyasu Regassa

MA


10/08/12

6

9

Zerfu Zewde

MA


11/08/12

4

10

Zegeye Hamesso

MA


17/08/12

5

Part One 

Part Two


በአገር ዉስጥና ውጭ ለምትገኙ ለስዳማ ተወላጆች በሙሉ 
የሲዳማ ሕዝብ የማንንም በር አንኳክቶ ደጃፉንም ረግጦ አያውቅም። ዎሮበሎችና ሌቦች ግን በተከታታይ ዘመናት ለመዳፈር
ሞክረዋል። የሲዳማ ሕዝብ ከአጼ ምንልክ ሥርወ መንግስት አንስቶ አሁን እየተንገዳገደ እስካለው የወያኔ ከፋፋይና ዋሾ መንግሥት
ድረስ ለዲሞክራሲና ለነፃነቱ የምያደርገዉን ትግል ባለማቌረጥ በየደረጃዉም ያገኟቸውን ድሎች በማጎልበት ነፃና ያልተሸራረፈ
የሥልጣን ባለቤትነት የሚረጋገጥበትን ሥርዓት ለመመሥረት ተመሳሳይ አቋም ካላቸው ኃይሎች ጋሪ ግንባር በመፍጠር ትግሉን
በማፋፋም ላይ ይገኛል።ዛሬም ትግሉ ቀጥሎ ወደ አድስ ምዕራፍ መሸጋገሪያ ደርሰናል።
አሁን ያለንበት ሁነታ በትዕብትና በጥላቻ የተዎጠረዉ ህወሃት/እሕአደግ በሕዝባችን ላይ እያደረሰ ያለው በደል ከምንግዘዉም የኬፋበት
ነው።ጥቅት ግለሰቦችን በገንዘብና በስልጣን በመደለልና መማታለል የራሳቸዉን ጥቅም ያስጠብቃሉ፡በተለያየ መልኩ ከሕዝባችን
በዘረፉት ገንዘብ መልሰዉ ሕይወቱን ለማኮላሸት ይጥራሉ፡ ብሳካላቸዉ አንድነታችንን ለማናጋትና ከፋፍለዉ ልገዙን ቀንና ሌልት
ይደክማሉ፡ ብዙዎችንም ለስደትና ለመከራ ዳርገዋል፡ለዘመናት ተከባብረን ከኖርንባቸዉ ጎሮበቶቻችን ሕዝቦች ጋር ትንኮሳን በመፍጠር
ለዕልቅት ለመዳረግ ይጥራሉ፡መሠረታዊ መብትን ለመጠየቅ የወጣዉን ሕዝባችንን በቈየዉ በግፍ ጨፍጭፈዋል።በአሁኑ ግዘ በተለይ
በህገመንግስቱ የተደነገገዉን ራስን በራስ የማስተዳደር መብት እንድሰጠዉ ህዝባችን ለአመታት ከዳር እስከዳር እየተንቀሳቀሰ ስጠይቅ
የቆየዉን መብት ጥቅማቸውን ስለሚነካባቸዉ ከማስፈጸም ይልቅ ሕዝባችንን በእስራትና በአፈና ለማንበርከክ እየዳዳቸዉ ናችው።
አምባገነኑ መር መለስ ዜናዊ ከተሰወሩ ወራቶች ቢያልፉም ከንቀታቸው የተነሳ መርጦናል ለምሉት ሕዝብ እንኳ እዉነታዉን ትንፍሽ
አላሉም፡ ይልቁኑ የኢትዮጵያ ሕዝብ አንቅሮ እንደተፋቸዉ ስላልተገነዘቡ የአገዛዝ ዘመናቸዉን ለማስረዘም እየዶለቱ ይገኛሉ።
በሌላ በኩል ደግሞ ከወያኔ ባላነሰ ዲሞክራሲን የምፈሩ ተላላዎች የተዛባና የተሳሳተ ዜናዎችን  በማናፈስ በእጅጉ መስዋዕት
የከፈልንለትን የትግላችንን አቅጣጫ ለማስቀየር ይሞክራሉ።
በመሆኑም ወቅቱ ጠንካራ የጋራ ትግልና ህብረትን ከመጠየኩም በላይ ታርካዊ ግደታችንም ስለሆነ በአገር ዉስጥና ዉጭ ላላችሁ
ለሲዳማ ተወላጆች በሙሉ የምከተለውን ጥሪ እናቀርባለን፡
1.  ብዙ ወገኖቻችን መስዋዕት የከፈሉለትንና እየከፈሉ ያሉለትን የነጻነት ትግል ከዳር ለማድረስ ሁላችን በቁርጠኝ ከመቸዉም ግዜ
በበለጤ መንቀሳቀስ አለብን። ማንኛውን የሰብአዊ መብት ረገጣ መረጃዎችን እርስ በርስ መለዋወጥና አለምአቀፋዊ አካላት
እንድያዉቁት ማድረግ
2.  በውጭ የምትገኙ የሲዳማ ተዎላጀች አሁን በመካሄድ ላይ ያለውን እንቅስቃሰ በቅርብ በመከታተል በተለያዩ መገናኛ ዘደዎች
ተገብዉን ድጋፍ እንድታደርጉና በሁሉ መልኩ ከሕዝቡ ጎን እንድትቆሙ
3.   በሀገር ውስጥ የምትገኙ የሲዳማ ተዎላጆች በደል የምደርስባቸውን ወገኖች በቅርበት መከታተልና በጐናቸዉ እየቆማችሁ
የታሰሩትንና ቤተሰባቸውን መጠየቅና አስፈላግውን ትብብር እንድታደርጉ።
4.  የሕዝቡን ትግል ለማኮላሸት በባንዳነት የቆሙትን በመከታተል መረጃዎችን በማሰባሰብና በማጋለጥ በሕዝቡ እንድተፉ እንድታደርጉ
5.   የሕዝቡን የትግል አቅጣጫ ያልተከተለ ሀሰተኛ ዜናዎችንና ወረወችን የምያናፍሱ የውጭና የዉስጥ ኋይሎችን ማጋለጥና መዋጋት
6. በመጨረሻም የወያኔ ተለጣፍ የሆናችሁ በሙሉ ለማይቀረው ዲሞክራስያዊ ሽግግር ተሳታፍ ለመሆን ከወያኔ የባርነት አገዛዝ ነፃ
ለመውጣት ከሲዳማ ሕዝብ ላይ በማንሳት ከጎኑ እንድትቆሙ ኅብረቱ ጥሪ ያቀርባል።
               ድል ለሕዝባችን፡ሽንፈት ለወያኔና ለግብረአበሮቹ!!
                             USPJF
                          ነህሰ 13 2004
http://www.sidamaliberation-front.org/sidama-kai.pdf
የመግለጫውን ሙሉቃል በእንግሊዥኛ

General Carter F. Ham, head of the U.S. Africa Command has persuaded the ruling party in Ethiopia, the Tigrean People’s Liberation Front (TPLF) to appoint Hailemariam Dessalegn as prime minister until the next fake election, according to Ethiopian Review Intelligence Unit sources. The TPLF junta has been resisting Hailemariam’s appointment fearing that power may slip from their hands… This is a developing story. Stay tuned for more updates.
http://www.ethiopianreview.net/index/?p=42052

በሀዋሣ ከተማ ዙሪያ የሚሰራው የተፋሰስ ልማት ሥራ ውጤት እየታየበት መሆኑ ተገለፀ፡፡በተፋሰስ ልማት በተደራጁ ወጣቶች ሠሞኑን ከ25 ሺህ በላይ የሀገር በቀል የዛፍ ችግኞች  በታቦር ተራራ ላይ ተክለዋል፡፡
ተክለው በኢየሩሳላም የህፃናትና የማህበረሰብ ልማት ፕሮግራም ጽህፈት ቤት አስተባባሪነት የተከናወነ መሆኑም ተመልክቷል፡፡የጽህፈት ቤቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ማስረሻ ክብረት እንደገለፁት ድርጅቱ በከተማው በአከባቢ ጥበቃ ሥራ በተደጋጋሚ ባከናወነው ተግባር ተጨባጭ ለውጥ ማምጣት ችሏል፡፡
ተከላውን በይፋ ያስጀመሩት የሃዋሣ ከተማ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በላይ በቀለ በበኩላቸው የከተማውን ልማት ለማፋጠንና ፀዳቷን ለመጠበቅ በአከባቢ ጥበቃ ሥራ ላይ የተሠማሩ ወጣቶች ያበረከቱት አስተዋፅፆ ከፍተኛ መሆኑን ገልፀው፤ አስተዳደሩም አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል፡፡
በዕለቱ ከኢየሩሳሌም ህፃናትና ማህበረሰብ ልማት ፕሮግራም ለ3 ማህበራት ከ75 ሺህ ብር በላይ የሚያወጡ የእርሻ መሣሪያዎች ድጋፍ ተደርጓል፡፡በተከላውም ከከተማ አስተዳደሩ፤ ከየትምህርት  ቤት የአከባቢ ጥበቃ ክበብ አባል ተማሪዎች፤ በማህበር የተደራጁ ወጣቶችና ሌሎችም ተሣታፊ ሆነዋል፡፡ ባልደረባችን በረከት ጌታቸው እንደዘገበችው፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/11NehTextN204.html