POWr Social Media Icons

Monday, August 13, 2012


በሃዋሳ ከተማ ነገ እና ከነገ ወዲያ የሚከበሩት የጫምባባላ እና የፊቼ በኣል፤ የሲዳማ ህዝብ መለያ እሴቶች በመሆናቸው ልዩ ትኩረት ስጥተው ለማክበር የተለያዩ ዝግጅቶት ተደርገው በመጠናቀቅ ላይ መሆኑ ተገልጿል።

በበኣሉ ላይ ከሁሉም የሲዳማ ወረዳዎች የታጋበዙ ሰዎች ተሳታፊ እንደምሆኑ ሲገለጽ፤ በነገው እለት የጫምባባላ በኣል በሲዳማ  ባህል ኣዳራሽ ከሲዳማ ቋንቋ ስምፖዚዬም ጋር በጥምር ይከበራል።

የዞኑ ማስታዎቂያ እና ባህል መምሪያ የቋንቋ ስምፖዚዬሙን ኣስመልክቶ ያዘጋጃቸውን ቲሸርት እና ኮፊያ ለበኣሉ ተሳታፊዎች በማደል ላይ ሲሆን፤በዚምፖዚዬሙ ላይ የሲዳማን ቋንቋ እና ባህል በተመለከተ ጥናታዊ ጽሁፎች እና ውይይቶች ይካሄዳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

በሲዳማ ባህል ኣዳራሽ ዝግጅት ላይ እንድገኙ የተለያዩ የመንግስት ባላስልጣናትን ጨምሮ  ታዋቅ ሰዎች እና የሃዋሳ ከተማ  ነዋሪዎች ተጋብዘዋል።

የፊቼ በኣል ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ ከሲዳማ ህዝብ ወጪ በዞኑ ነዋሪ በሆኑ በሌሎች ብሄሮችም ጭምር እየተከበረ ያለ ሲሆን፤ ከሌሎች ኣካባቢዎችም  በርካታ ሰዎች በኣሉን ከሲዳማ  ህዝብ ጋር ለማክበረ ወደ ሃዋሳ ከተማ ይመጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የሃዋሳ ከተማ  ኣስተዳዳር እና የሲዳማ ዞን ለበኣሉ ድምቀት የፖሊስ ማርሽ ኦርኬስትራ ያስመጡ ሲሆን፤ የፖሊስ ኦርኬስትራው  የተለያዩ ጣእመ  ዜማዎችችን  በበኣሉ ያቀርባል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ካለፈው ወር ጀምሮ ከሲዳማ ክልል ጥያቄ ጋር በተያያዘ በሲዳማ ዞን ውስጥ ተነስቶ የነበረው  ህዝባዊ  ንቅናቄ  በፊቼ  ኣከባበር ላይ ችግር ልፈጥር ይችላል በምል የጸጥታ ቁጥጥሩ መጥበቁ እየተነገረ ሲሆን፤ ከሃዋሳ መግቢያ ላይ በተለይ ሞኖ ፖል ላይ ግለሰቦች የጦር መሳሪያ ይዘው ወደ ከተማ እንዳይገቡ እየተፈሹ ነው።

መንግስት በማድረግ ላይ ካለው የጸጥታ ቁጥጥር በተጨማር የሲዳማ ሽማግሌዎችም በኣሉ በሰላማዊ ሁኔታ እንድከበር ጥር ኣቅርበዋል።