POWr Social Media Icons

Tuesday, August 7, 2012


ካላ ሽፈራው ሽጉጤ

ሙሉ ጽሁፉን ለማንበብ ከታች ካለው ፎቶ ላይ ዴብል ክሊክ ኣድጉ 
... ራሳች እራሳችን ስናስተዳድር አንድ ሲዳማ ሆነን ክልላዊ መንግስት ከመሰረተን የሚከተሉ ጥቅሞችን እንጎናጽፋለን፤ ሲዳማ
1. የራሱ መንግስት በክልል ደራጃ ይመሰርታል፤ ከማንም መጨፈለቅን ያስወግዳል፤ ነጻነት ያገኛል፤
2. የክልሉ ህገ-መንግስት ይኖረዋል፣ የራሱ ክልል ም/ቤት ይመሰርታልም፤ የሀዋሳ ጥያቄ ዳግም አይነሳም፤
3. የራሱን ገቢ ይሰበስባል፣ ራሱን ያለማል ለፈደራል ከተተወው ውጪ/ አሁንኮ ለክልል ያስገባል ደግሞም ደቡብ በሙሉ በኛ ክሳራ ይለማበታል/
4. የክልል፣ የዞኖች፣ የወረዳዎችና ቀበሌ መዋቅሮች ማንም ሳይቀላቀልበት ይኖሩታል፤ ይህ በመሆኑ የራሳችንን ሀብት ለራሳችን ልማት ስለሚናውል አሁን ከሚናየው ዕድገት የበለጠ አርንጓዴ የሆነች ሲደማን በርግጥ የሚናያት ይሆናል፤ በዓለም ደረጃ ጎብኚዎች ሳቢ የሆነ አከባቢ እንፈጥራለን፤ 
5. ከሁሉም ክልሎች ህዝብ እኩል የፌደራል መንግስት ስልጣን ድርሻና እኩል ውክልና ይኖረዋል፤
6. ቡና፣ ጫትና ሌሎች ምርቶችን ከአሁኑ በሚበልጥ አግባብ በማቅረብ የተሻለ ኢኮኖሚ ያመነጫል
7. ትውልዱ የመብት ጥያቄው ስለተመለሰ እጅግ በጣም በሳይንስና ተክኖሎጂ ፈጠራ በመሳተፍ ስራ ፈጣሪ በሚያደርጉት ተግባራት ጊዜውን የሚጠቀም ይሆና
8. በኢትዮጲያ ታርክ ህገ-ምንግስቱ ተግባራዊ የሆነበት አጋጣሚ የሚፈጠር በመሆኑ ዴሞክራሲ ከቆመበት አንድ እርምጃ መራመድ ይጀምራል
9. የመብት ጥያቄን ያነሳሉ፣ ለሲዳማ ዳግም መነሳት ከፍተኛ ሚና ይጫወታሉ ተብለው ከሀገር እንዲሰደዱ የተደረጉ የዓለማችን ብርቅዬ ምሁራኖች ወደ ክልላቸው ተመልሰው በእውቀታቸው ያለሟታል፤ ይመሯታል፤ ሀብታቸውን ያፈሱባታል፤ የምትገርም አካባቢ ትሆናለች/እውነተኛ ትንታኔ ነው/
10. በጀት፣ ድጎማን በፊትሃዊ መንገድ ማለትም አስፈላጊ ቀመር ተሰርቶ ከፈደራል መንግስት ቀጥታ እናገኛለን፤ በራሳችን ቋንቋ የተተረጎሙ ህጎች፣ የቴሊዢን ጣቢያዎች፤ ሲዳማን የሚያስታወቁ ጽሁፎ
11. ሌሎች እጅግ ብዙ ያልተዘረዘሩ አሉ እጅግ በጣም ብዛት ያላቸው ጥቅሞች አሉ
ስለዚህ ለደቂቃ ሠላሚ ትግሎችን ከማካሄድ ጥያቄውን ከሚያካሄዱ አባቶቻችን ጋር በመተባበር እንዲንሰራ የትውልድ አደራ ጥሪ እናቀርባለን፤ እኛ ለአንድት ደቂቃ ስለወደፊቱ ሲዳማ ብቻ በማሰብን ትግሉን እስከ መጨረሻው እልህ አስጨራሽ ትግል ለማካሄድ ስለወሰንን አይዞአችሁ፣ ማንም ከጠየቃችሁ ከላይ የተዘረዘሩ ጥቅሞችን በማስረዳት ግንዛቤ አስጨብጡት!!.......... 
አንቢቡ ሌሎችም እንዲያነቡ አድርጉ
http://www.facebook.com/hagerselam.haroressa


ሃዋሳ ነሃሴ 01/2004/የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በ2005 የትምህርት ዘመን በዶክትሬት ደረጃ የስታቲስቲክስና ማቲማቲካል ሞዴሊንግ የትምህርት ፕሮግራም ለመክፈት መዘጋጀቱን ገለጸ፡፡
ዩኒቨርስቲው የተማሪዎች ቅበላ አቅሙን 30 ሺህ ለማድረስ እየሰራ መሆኑም ተመልክቷል፡፡
የዩኒቨርስቲው የማቲማቲካልና ስታቲስቲክስ ትምህርት ቤት ኃላፊ አቶ ታደለ ተስፉ ትላንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የትምህርት ፕሮግራሙ መከፈት ብቃት ያለው የሰው ሀይል በሚፈለገው መጠንና ጥራት ለማፍራት የላቀ አስተዋጾኦ አለው፡፡
በመሆኑም የትምህርት ፕሮግራሙ መጀመር ከዚህ በፊት የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎችን ወደ ውጪ በመላክ ያወጣው የነበረውን ከፍተኛ ወጭ ያስቀራል ብለዋል፡፡
ፕሮግራሙንም ለመጀመር የመማሪያ ክፍሎች፣ መምህራን፣ መጻህፍትና ለመማር ማስተማሩ ስራ የሚያስፈልጉ ሌሎች የትምህርት ግብአቶች መዘጋጀታቸውን ኃላፊው አስረድተዋል፡፡
ዩኒቨርስቲው በአሁኑ ወቅት በዘርፉ በሁለተኛ ድግሪ 40 ተማሪዎች ተቀብሎ በማስተማር ላይ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡