POWr Social Media Icons

Saturday, July 14, 2012

 ከካላ ደንቦባ ናቲ ጋር የተደረገውን ውይይት ከ6:17 ደቂቃ ጀምረው መከታተል ይችላሉ።ኢሳት ዜና:-በቅርቡ ከሲዳማ ዞን እጣ ፈንታ እንዲሁም አጠቃላይ የፍትህ ጥያቄ ጋር በተያያዘ በአካባቢው የተነሳው ውጥረት መቀጠሉን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ

ባለፈው ሳምንት የግንቦት7 አባላት ናቸው ተብለው የተረጠረጠሩ በርካታ ወጣቶች መያዛቸውን የደቡብ ክልል ዘጋቢያችን የገለጠ ሲሆን፣ የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት የሆኑት አቶ በረከትንና አቶ አባይ ጸሀየን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ ፓርቲዎች በችግሩ ዙሪያ በአዋሳ ከተማ ውይይት እያደረጉ ነው።

የተባበሩት የሲዳማ ፓርቲዎች ለነጻነትና ለፍትህ ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ ደንቦባ ናቲ ለኢሳት እንደተናገሩት የሲዳማ ሽማግሌዎችና የአካባቢው ሰዎች በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት እያደረጉ ሲሆን ተቃውሞው እንደሚቀጥልም አስታውቀዋል::
አቶ ደንቦባ እንዳሉት የሲዳማ የኢህአዴግ አባላት በብዛት አባልነታቸውን እየሰረዙ ነው::