Posts

Showing posts from June, 2012

የአዋሳው እሳት የወያኔ መጥፊያ ይሆናል!!!

Image
ከአስር ዓመታት በፊት “ሲዳማ ክልል ሁና ትደራጅ” የሚል ጥያቄ በማቅረባቸው በአንድ ቀን ውስጥ ከ60 በላይ የሆኑ የአዋሳ ከተማ ነዋሪዎች በአጋዚ ጦር በግፍ ተጨፈጨፉ፤ በመቶዎች የሚቆጠሩ ለአካል ጉዳቶች ተዳረጉ፤ በርካቶች ታሰሩ። ከሰባት ዓመታት በፊት ደግሞ  - በምርጫ 97 ማግሥት – “ድምፃችን ይከበር” በማለታቸው እስካሁን ቁጥራቸው በትክክል የማይታወቅ የአዋሳ ወጣቶች ተገደሉ፤ በርካታ ወጣቶችና አዛውንት ታሰሩ፣ ተደበደቡ፣ ተጋዙ። ዛሬም አዋሳ በውጥረት ውስጥ ነች። የመለስ ዜናዊ ዘረኛ አገዛዝ ሠራዊት እንደለመደው የአዋሳን እና የአካባቢው ነዋሪዎች ሊገድል፣ ሊያቆስል፣ ሊያስር ዘምቷል። ከአዋሳ ወጣ ብላ በምትገኘው አለታ ጭኮ የመለስ ዜናዊ ፓሊሶች ነዋሪዎችን ገድለዋል፤ በርካቶችን አቁስለዋል። ነዋሪዎችም በፓሊሶች ለደረሰባቸው ጥቃት በወሰዱት የመከላከል እርምጃ አንድ ፓሊስ ሕይወቱን አጥቷል። የሚሰማቸው ጆሮ አላገኙም እንጂ ሕዝብን ከሕዝብ በማጣላት ሙያ የተካኑት  የመለስ ካድሬዎች “አዋሳ ከተማ ወደ ፌደራል ትጠቃለል  ያሉት ወላይታዎች ናቸው” እያሉ በማስወራት ላይ ናቸው። መለስ ዜናዊ የፈጠረው ዘርን ብቻ መሠረት ያደረገው “ፌደራሊዝም” በማር የተለወሰ መርዝ መሆኑ ባለፉት ሃያ ዓመታት በተግባር ያየነው ጉዳይ ነው። የመለስ ዜናዊ የውሸት ፌደራሊዝም ከሁሉም የአገራችን ክፍሎች በባሰ የተሳለቀበት “የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት” በሚባለው የአገራችን ክፍል ነው። አዋሳ ደግሞ የዚህ የአቅጣጫ ስያሜ የተሰጠው “መንግሥት” መቀመጫ ናት። አዋሳ እና እሷ የምትወክለው “የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት” የመለስ ዜናዊ ፌደራሊዝም አስከፊ ገጽታ ማሳያዎች ናቸው። በመለስ ዜናዊ ፌደራሊዝም ምክንያት ውቧ አዋሳ የግጭቶች

ኢሳት “ሰበር ዜና” የሲዳማ ወጣቶች “ሲወን” የሚል አዲስ የህቡዕ ድርጅት ዛሬ በአዋሳ መሰረቱ

ሰኔ ፳፫ (ሃያ ሶስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች፣  የግብርና ሰራተኞች፣ መምህራን፣ የክልሉ ፖሊስ ተወካዮች፣ የምክር ቤት አባላትና  እና ሌሎችም ከ 300 በላይ የሚሆኑ ወጣቶች ዛሬ በአዋሳ ከተማ በህቡእ ተሰባስበው የሲዳማ ወጣቶች ንቅናቄ የሚል ድርጅት መስረተዋል። በጉባኤው ላይ ከ22 ወረዳዎች የተውጣጡ የተለያዩ ብሄር ብሄረሰቦች የተወከሉ ወጣቶች የተገኙ ሲሆን፣ የትግል ስትራቴጂያቸውን እና አላማቸውን ለተሰብሳቢው ይፋ አድርገዋል። በከፍተኛ ሚስጢር በተካሄደው ጉባኤ ላይ የወጣቱ አመራሮች የሲዳማ ህዝብ ማንነቱን ለማረጋገጥ የሚያደረገውን ትግል ወጣቶቹ ወደ ፊት ለመግፋት መወሰናቸውን የገለጡ ሲሆን ፣ የመጨረሻ ግባቸው ኢትዮጵያን አሁን ከገባችበት ፈተና ለማላቀቅ ትግል ማድረግ መሆኑን ገልጠዋል። የወጣቶቹ አመራሮች የተለያዩ ብሄረሰብ ተወካዮችን ለመጥራት የተገደዱትም አላማቸው አካባቢያዊ ሳይሆን ብሄራዊ አጀንዳ ያለው መሆኑን ለማሳየት ነው ብለዋል። በጉባኤው ላይ የወላይታ ተወካይ ” እኛ ወንድማማች ህዝብ ነን፤ ኢትዮጵያዊነታችን ይበልጣል፣ ሀይለማርያም ደሳለኝ በሰራው ስህተት ወላይታ በሙሉ በሲዳማ የሚጠላበት እና የምንለያይበት ምክንያት የለም ፣ ሀይለማርያም በምንም አይነት መልኩ ወላይታን አይወክልም፤ ስለዚህ በእርሱ አይን ባታዩን፣ አብረን ብንሰራ ይህችን አገር እናሳድጋለን፣ ከገባችብት ችግር እናወጣለን” ብሎአል። የንቅናቄው አመራሮች “የእኛ ትግል የብሄር ጥያቄ አይደለም ፤ የአማራ፣ የኦሮሞ፣ እና የሌሎች ብሄርና ብሄረሰቦችን ተወካዮችን የጋበዝነውም አላማችን ብሄራዊ መሆኑን ለማሳየት ነው፣ አሁን የሲዳማን ጥያቄ አንስተናል ትግላችን ግን በዚህ አያቆምም፣ አብረን ለኢትዮጵያ ነጻነት እንታገላለን” የሚል መልስ ሰጥተዋል።

ሲዳማ ውስጥ ሰዎች እየተራቡ ነው፡ህጻናት በተመጠጠነ ምግብ እጦት ለተለያዩ በሽታዎች እየተጋለጡ ነው።

ሲዳማ በታሪኩ  የተራበባቸው ግዚያት ብዙም ኣይደለም። ሲዳማ መራብ የጀመረውም ከቅርብ ኣመታት ወዲህ ነው። ሲዳማ ከሚመገበው የምግብ ኣይነት ማለትም እንሴት ካለው ደርቅን የመቋቋም ኣቅም የተነሳ ኢትዮጵያን በተደጋጋሚ የሚያጠቃውና በተለያዩ መዝገቤ ቃላት ለኣገሪቱ እስከ ብያኔ መስጫነት እያገለገለ ያለው ረሃብ ብዙ ጊዜ የሲዳማን ኣካባቢ ኣይዳፈሪም ነበር። ታዲያ ዛሬ ዛሬ ያ ታሪክ ተቀይሮ የሲዳማ ህዝብ እየተራበ እና የውጭ እርዳታ መጠባበቅ መጀመሩ እየተነገረ ነው። ከዛሬ ሰባት እና ስምንት ኣመታታ በፊት የሲዳማ ህጻናት በተለይ በቦርቻና በሽቤዲኖ ወረዳዎች ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ በተመጣጠኔ ምግብ እጦት ለበሽታ ተዳርገው እንደነበር ይታወሳል፤ በወቅቱ ኣለም ኣቀፍ ድርጅቶች ባደረጉት ከፍተኛ ህይወት የመታደግ ርብርብ የበርካታ ህጻናትን ህይወት ለመታደግ ተችሏል። የኣከባቢው ባለስልጣናት ላለፉት ኣስር ኣመታት በኣከባቢው የምግብ ዋስትናን በተመለከተ  ይህ ነው የሚባል ስራ ባለመስራቻቸው  ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ኣካባቢ በድጋሚ በረሃብ መጠቃቱን እና ህጻናትም በተመጠጠነ ምግብ እጥረት ተጠቅተው ወደ እርዳታ  መስጫ ጣቢያዎች በመጉረፍ ላይ መሆናቸውን የተለያዩ ኣለም ኣቀፍ እርዳታ ሰጪ ድርጅቶች በሪፖርታቸው እያመለከቱ ነው። በቦርቻ ወረዳ ህጻናት በተመጣጠኔ ምግብ እጥረት በየትምህርት ቤቶች ተስላፍልፈው እየወደቁ መሆ ናቸው እና የበሰባቸው ደግሞ ወደ ማገገሚባ ጣቢያዎች በመግባት ላይ ናቸው። በየጣቢያዎቹ ህጻናቱን ይዘው የመጡ እናቶች እንደምሉት ከሆነ በኣከባቢው ካለው ድርቅ የተነሳ ልጆ ቻቸውን መመገብ ኣልቻሉም። ወደ ኣካባቢው በኣስቸኳይ የምግብ እርዳታ ካልተላከበሰው ህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ልደርስ እንደምችል ኣለም ኣቀፍ ድርጅቶች በሪፖርታቸው ኣመልክቷል። ሪፖር

Complementary feeding: Patterns and practices in Sidama, Southern Ethiopia

ABSTRACT Complementary feeding is important for healthy growth of infants after 6 months of age. The purpose of the study was to understand the pattern of complementary feeding in the Sidama region of southern Ethiopia. We surveyed mothers about breastfeeding, complementary feeding practices and beliefs, and maternal characteristics. Weight and length of infants were taken and converted to z-scores using WHO software, and hemoglobin was assessed by HemoCue®. Of the 96 infants (age: 9.45 ± .50 months), 18% had a length for age z-score <–3 and 22% had a length z-score between –3 and –2. Males were more likely to be malnourished than females (p=.009). Iron supplements after birth were reported by 82%. All the infants were currently breastfed and 91% of males and 86% of females had received solid foods within the last 24 hours; twice on average. The most commonly fed items were water (82%); corn bread (65%) and animal milk (28%). Less than 2% of infants were given yellow or green ve

ሲዳሙ ዎርባሆ ዎርብማስ ኩሌ ኣይራዳ ጎባሆ

Image
ሲዳሙ ዎርባሆ ዎርብማስ ኩሌ ኣይራዳ ጎባሆ 

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ያቋቋመዉ የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ስርጭቱን ጀመረ

Image
ሃዋሳ ሰኔ 21/2004 የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ ከ2 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ በዋናው ግቢ ያቋቋመው የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ትናንት ተመርቆ ስርጭቱን በይፋ ጀመረ፡፡ የዩኒቨርስቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሴፍ ማሞ የሬዲዮ ጣቢያውን ለአገልግሎት ሲከፍቱ እንደተናገሩት የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያዉን ለማቋቋም የተቻለዉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ባደረገዉ ድጋፍና በዩኒቨርሲቲዉ ጥረት ነዉ ። በአሁኑ ጊዜ የጣቢያዉ የስርጭት አቅም 50 ኪሎ ሜትር ሬዲዬስ የሚሸፍን ሲሆን ወደፊትም ይህንን አድማሱን በማስፋት የተጠቃሚዉን ህብረተሰብ ቁጥር ለማሳደግ እቅድ ተይዟል ብለዋል ። የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ በተለይ የመማር ማስተማሩ ስራ ከምርምር፣ ከዕውቀትና ከቴክኖሎጂ ሽግግር ጋር አያይዞ ለእድገትና ልማት የሚበጁ መረጃዎችን በማስተላለፍ ጠቃሚ አገልግሎት እንደሚሰጥ አስታዉቀዋል ። ህብረተሰቡ በሬዲዮ ጣቢያው ተጠቅሞ ጥያቄ የሚያቀርብበት፣ መረጃ የሚሰጥበት፣ ስራዉን የሚገመግምበት፣ ያሉትን ክፍተቶች የሚጠቁምበት እንደሚሆንም ያላቸዉን እምነት አሳስበዋል ። ዩኒቨርሰቲው በቅርቡ በጋዜጠኝነትና ማስ ኮሙኒኬሽን ለከፈተው አዲስ ፕሮግራም የተግባር መለማመጃ በመሆን ጭምር ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እንዳለው ዶክተር ዮሴፍ አስታዉቀዋል ። በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ተወካይ ሚስተር ሮበርት ፖስት/m.r robert post /በበኩላቸው መንግስታቸው የሀገሪቱን ግብርና፣ ትምህርት፣ ጤና፣ በተለይ ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከልና የእናቶች ጤንነትን ለማጎልበት የሚረዱ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን አስታዉቀዋል። ከዚህም ባሻገር የማህበረሰብ ሬዲዮ ጣቢያ ለማሰፋፋት በሚደረገዉ ጥረት ከአሁን ቀደም ለሀሮማያ ዩኒቨርስቲ አሁን ደግሞ ለሀዋሳ ዩኒቨርስቲ መንግስታቸዉ ድጋፍ ማድረጉን ገልጠዋል። ለወደፊትም የ

The Oromo and Sidama Peoples’ Historical and Neighbourly Relation Cannot Be Dented by the TPLF Plots

Image
OLF and SLF Joint Statement June 29, 2012 The Tigrian Peoples Liberation Front (TPLF) regime has relentlessly pursued the ‘divide and rule’ policy to prolong its grip on power. The regime has initiated conflict between different nations, nationalities and peoples at different times and places, since it came to power, causing destruction of thousands of lives and millions of dollars worth properties. This anti peace and brutal regime, pursuant to its standing policy, has been engaged in overtly and covertly instigating conflict between the Oromo and the Sidama peoples. Accordingly it has managed to instigate conflict in the district of Riimaa Dhaadessaa between the Oromo people in Ajje sub‐zone of Arsi Zone and the Sidama people in Hawasa subzone of Sidama Zone. Loss of lives and property has been reported due to this conflict initiated by the agents of the regime on both sides. The motive of the regime in initiating this conflict is consistent with its hitherto policy else

Ethiopia: Awassa Residents Walked Out Of a High Profile Meeting

27 June 2012 [ESAT] Reports coming to our news desk suggest the political turmoil in the Southern Nations, Nationalities, and Peoples states if far from over. Just yesterday residents of Awassa town who were called for a meeting with the regional state’s president had to walk out on him after he bluntly declared that Sidamas’ struggle for statehood is a wishful thinking. Other ethnicities living in Awassa say ethnic Sidamas have never felt antagonistic towards them. Instead they accuse the regional state government for the political controversy and ethnic tension pervading in the zone and Awassa city. They accuse of the regional government of litany of contradicting laws and what the residents termed unhelpful political propaganda. Passions are running high. One respected senior citizen of ethnic Sidama origin declared on the meeting that the demand for statehood is the most important agenda for Sidamas and the struggle will continue till that last man standing. One activist wh

የጭኮ እና የይርጋለም ህንጻዎች መፈክሮች ተውበው ታዩ፣ መፈክሮችን ለማጥፋት ህንጻዎች እንዲፈርሱ ተደርጓል

ሰኔ ፳፩ (ሃያ አንድ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጭኮና በይርጋለም ከተሞች ዛሬ ጠዋት የታየው ነገር በከተማዋ ታሪክ ታይቶ የማይታወቅ ነው ይላል ዘጋቢያችን።  ሰላም የራቀውና በሀዘን ድባብ ላይ የሚገኘው የከተማው ህዝብ ከቤቱ በጧት ሲወጣ የጠበቀው  እንደ ሰሞኑ ፍርሀትና ጭንቀት ሳይሆን ደስታና ተስፋ ነበር።  በከተማዋ የሚገኙ ህንጻዎች  ሁሉም በሚባል ደረጃ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ሌሊቱን በሙሉ  በደማቅ ቀለማት ሲሸለሙ አድረዋል። ህዝቡም በግድግዳዎቹ ላይ የተጻፉትን መፈክሮች ለማየት እየተደዋዋለ ወደ አደባባዩ ጎረፈ። የሚይዙት የጠፋቸው የመንግስት ባለስልጣናት እና ፖሊሶች መፈክሮችን በውሀ ለማጥፋት ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም። ተስፋ በቆረጠ ስሜትም ጽሁፎችን ለማጥፋት የፊት ግድግዳዎች መፍረስ እንደገና መልሰውም በስሚንቶ መለሰን ነበረባቸው። ፖሊሶች የህንጻ መቦርቦሪያ ማሽኖች እየያዙ በየህንጻዎች ላይ በመውጣት ሲቦረቡሩ ፣ ሲለስኑ የከተማው ህዝብም በፖሊሶች ድርጊት ይዝናና ነበር። ከ 10 በላይ መፈክሮች በከተማዋ አስፓልት ላይም ተጽፈው ነበር። ፖሊሶችም መኪኖችን አስቁመው አስፓልቱን በጋዝ ሲወለውሉ ውለዋል። ዘጋቢያችን በጭኮ ወረዳ በግድግዳዎች ላይ ከተጻፉት መፈክሮች መካከል የተወሰኑት እንደሚገኙበት ገልጧል።፡” በጭኮ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ላይ ” ሽፈራው ሽጉጤ የሲዳማን ህዝብ አይወክልም፣ የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ይመለስ፣ ጥያቄያችን ሳይመለስ ትግላችን አይቋረጥም” ይላል። ከተማ መሀከል ከተጻፉ መፈክሮች መካከል ” የሲዳማ ህዝብ ጥያቄ ይመለስ ” የሚል ተጽፎአል። በከተማዋ መናሀሪያ ላይ ደግሞ ” አዋሳና ሲዳማ አይነጣጠሉም “፣   የኢህአዴግ ካድሬዎች የሲዳማን ህዝብ ደም ማፍሰስ ያቁሙ፣ የሲዳማ ተወላጆች የወገኖቻቸውን ደም ማፍሰስ ያቁሙ፣ ሲ

በስብሰባው ላይ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በሲዳማ ተወላጆችና በሌሎች ነዋሪዎች መካከል ልዩነት በመፍጠር ግጭት እንዲፈጠር ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካለቸውም ተባለ

በአዋሳ ከተማ በተደረገው ስብሰባ ህዝቡ ስብሰባውን ረግጦ ወጣ ሰኔ ፳ (ሃያ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በትናንትናው እለት የክልሉ መስተዳደር ሀላፊ የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ የአዋሳ ከተማ ነዋሪዎችን በአዋሳ ባህል አዳራሽ ውስጥ በሰበሰቡት ወቅት ነው ውዝግቡ የተፈጠረው። አቶ ሽፈራው ” ሲዳማ ክልል እንዲሆን የጠየቃችሁት መቼውንም አይሳካም ቁርጡን እወቁት ” በማለት ሲናገሩ ተሰብሳቢው ተቃውሞውን ገልጧል። በአዋሳ ተወልደው የኖሩ የሲዳማ ብሄረሰብ ተወላጅ ያልሆኑ የከተማው ነዋሪዎች ” እኛን የሲዳማ ህዝብ አላጠቃንም፣ ሲዳማ እኛን አይጠላንም፣ እኛን እያስጠቃን ያለው አመራሩ የሚያወጣው ህግ ነው፣ እኛ ተከባብረን፣ ተዋልደን የምንኖር ህዝብ ነን” በማለት አስተያየት ሲሰጡ፣ ከሲዳማ ተወላጆች በስተቀር የሌላ አካባቢ ተወላጆች አዳራሹን ለቀው እንዲወጡ አቶ ሽፈራው ሲናገሩ ነው፣ ውዝግቡ የተፈጠረው። የከተማው ነዋሪዎችም እኛ የትም አንሄድም፣ ብትፈልጉ እንደ ጓደኞቻችን እዚሁ እሰሩን በማለት ሲቃወሙ ከዋሉ በሁዋላ አንድ ሽማግሌ ” ህዝቡ አልቆ ሲዳማ የሚለው ስም እሲኪሰረዝ ድረስ ትግላችንን አናቆምም፣ ጥያቄያችን እስኪመለስ ድረስ” በማለት ተናግረው አዳራሹን ለቀው ሲወጡ፣ ህዝቡም ተከትሎአቸው ወጥቷል። በስብሰባው ላይ አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በሲዳማ ተወላጆችና በሌሎች ነዋሪዎች መካከል ልዩነት በመፍጠር ግጭት እንዲፈጠር ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም አልተሳካለቸውም ሲል በአዳራሹ የተገኘው ዘጋቢያችን ገልጧል። ህዝቡም በግልጽ ከሌሎች ወንድሞቻችን ጋር ልታጋጩን አትሞክሩ በማለት ተቃውሞውን አሰምቷል። በቡድን የተደራጁት የአዋሳ ወጣቶች ህዝቡን እያስመቱ የሚገኙ የመንግስት ባለስልጣናት የሚል በርካታ ስም ዝርዝሮችን የያዙ ወረቀቶችን እየበተኑ ነው። የዩኒቨርስቲ ተማሪ

The Sidama people are surrounded and forced not to move about by the Special Forces which are currently granted shoot to kill authority by the government. The Woredas such as Aleta Wondo, Yirgalem, Bensa, Harbegona, Chuko, Arroresa, etc are facing harsh treatments by the Special Forces.

The Second Round Massacre of Sidama People by Prime Minister Meles Zenawi and Deputy Prime Minister Hailemariam Desalegn of Ethiopia 26 June 2012 1.  YET ANOTHER Massacre of Sidama people of Ethiopia BY MELES ZENAWI AND HAILEMARIAM DESALEGN has begun. The second round of the massacre of innocent people of Sidama in Ethiopia started a week ago.  However, the first massacre of about 100 innocent people of Sidama took place at a village called Loqqe in Hawassa at about midday on Friday 24 th  May 2002.  The killing of Sidama people went on throughout the day and the bodies were dumped at Hawassa Health Centre compound and the Police station.  Other bodies were collected from the maize plot in Hawassa.  The main architects of the massacre were Bereket Simon and Hailemariam Desalegn with direct instruction and approval by Meles Zenawi. The following personalities took the pleasure of finalising and authorising the massacre of Sidama people on that day, 10 years ago: Bereket Simo

የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ አሁን የተነሣ ሳይሆን ለዓመታት ሲታገልለት የቆየ መሆኑን የሲዳማ አርነት ንቅናቄ አስታወቀ፡፡

Image
ኢሕአዴግ በ1984 ዓ.ም አምስት የነበሩትን ክልሎች ወደ አንድ በማምጣት አሁን ደቡብ የሚባለውን ክልል የፈጠረበት ሁኔታም ድንገተኛና የሚመለከታቸው ያልመከሩበት ነው ሲሉ የክልሉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ተችተዋል፡፡ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ - ሲአን ለሰጠው መግለጫ መነሻ የሆነው የሃዋሣ ከተማን ዕጣ ፈንታ አስመልክቶ በክልሉ ገዥ ፓርቲ ለውይይት ቀረበ የተባለው ሠነድ ነው፡፡ ሜትሮፖሊታን ከተማችንን እንዴት እንምራው በሚል ርዕስ የተዘጋጀው ሠነድ ከግንቦት 27 ቀን 2004 ዓ.ም ጀምሮ ለውይይት መቅረቡን ፓርቲው አስታውቋል፡፡ ሠነዱ ለውይይት የቀረበውም ለሲዳማና ለሃዋሣ ከተማ አስተዳደር የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት እንዲሁም ለሲዳማ ተወላጅ የደኢሕዴን አባላት መሆኑን ጠቅሷል፡፡ ሠነዱ ሃዋሣ በተለያዩ ብሔረሰቦች ስብጥር እንድትተዳደር የሚጠይቅ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡ ይህንን ሠነድ አጥብቆ እንደሚቃወመው የገለፀው ሲአን የዞኑ ተወላጆችም ይቃወሙታል ባይ ነው፡፡ ፓርቲው በዚሁ መግለጫ የሲዳማ ሕዝብ “ክልል የመሆን ጥያቄ”ም ሊመለስ ይገባል ሲልም አሣስቧል፡፡ የሃዋሣው ሠነድ ጉዳይ ወቅታዊ ይሁን እንጂ የሲዳማ ክልል የመሆን ጥያቄ በተደጋጋሚ የተነሣና ሲታገልለት የቆየ መሆኑንም ሲአን አስታውቋል፡፡ ዝርዝሩን ያዳምጡ፡፡ ሜትሮፖሊታን ሃዋሣ እና “ክልል” ሲዳማ እያነጋገሩ ነው

በሲዳማ ዞን ጭኮ ወረዳ የተነሳው ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው

Image
ሰኔ ፲፱ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት የወረዳው የመረጃ ምንጭ እንደገለጠው ተቃውሞው የተነሳው ዛሬ 4 ሰአት ላይ ነው። በትናንትናው እለት እንደዘገብነው የካናዳ ጉብኝታቸውን አቋርጠው ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱት የደቡብ ክልል ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በቅርቡ በሲዳማ ዞን የተነሳውን ተቃውሞ ያነሳሱት ባለሀብቶችና ተቃዋሚዎች ናቸው በማለት የተናገሩትን ለመቃወም ነበር ዛሬ ሰለማዊ ሰልፉ የተጠራው። አቶ ሽፈራው ያደረጉትን ንግግር ያስቆጣቸው የጭኮ ወረዳ ነዋሪዎች በተወካዮቻቸው አማካኝነት ሰለማዋዊ ሰልፍ ለማድረግ እንዲፈቀድላቸው ጥያቄያቸውን ወረዳው አስተዳዳሪ ለሆኑት ለአቶ አሻግሬ ጀምበሬ ደብዳቤ አስገብተው ነበር። በዚህም መሰረት ዛሬ ጧት የተቃውሞ ሰልፉን ለማካሄድ ወደ ስታዲየሙ ሲያቀኑ የወረዳው የጸጥታ ዘርፍ ሀላፊ የሆኑት አቶ አለማየሁ ክፍሌ የፌደራል ፖሊስ በመጥራት የህዝቡ መሪዎች እንዲያዙ አድርገዋል። የከተማው ነዋሪ ተወካዮችን ለማስለቀቅ ከፌደራል ፖሊስ አባላት ጋር ውዝግብ ውስጥ መግባቱን ተከትሎ፣ ፖሊሶች ለተቃውሞ የመጣውን ሰላማዊ ሰው በቆመጥ እየደበደቡ ለመበትን ሲሞክሩ ቆይተዋል። ከሰአት በሁዋላ የከተማው ህዝብ በነቂስ በመውጣት የታሰሩት መሪዎች እንዲፈቱለት ፖሊስ ጣቢያውን በመክበብ ጥያቄውን አቅርቧል። ስቱዲዮ እስከገባንበት ጊዜ ድረስ ህዝቡ የፖሊስ ጣቢያውን እንደከበበ ነበር። ህዝቡን ውስጥ ለውስጥ ለአመጽ እንዲነሳ አድርገዋል በሚል የወረዳው ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ዘላለም ላላም ታስረዋል። እንዲሁም ከመንግስት ሰራተኞች መካከል አቶ ገረመው ፊሳ፣ አቶ ኤፍሬም ተፈራ፣ ኢዛ እንዳለና ንጉሴ ታደሰ የታሰሩ ሲሆን፣ ባለሀብቱ አቶ አስቻለው በቀለም ታስረዋል። አቶ ገረመው ፊሳ፣ አቶ ኤፍሬም ተፈራ፣ አቶ

ደቡብ ኢትዮጵያ የሚኖረዉ የሲዳማ ብሔረሰብ እራሱን የቻለ መስተዳድር እንዲሰጠዉ ሰሞኑን በተከታታይ ባደረገዉ ሠላማዊ ሠልፍ ጠየቀ

Image
የሲዳማ አርነት ንቅናቄ እንዳስታወቀዉ የሕዝቡ ጥያቄ ሠላማዊና የሕገ-መንግሥቱን ድንጋጌዎች የጠበቀ ነዉ።በሌላ በኩል የደቡብ ኢትዮጵያ መስተዳድርን ከኦሮሚያ መስተዳድር ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች በተከሰተ ግጭት ሰዎች መሞት፥ መቁሰላቸዉ ተነግሯል። ደቡብ ኢትዮጵያ የሚኖረዉ የሲዳማ ብሔረሰብ እራሱን የቻለ መስተዳድር እንዲሰጠዉ ሰሞኑን በተከታታይ ባደረገዉ ሠላማዊ ሠልፍ ጠየቀ።በደቡብ ኢትዮጵያ ርዕሠ-ከተማ በአዋሳና በአካባቢዉ ከተሞች አደባባይ የወጣዉን ሕዝብ ለመቆጣጠር መንግሥት በርካታ ፀጥታ አስከባሪዎች አስፍሯል።የሲዳማ አርነት ንቅናቄ እንዳስታወቀዉ የሕዝቡ ጥያቄ ሠላማዊና የሕገ-መንግሥቱን ድንጋጌዎች የጠበቀ ነዉ።በሌላ በኩል የደቡብ ኢትዮጵያ መስተዳድርን ከኦሮሚያ መስተዳድር ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች በተከሰተ ግጭት ሰዎች መሞት፥ መቁሰላቸዉ ተነግሯል።ወኪላችን ታደሰ እንግዳዉ ከአዲስ አበባ ሁኔታዉን ተከታትሎታል። ሙሉ ዘጋባውን በሚቀጥለው ሊንክ ያዳምጡ ሠላማዊ ሠልፍና ግጭት በደቡብ ኢትዮጵያ

በመላው ኣለም ላይ የሚገኙ የሲዳማ ዳይስፖራ በሲዳማ ዞን ውስጥ እየተካሄደ ያለውን ህዝባዊ ንቅናቄ በንቃት በመከታተል እና በመደገፍ ላይ መሆናቸውን ገለጹ።

የዳይስፖራው ተወካዮች ለሲዳማ ወራንቻ የኢንፎርሜሽን ማእከል በላኩት መልእክት እንዳስታወቁት፤ የሲዳማ ህዝብ ያነሳቸውን የመልካም ኣስተዳደር እና የክልል ጥያቄዎችን ይደግፋሉ ለተግባራዊነቱም ከዞኑ ህዝብ ጎን ይቆማሉ። በሰሜን ኣሜሪካ፡ በታላቋ ብርታኒያ፡ በኖርዌይ፡ በኔዘርላንድ፡ በመካከላኛው ኣውሮፓ ኣገራት፡ በህንድ፡ በሳውድ ኣረቢያ እና ደቡብ ኣፍሪካ ነዋሪ የሆኑት የዞኑ ዳይስፖራ ኣባላት ህዝባዊ ንቅናቄውን በቅርበት በመከታተል ላይ መሆናቸውን ኣስታውቀዋል። ህዝባዊ ንቅናቄው ከተጀመረበት ጊዜ ጀምሮ በንቅናቄው ላይ የኣለም ህዝብ ትክክለኛ ግንዛቤ እንዲኖረው በተለያዩ የዜና ኣውታሮች የሚቀርቡ ዘገባዎች ከህዝባዊው ንቅናቄ ኣላማዎች ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ የማደረግ ስራ በመስራት ላይ መሆናቸውን ኣስረድታዋል። ኣያይዘውም ለህዝባዊ ንቅናቄ መሳካት ኣስፈላጊውን ደጋፍ ለማደረግ ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ባለፈው ሳምንት በሲዳማ ዞን የተነሳው ተቃውሞ ወደ ዘር ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚለው የኢሳት ዘገባ የሲዳማ ተወላጆች ያነሱትን ዋነኛ ጥያቄ ያልዳሰሰ ነው በማለት የሲዳማ ተወላጆች አስተያየቶቻቸውን ልከዋል።

Image
ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት ከአዋሳ እና ከሲዳማ ዞን ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በካናዳ ትምህርታዊ ጉብኝት ሲያደርጉ የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጉብኝታቸውን ትተው በመመለስ ትናንት መግለጫ ሰጥተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት በሲዳማ ዞን የተነሳው ተቃውሞ ወደ ዘር ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚለው የኢሳት ዘገባ የሲዳማ ተወላጆች ያነሱትን ዋነኛ ጥያቄ ያልዳሰሰ ነው በማለት የሲዳማ ተወላጆች አስተያየቶቻቸውን ልከዋል። አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በአዋሳ ጉዳይ ለተነሳው ተቃውሞና ለጠፋው የሰው ህይወት ችግሩን የቀሰቀሱትን ለፍርድ እንደሚያቀርቡ ለክልሉ ራዲዮ ተናግረዋል። አቶ ሽፈራው የአዋሳ ጉዳይ በሀሳብ ደረጃ ተነሳ እንጅ ውሳኔ ያልተሰጠበት በመሆኑ ህዝቡ እንዲረጋጋ ጠይቀዋል። ከህዝቡና ፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሚመለከታቸው ሰዎች ጋር በመሆን ጉዳዩን እንደሚያብላሉትም ገልጠዋል። ፕሬዚዳንቱ ሰሞኑነ በተነሳው ግጭት የሰው ህይወት መጥፋቱንና ንብረት መውደሙን ቢገልጡም ሀላፊነቱን ለመውሰድና ይቅርታ ለመጠየቅ አልሞከሩም፣ ይልቁንም ችግሩን የፈጠሩት የተቃዋሚ አባላት ፓርቲና አንዳንድ ባለሀብቶች መሆናቸውን በመግለጥ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት። ሌሎች ወገኖች ግን ግጭቱን የቀሰቀሱት የደኢህዴግ ኢህአዴግ አባላት ናቸው:: አዋሳ አሁንም በፌደራል ፖሊስ እየተጠበቀች ነው። ወደ ይርጋለም በሚወስደው መንገድ ላይ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ የፌደራል ፖሊስ አባላት ሰፍረው ይገኛሉ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት በሲዳማ ዞን የተነሳው ተቃውሞ ወደ ዘር ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚለው የኢሳት ዘገባ የሲዳማ ተወላጆች ያነሱትን ዋነኛ ጥያቄ ያልዳሰሰ ነው በማለት

Freedom

Image

የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች የተለያዩ ፖለቲካዊ ጥያቄዎቻቸውን ለምመለከተው መንግስታዊ ኣካል በሰላማዊ መንገድ ለማቅረብ እንዲያስችላቸው በየወረዳዎች ደረጃ የሚወክሏቸውን ተወካዮች በመምረጥ ላይ ሲሆኑ፤ የክልል ባለስልጣናት በበኩላቸው ህዝብ እንዲረጋጋ በመጠየቅ ላይ ናቸው::

በየኣስር ኣመቱ በክልል ባለስልጣናት እየረቀቀ የሚቀርበውን የሃዋሳን ከተማ በኮታ የማስተዳደር ጥያቄ ለኣንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንዲያገኝ ታስቦ የተጀመረውን የክልል ጥያቄ ከዳር ለማድረስ የተቀጣጠለው ህዝባዊ ንቅናቄ እንደቀጠለ ሲሆን: የሲዳማ ህዝብ ያሉትን የመልካም ኣስተዳደር ችግሮን እና የክልል ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ለሚመለከተው መንግስታዊ ኣካል ለማቀረብ እንቅስቃሴ ጀምሯል:: የበንሳ ወረዳ የህዝብ ንቅናቄ ኣባላት የወረዳው ህዝብ በመወከል ህዝባዊ ጥያቄዎችን የሚያቀረቡ ሽማግሌ ተወካዮቻቸውን የመረጡ ሲሆን ሌሎች የዞኑ ወረዳዎችም የባንሳ ወረዳ ኣረኣያ በመከተል ተወካዮቻቸውን በመምረጥ ላይ መሆናቸው ተገልጿል:: ሰሞኑን በዞኑ ኣስተዳዳሪ የተመራው ኣንድ ከሲዳማ ዞን እና ከክልል ቢሮዎች የተወጣጣ የሲዳማ ልኡካን ቡድን ወደ ኣዲስ ኣበባ ኣቅንቶ የተመለስ ሲሆን በዛሬው ቀን ሙሉ ቀኑን የዞን ካቢኔዎች ስብሰባ ላይ በመሆናቸው ተጓዧቹ ከፈዴራል መንግስት ባለስጣናት የተሰጣቸውን ምላሽ ለመስማት ኣልተቻለም:: ሆኖም ለቀረቡት ጥያቄዎች የፈዴራል መንግስት ኣጥጋቢ ምላሽ ሳይሰጥ እንዳልቀረ ከውስጥ ኣዋቅ ምንጮች ያገኝናቸው መረጃዎች ያሳያሉ::   በዛሬው እለት መላዋ ሲዳማ በተለይ የሃዋሳ ከተማ ምንም እንኳን በከፍተኛ ጥበቃ ስር ያለ ቢሆንም በከተማዋ ጸጥ ረጭ ብለው የነበሩ ንግድና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ወደ ቀደሞው እየተመለሱ መሆናቸው ተገልጿል::  በሌላ በኩል የክልሉ ፕሬዚዴንት ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከክልሉ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ህዝቡ እንዲረጋጋ መልእክት ያስተላላፉ ሲሆን፤ በደኢህዴን ተዘጋጅቶ ወሳኔ ሳይሰጥበት በድንገት ወደ ህዝብ ጆሮ የደረሰው እና ለተፈጠረው ህዝባዊ ንቅናቄ መሰረት የሆነው ጽሁፍ “በሬ ወለደ ወሬ”

የሲዳማ ዳይስፖራ በማወያያ ጽሁፉ ላይ የሰላ ሂስ ኣቀረበ

ሜትሮፖሊታን ከተማችንን እንዴት እንምራው? በሚል የደኢህዴን ስራ ኣስፈጻም ኮሚቴ በተዘጋጀው የማወያያ ጽሁፍ ላይ ከተላያዩ ኣካላት እየቀረበ ያለው ትችት ተፋፉሞ ቀጥሏል፡፡የሲዳማ ዳይስፖራ በማወያያ ጽሁፉ ላይ የሰላ ሂስ ኣቅርቧል። በኣቀረበው ሂስ ላይ የማወያያ ጽሁፉን ከተለያየ ጎን የተመለከተው ሲሆን፤ ከስያሜው ጀምሮ በጽሁፉ ውስጥ የተነሱ እና ትኩረት የተሰጣቸውን ጽንስ ሀሳቦች ገምግመዋል። ''The Sidama leadership that ensured that Hawassa grew faster than any other towns in the country during the past 20 years is regarded as having no political commitment and capacity to deliver these all of the sudden! Another blatant fallacy!''   ከጽሁፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ::  የማወያያ ጽሁፉ እና የዳይስፖራውን ሂስ በሚቀጥለው ሊንክ ይመልከቱ። ደኢህዴን በሃዋሳ ከተማ እጣ ፋንታ ላይ በየደረጃው ያሉት ኣመራሮች ለማወያያት ያዘጋጁት ባላ 15 ገጽ የማወያያ ጽሁፍ Ethiopia Regime Manfesto Uprooting Sidama From City

የሜትሮፖሊታን ከተማችንን እንዴት እንምራው? በሚል የደኢህዴን ስራ ኣስፈጻም ኮሚቴ በሃዋሳ ከተማ የወደፊት እጣ ፋንታ ላይ በየደረጃው ካሉት ከሚመለከታቸው ኣመራሮች ጋር ውይይት ለማድረግ ኣዘጋጅቶት በነበረው በለ 15 ገጽ የማወያያ ጽሁፍ ላይ ትችት ቀረበ:: የማወያያ ጽሁፉ የሲዳማ ህዝብ ማህበራዊ፤ኢኮኖሚያዊ እና ባህላዊ እሴቶቹን የሚያንቋሽሽ እና ስራ ኣስፈጻሚ ኮሚቴ ለ ህዝቡ ያለውን ንቀት የሚያሳይ መሆኑ ተገለጸ::

የሲዳማ ምሁራን የማወያያ ጽሁፉን በተመለከተ በተለያዩ ማህበራዊ መረቦች ላይ ያቀረቡት ትችት እንደምያመለክተው፡ በደኢህዴን ስራ ኣስፋጻሚ ኮሚቴ የተዘጋጀው የማወያያ ጽሁፍ የሃዋሳ ከተማ በጥቂት ኣመታት ውስጥ ያሳየችው እድገት በሲዳማ ኣስተዳደር ብቃት መሆኑን የ ሚ ክድ፤ የሲዳማን ህዝብ እንግዳ ተቀባይነትን ከግምት ውስጥ ያላስገባና በጭፍን የሲዳማን ህዝብ የሚያጥላላ ነው ብለዋል :: በማወያያ ጽሁፉ ላይ የቀረበውን ሙሉ ትችት እንደምከተለው ኣቅርበናል :: ሲዳማ ከዘመነ አፄ ምኒልክ እስከ ደኢህዴን/ኢህአዴግ የአፄ ምኒልክ ተዋጊ ኃይል የሲዳማን ህዝብ በአስከፊ ጭቆናና ብዝበዛ ስር ለማስተዳደር ባካሄደው ወረራ በወቅቱ ይጠቀምበት የነበረውን የጦር መሳሪያ ከህዝቡ ስነ-ልቦናዊ ዝግጅት አንጻር የማይጣጣም በመሆኑ የሲዳማን ህዝብ በግፍ እየጨፈጨፈ እስከ ደቡባዊ አገር ድረስ መዝለቁ አልቀረም፡፡ በወቅቱ ያደረሰው ብዝበዛና ጭቆና የህዝባችንን ሰብዓዊ ክብር ያዋረደና ነፃነቱን ያሳጣ በመሆኑ የሲዳማ ህዝብ በቡድንና በተናጥል ባልተደራጀ ሁኔታም ቢሆን ከምኒልክ ወረራ ጀምሮ እስከ አፄ ኃይለስላሴ ውድቀት ድረስ ለማንነቱና ለሰብዓዊ ክብሩ ያደረጋቸው የነፃነት ተጋድሎዎች ለታሪክ የሚዘከሩ ናቸው፡፡ በተለያየ መንገድ ፈርጀ ብዙ የሆኑ የፀረ ነፍጠኛ ወይንም መልከኛ ትግል እስከ ደርግ መንግስት ቀጥሎ የመልከኛ ስርዓት ተወገደ፡፡ እንደማንኛውም ነፃነት ፈላጊና ገባሪ ብሔሮች ሁሉ የሲዳማ ሕዝብ የተቀማውን የመሬት ባለቤትነት መብት አገኘ፡፡ ቀጣይ የማንነትና የዴሞክራሲያዊ መብት ጥያቄዎች ባይመለሱለትም የሲዳማ ሕዝብ ከ70 ዓመታት በፊት ከአባቶቹ እጅ የተነጠቀውን መሬት መልሶ በማግኘት ለአጭር ጊዜም ቢሆን እፎይታ ያገኘ መስሎ ቢታይም ሰው በላው የወቅቱ መንግሥት ግን በር