POWr Social Media Icons

Monday, June 25, 2012ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት ከአዋሳ እና ከሲዳማ ዞን ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በካናዳ ትምህርታዊ ጉብኝት ሲያደርጉ የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጉብኝታቸውን ትተው በመመለስ ትናንት መግለጫ ሰጥተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት በሲዳማ ዞን የተነሳው ተቃውሞ ወደ ዘር ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚለው የኢሳት ዘገባ የሲዳማ ተወላጆች ያነሱትን ዋነኛ ጥያቄ ያልዳሰሰ ነው በማለት የሲዳማ ተወላጆች አስተያየቶቻቸውን ልከዋል።

አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በአዋሳ ጉዳይ ለተነሳው ተቃውሞና ለጠፋው የሰው ህይወት ችግሩን የቀሰቀሱትን ለፍርድ እንደሚያቀርቡ ለክልሉ ራዲዮ ተናግረዋል።

አቶ ሽፈራው የአዋሳ ጉዳይ በሀሳብ ደረጃ ተነሳ እንጅ ውሳኔ ያልተሰጠበት በመሆኑ ህዝቡ እንዲረጋጋ ጠይቀዋል። ከህዝቡና ፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሚመለከታቸው ሰዎች ጋር በመሆን ጉዳዩን እንደሚያብላሉትም ገልጠዋል። ፕሬዚዳንቱ ሰሞኑነ በተነሳው ግጭት የሰው ህይወት መጥፋቱንና ንብረት መውደሙን ቢገልጡም ሀላፊነቱን ለመውሰድና ይቅርታ ለመጠየቅ አልሞከሩም፣ ይልቁንም ችግሩን የፈጠሩት የተቃዋሚ አባላት ፓርቲና አንዳንድ ባለሀብቶች መሆናቸውን በመግለጥ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት። ሌሎች ወገኖች ግን ግጭቱን የቀሰቀሱት የደኢህዴግ ኢህአዴግ አባላት ናቸው::

አዋሳ አሁንም በፌደራል ፖሊስ እየተጠበቀች ነው። ወደ ይርጋለም በሚወስደው መንገድ ላይ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ የፌደራል ፖሊስ አባላት ሰፍረው ይገኛሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት በሲዳማ ዞን የተነሳው ተቃውሞ ወደ ዘር ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚለው የኢሳት ዘገባ የሲዳማ ተወላጆች ያነሱትን ዋነኛ ጥያቄ ያልዳሰሰ ነው በማለት የሲዳማ ተወላጆች አስተያየቶቻቸውን ልከዋል። ለጉዳዩ ቅርበት አለን የሚሉ ወገኖች ለኢሳት በላኩት መልእክት የአዋሳ ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄ የፍትህ ጥያቄ በመሆኑ በሌሎች አካባቢዎች ከሚነሱት ጥያቄዎች የተለየ አይደለም።


በየኣስር ኣመቱ በክልል ባለስልጣናት እየረቀቀ የሚቀርበውን የሃዋሳን ከተማ በኮታ የማስተዳደር ጥያቄ ለኣንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንዲያገኝ ታስቦ የተጀመረውን የክልል ጥያቄ ከዳር ለማድረስ የተቀጣጠለው ህዝባዊ ንቅናቄ እንደቀጠለ ሲሆን: የሲዳማ ህዝብ ያሉትን የመልካም ኣስተዳደር ችግሮን እና የክልል ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ለሚመለከተው መንግስታዊ ኣካል ለማቀረብ እንቅስቃሴ ጀምሯል::

የበንሳ ወረዳ የህዝብ ንቅናቄ ኣባላት የወረዳው ህዝብ በመወከል ህዝባዊ ጥያቄዎችን የሚያቀረቡ ሽማግሌ ተወካዮቻቸውን የመረጡ ሲሆን ሌሎች የዞኑ ወረዳዎችም የባንሳ ወረዳ ኣረኣያ በመከተል ተወካዮቻቸውን በመምረጥ ላይ መሆናቸው ተገልጿል::

ሰሞኑን በዞኑ ኣስተዳዳሪ የተመራው ኣንድ ከሲዳማ ዞን እና ከክልል ቢሮዎች የተወጣጣ የሲዳማ ልኡካን ቡድን ወደ ኣዲስ ኣበባ ኣቅንቶ የተመለስ ሲሆን በዛሬው ቀን ሙሉ ቀኑን የዞን ካቢኔዎች ስብሰባ ላይ በመሆናቸው ተጓዧቹ ከፈዴራል መንግስት ባለስጣናት የተሰጣቸውን ምላሽ ለመስማት ኣልተቻለም:: ሆኖም ለቀረቡት ጥያቄዎች የፈዴራል መንግስት ኣጥጋቢ ምላሽ ሳይሰጥ እንዳልቀረ ከውስጥ ኣዋቅ ምንጮች ያገኝናቸው መረጃዎች ያሳያሉ::  

በዛሬው እለት መላዋ ሲዳማ በተለይ የሃዋሳ ከተማ ምንም እንኳን በከፍተኛ ጥበቃ ስር ያለ ቢሆንም በከተማዋ ጸጥ ረጭ ብለው የነበሩ ንግድና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ወደ ቀደሞው እየተመለሱ መሆናቸው ተገልጿል:: 

በሌላ በኩል የክልሉ ፕሬዚዴንት ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከክልሉ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ህዝቡ እንዲረጋጋ መልእክት ያስተላላፉ ሲሆን፤ በደኢህዴን ተዘጋጅቶ ወሳኔ ሳይሰጥበት በድንገት ወደ ህዝብ ጆሮ የደረሰው እና ለተፈጠረው ህዝባዊ ንቅናቄ መሰረት የሆነው ጽሁፍ “በሬ ወለደ ወሬ” ነው በማለት ኣጣጥለውታል::

የራሳቸው ሰዎች ያዘጋጁት እና በብዙ ኮፒዎች ተዛዝተው ከህዝብ እጅ የገባው ባለ 15 ገጽ የማወያያ ጽሁፍ እንዴት ሆኖ በሬ ወለደ ወሬ ልሆን እንደቻለ ብዙም ያሉት ነገር ባይኖርም፤ የማወያያ ጽሁፉን መሰረት ተደርጎ የሚወሰድ ወሳኔ እንደሌለ ግን ተናግረዋል::

በተጨማሪም የሲዳማ ህዝብ እንግዳ ተቀባይ እና ከሌሎች ብሄርና ብሄረሰቦች ጋር ለብዙ ኣመታት በሰላም የኖረ ህዝብ መሆኑን ግልጸው በሲዳማና በሌላው ህዝብ መካከል ግጭት ለመፍጠር ኣሉባልታ የምያናፍሱትን ነቅፈዋል:: 

ኣክለውም በሲዳማ ህዝብ የተነሱትን የተለያዩ የመልካም ኣስተዳደር ጥያቄዎች ለማስተናገድ ዝግጁ መሆናቸውን ኣስታውቀዋል::  
    


ሜትሮፖሊታን ከተማችንን እንዴት እንምራው? በሚል የደኢህዴን ስራ ኣስፈጻም ኮሚቴ በተዘጋጀው የማወያያ ጽሁፍ ላይ ከተላያዩ ኣካላት እየቀረበ ያለው ትችት ተፋፉሞ ቀጥሏል፡፡የሲዳማ ዳይስፖራ በማወያያ ጽሁፉ ላይ የሰላ ሂስ ኣቅርቧል።

በኣቀረበው ሂስ ላይ የማወያያ ጽሁፉን ከተለያየ ጎን የተመለከተው ሲሆን፤ ከስያሜው ጀምሮ በጽሁፉ ውስጥ የተነሱ እና ትኩረት የተሰጣቸውን ጽንስ ሀሳቦች ገምግመዋል።

''The Sidama leadership that ensured that Hawassa grew faster than any other towns in the country during the past 20 years is regarded as having no political commitment and capacity to deliver these all of the sudden! Another blatant fallacy!''  ከጽሁፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ::

 የማወያያ ጽሁፉ እና የዳይስፖራውን ሂስ በሚቀጥለው ሊንክ ይመልከቱ።
ደኢህዴን በሃዋሳ ከተማ እጣ ፋንታ ላይ በየደረጃው ያሉት ኣመራሮች ለማወያያት ያዘጋጁት ባላ 15 ገጽ የማወያያ ጽሁፍ
Ethiopia Regime Manfesto Uprooting Sidama From City