POWr Social Media Icons

Tuesday, May 22, 2012


መ/ር ቀለሙ ሁነኛው
Kelemhun@yahoo.com
አቶ ኃ/ማርያም የገፅታዎ ወዘና ሲታይ በእውነቱ
ወንበሩ የተመችዎት ይመስላል፡፡ እነ አቶ መለስ ደደቢት
በረሀ መሽገው ሲዋጉም ሆነ ደርግን ድል አርገው
ቤተመንግስት ሲገቡ ርስዎ በትግል ማህፀን ውስጥ
አልተፀነሱም ነበር፡፡ ከወቅቱ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ርቀው
ባህር ማዶ በትምህርት ላይ እንደነበሩ ወዳጄ ተመስገን
በፍትህ ጋዜጣ ላይ አስነብቦናል፡፡ መቼም እደለኛ ነዎት
ይህም ከዕድል ከተቆጠረ፤ ህወሓት /ኢህአዴግ ሕዝብን
በብሔረሰብ ከፋፍሎ የመግዛት ፖሊሲውን በመላው
አገሪቱ ሲተገብር በወላይታ ብሔር ተወላጅነታችሁ ርስዎና
አምባሳደር ተሾመ ቶጋ የአቶ መለስ ቀኝ እጅ በመሆን ብቅ
አላችሁ፡፡ የሁለታችሁ ፍፁም ታዛዥነት ለስልጣን ማማ
አበቃችሁ፡፡
ክቡር አቶ ኃ/ማርያም የርስዎ መሰላል ግን የሚገርም
ነው፡፡ ከስልጣን ወደ ስልጣን ለመሸጋገር ከመፍጠንዎ
የሀላፊነትዎ መደራረብ ከበረሀ ጀምሮ ለ17 ዓመታት በፅናት
የታገሉት አቶ አዲሱ ለገሠና አቶ ስዩም መስፍን በተናጠል
የያዙትን የሥልጣን ቦታ ርስዎ በግልዎ ሲጠቀልሉት ምን
አይነት ደስታ ተስማዎት ይሆን? የተደራረበልዎት ሥልጣን
የኢህአዴግ ምክትል ሊቀመንበር፣ የኤፌዲሪ ም/ጠ/ሚ/ር፣
የውጭ ጉዳይ ሚ/ር፣ የሕዳሴ ግድብ አስተባባሪ ብሔራዊ
ኮሚቴ የበላይ ጠባቂ የ. . .ድርጅት የቦርድ ሰብሳቢ . . .
አቤት የስልጣንዎ ብዛት! መቼም ስልጣንም “የቁጩ”
ባይሆን ኖሮ ምድር የሚበቃዎት አይመስለኝም፡፡ አቶ
መለስም መተካካት በሚል ለፈጠሯት የሥልጣን ዕድሜ
ማራዘሚያቸው ከ2002 ዓ.ም ምርጫ በኋላ ርስዎ ብርሃንዋ
በደበዘዘ ባትሪ ተፈልገው ተገኙ፡፡ “ከአብሮ አደግ አትሰደድ”
በሚል ውስጠ ሚስጥር የሕይወት መስዋዕትነት እየከፈለ
የመጣውን ጀግናውን የህወሓት ሠራዊት በዘዴ የሸኙት
አቶ መለስ በሁለት አስርት አመታት አገዛዛቸው የትግል
አጋሮቻቸውን በሰበብ በአስባቡ ከጨዋታ ውጭ እያደረጉ
በሥልጣን መንበራቸው ዙሪያ ከኮለኮሏቸው ጋሻ ጃግሬዎች
እንደ ጆከር እየተሰኩ የፖለቲካውን ቁማር የሚያስቆምሩ
በመሆንዎ፡፡
ክቡር ም/ጠቅላይ ሚ/ርና የውጭ ጉዳይ ሚ/ር
የሲዳማ ብሔር ተወላጆች የሆኑት አቶ አባተ ኪሾና አቶ
ሽፈራው ሽጉጤ የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች
ክልል ፕሬዝዳንት ሆነው ክልሉን ሲመሩ ርስዎ ለበለጠዉ
ቦታ በአቶ መለስ ተቀቡ፡፡ የደቡብ የሹመቱ ተራ ከሲዳማ
ብሔረሰብ ወደ ወላይታ አመራ፡፡ በወቅቱ ሁኔታው በክልሉ
የበላይነት ስሜትን ለሚያንፀባርቁና በአንዳንድ አራዳዎች
አባባል “የደቡብ ትግሬዎች” የሚል ስም ለተሰጣቸው
የሲዳማ ብሔረሰብ ሹማምንት የእርስዎ ፕሬዝዳንት
መሆን አልተዋጠላቸውም ነበር፡፡ ውስጥ ውስጡን እያየለ
የመጣው ሽኩቻ ውሎ አድሮ ችግር መፍጠሩ አልቀረም፡፡
የደቡብ ክልል በጉያዋ ካቀፈቻቸው ከ56 በላይ ብሔረሰቦች
መካከል የሲዳማና የወላይታ ብሔረሰብ ተወላጆች
ቁጥራቸው የላቀ እንደሆነ ይታመናል፡፡ የወላይታ ህዝብ ግን
ስፋት ባለው የመሬት ይዞታ ላይ አለመስፈሩ ይታወቃል፡፡
የክልሉን የፕሬዝዳንትነት ሥልጣን ያጡት የሲዳማ
ተወላጅ ሹማምንት በምርጫ 97 ዓ.ም ዋዜማ ላይ በብርቱ
አጉረመረሙ፡፡ መልክአ ምድራዊ አቀማመጣቸውንና
የህዝባቸውን የቁጥር ብዛት አንተርሰው ራሳቸውን ችለው
ክልል ለመሆን ለፌደራል መንግስት ጥያቄ አቀረቡ፡
፡ በወቅቱ የሲዳማ ዞን ዋና ከተማ ከሀዋሳ ተነስቶ ወደ
ይርጋለም ከተማ መዛወሩና ሀዋሳ የደቡብ ህዝቦች ክልላዊ
መንግስት ርዕስ ከተማ መሆኗ የሲዳማን ህዝብ በብርቱ
እንዳስከፋው ይታወቃል፡፡ ውድ አንባብያን በ1997 ዓ.ም
ምርጫ ቅንጅት አዲስ አበባ ላይ በማሸነፉ የኦሮሚያ ክልላዊ
መንግሥት ዋና ከተማ ከአዳማ አዲስ አበባ እንደመጣና
ሕዝቡ በየአካባቢው የድጋፍ ሰልፍ እንዲወጣ መደረጉ
ይታወቃል፡፡ ሁላችንም እንደምናውቀው ከምርጫው
በፊት የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት መቀመጫው ወደ
አዳማ ሲዛወር በተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የሚገኙ የብሔረሰቡ
ተወላጆች ድርጊቱን በመቃወማቸው ብዙ አፍላ ወጣቶች
የጥይት ራት ሆነዋል፤ ብዙዎቹ ታስረዋል፤ የቀሩትም
ከአገር ተሰደዋል፡፡ ይህን ግፍ የፈፀመው ኢህአዴግ አይኑን
በጨው አጥቦ “አዲስ አበባ የኦሮሚያ ዋና ከተማ በመሆኗ
ህዝቡ ለኢህአዴግ ያለውን ድጋፍ በደስታ ገለፀ” ሲል ነጋሪት
አስጎሰመ፡፡ የታሪክ ማፈሪያ!
ወደ ዋናው ጉዳዬ ስመለስ በወቅቱ የነበረው የሲዳማ
ብሔረሰብ ተወላጆች ኩርፊያ አቶ መለስን ሁለት ጊዜ
ወደ ሀዋሳ አመላለሳቸው፤ ጥያቄው ለሕወሓት ዘዋሪው
ኢህአዴግ ለአፍታ እንኳን የማይዋጥ ጉዳይ በመሆኑ
“ሳይቃጠል በቅጠል” እንዲሉ በአጭሩ መቀጨት ነበረበት፡፡
በመጀመሪያው ዙር ድርድር ራሳቸውን ችለው ክልል መሆን
እንደማይችሉ አስረግጠው የነገሯቸው አቶ መለስ “ለህፃን
ልጅ ብርጭቆ አይሰጥም” ሲሉ ቅስማቸውን በመስበር
አሸማቀቋቸው፡፡ ይሁን እንጂ የተቀጣጠለው እሳት ሙሉ
ለሙሉ አልጠፋም ነበር፡፡ ችግሩ እንደገና አገርሽቶ ሕዝቡ
ተቃውሞ በመውጣቱ አያሌ የሲዳማ ብሔረሰብ አባላት
ከአኝዋክ ህዝብ ባልተናነሰ ሁኔታ መጨፍጨፋቸው
የሚዘነጋ አይደለም፡፡ አቶ መለስም ከሁኔታዎች አሳሳቢነት
የተነሣ ዳግም ሀዋሳ ከተማ ተገኙ፤ እንደ ቀድሞው
ተለሳልሰው ሳይሆን እሳት ጎርሰው እሳት ለብሰው አመፁን
በቀዳሚነት የመሩትን የሲዳማ ብሔረሰብ ሹማምንትና ጋሻ
ጃግሬዎቻቸውን ከስልጣናቸው አራግፈውና የሲዳማ ዞንን
ዋና ከተማ ወደ ሀዋሳ እንዲመለስ መመሪያ ሰጥተው ካረጋጉ
በኋላ “ምጣዱ መስማቷ ላይቀር እንጨት ትጨርሳለች፡፡”
ሲሉ ተሳለቁባቸው፡፡ እንቅስቃሴውን ለአንዴና ለመጨረሻ
ጊዜ ለማዳፈንም አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝን አንስተው
ለሁለተኛ ጊዜ አቶ ሽፈራው ሽጉጤን ሾሙ፡፡ መንበር
ስልጣኑ ከወላይታ ወደ ሲዳማ ሲመለስ ነገሮች ፀጥ ረጭ
አሉ፡፡

የበለጠውን በምቀጥለው ሊንክ ያንቡ:
http://andinet.org/wp-content/uploads/2012/03/Finote-Netsanete-Issue-35.pdf