POWr Social Media Icons

Sunday, April 1, 2012


ለሁለት ቀናት በሀዋሣ ሲካሄድ የቆየው የሲዳማ ዞን ምክር ቤት 3ኛ ዙር 8ኛ መደበኛ ጉባኤ ሦስት የዞን ካቢኔዎችን ሹመትና ከ32 ነጥብ 8 በላይ ተጨማሪ በጀት በማፅደቅ ተጠናቀቀ፡፡የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ማሊዮን ማቴዎስ ለም/ቤቱ በእጩነት ያቀረቧቸው ካቢኔዎች የዞኑ ግብይትና ህብረት ስራ መምሪያ ኃላፊ የከተማ ልማት መምሪያ ኃላፊ እንዲሁም የሲቪል ሰርቪስ መምሪያ ኃላፊ በመሆን በም/ቤቱ ሙሉ ድምፅ መመረጣቸው ታውቋል፡፡
በተጨማሪም ም/ቤቱ ለቀጣይ ወራት የዞን ማዕከል፣ 19 ወረዳዎችና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች ለልማትና ለመልካም አስተዳደር ስራዎች እንዲሁም ለሰራተኞች ደመወዝ ክፍያ የሚጠቀሙበትን ከ32 ነጥብ 8 ሚሊዮን በላይ በጀት ማፅደቁ ተመልክቷል፡፡
በም/ቤቱ የኢኮኖሚ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ሲምቦ ሽብሩ የተጨማሪ በጀት ደንብ ሰነድ ለም/ቤቱ አባላት ሲያቀርቡ ከተመደበው ተጨማሪ በጀት ከ6 ነጥብ 9 በላይ ሚሊዮን በ2ዐዐ3 የበጀት አመት በተለያዩ ምክንያት ስራ ላይ ያልዋለ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ቀሪው ከ25 ነጥብ 9 በ ላይ ሚሊዮን በጀት ደግሞ የዞኑ ማዕከል፣ ወረዳዎችና ከተማ አስተዳደሮች ከእቅዳቸው በላይ የሰበሰቡት መሆኑን አቶ ሱምቦ መጠቆማቸውን የዘገበው የዞኑ ባህል ቱሪዝም የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ ነው፡፡

የዳራ ወረዳ ውና፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ህብረተሰቡን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡፡
የጽህፈት ቤቱ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የተቋማት አስተዳደር ሥራ ሂደት አስተባባሪ ተወካይ አቶ ባንታየሁ ጉዲሳ አንደገለፁት በንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ኘሮግራም እቅድ ከተያዙት 17 ምንጮች የ12ቱ ግንባታ 87 በመቶ ተጠናቋል፡፡
የግንባታው ወጪም 85 በመቶ ትንሳኤና ብርሃን በተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት የሚሸፈን ሲሆን 15 በመቶ በወረዳው በጀት ይሸፈናል፡፡ግንባታው ሲጠናቀቅ የወረዳው የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን 38 ነጥብ 8 በመቶ ይደርሳል ማለታቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡