የሀዋሣሳ ከተማ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ሁሉን አቀፍና ተደራሽ ህብረተሰብ ለመፍጠር መሰናክሎች ማስወገድ በሚል መሪ ቃል የአለም አቀፍ የአካል ጉዳተኞች ቀን አከበረ፡፡


ቀኑ የመንግስት ሴክተር መስሪያ ቤቶች አካል ጉዳተኞችን ተሳታፊና ተጠቃሚ የሚያደርጉ እቅዶችን መያዛቸውን ለመገምገም የተዘጋጀ ነው፡፡
የክልሉ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ኤጀንሲ የማህበራዊ  ደህንነት ልማት ኦፊሰር አቶ አየለ ስሜ እንደገለፁት አካል ጉዳተኞች በሁሉም ዘርፎች እኩል ተጠቃሚ የሚሆንበት አሠራር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል፡፡
የኢትዮጵያ አካል ጉዳተኞች ብሔራዊ  ማህበራት ፌደሬሽን የደቡብ ክልል ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስኪያጅ  አቶ ወንድማገኘው ይስሀ አካል ጉዳተኝነት ለኤች አይ ቪ ኤድስ እና ለድህነት የሚያጋለጥ በመሆኑ በጤና ተቋማት አካል ጉዳተኞችን  ያካተተ ስራ መጠናከር እንዳለበት ገልፀዋል፡፡

አንዳንድ የውይይቱ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በከተማው ለአይነ ስውራንና  መስማት ለተሳናቸው የሚሆን የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለመኖሩ ትምህርታቸው መጠቀል አለመቻላቸውን ተናግረዋል፡፡
የተለያዩ የስፖርት ውድድሮችም የተካሄዱ ሲሆን ከአንድ እስከ 4 ለወጡ ተወዳዳሪዎችም የብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡ ባልደረባችን ቢንያም ተስፋዬ እንደዘገበው፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/25HidTextN305.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር