በደቡብ ደርቢ በጉጉት የሚጠበቀው የሀዋሳ ከነማና አርባ ምንጭ ከነማ ፍልሚያ ሀዋሳ ላይ ይደረጋል: ሀዋሳ ከነማ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ በድል ከተወጣ ለሁለት ወራት ያህል የደረጃ ሰንጠረዡን መምራት የሚያስችለውን አጋጣሚ ያገኛል



9ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ መለስ ዋንጫ ህዳር 25/2005 ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል።

በ8ኛው ሳምንት መርሀ ግብር በሜዳው በሀዋሳ ከነማ ሽንፈት የደረሰበት ቅዱስ ጊዮርጊስ ህዳር 25/2005 ሀረር ላይ ከሀረር ቢራ አንድ አቻ በመለያየት ተመልሷል፡፡ባለ ሜዳዎቹ ሀረር ቢራዎች አሸናፊ አደም ባስቆጠራት ግብ ለበርካታ ደቂቃዎች መርተዋል።
የደረጃ ሰንጠረዡ መሪ ቅዱስ ጊዮርጊስ አንድ ነጥብ ያገኘበትን የአቻነት ግብ ኡመድ ኡኩሪ በ77ኛው ደቂቃ ላይ አስቆጥሯል፡፡በሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ላይ 5 ነጥቦችን የጣለው ቅዱስጊዮጊስ ህዳር 26/2005 ሀዋሳ ከነማ የሚያሸንፍ ከሆነ የደረጃ መሪነቱን ይነጠቃል፡፡ደደቢትም በተሻለ ግብ ልዩነት ድል ከቀናው ከቅዱስ ጊዮርጊስ በላይ መቀመጥ ይችላል፡፡
የህዳር 25/2005 መርሀ ግብር የሆነው ሌላው በአዲስ አበባ ስታድየም መከላከያና የኢትዮጵያ ውሀ ስራዎች ፍልሚያ ነበር፡፡መከላከያ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት በመርታት ሁለት ደረጃዎችን በማሻሻል ከ10ኛ ወደ 8ኛ ከፍ ማለት ችሏል፡፡ኢትዮጵያ ውሀ ስራዎች ግን ከዘጠኝ ጨዋታዎች በምንም ማሸነፍ ተስኖታል፡፡ያለው ብቸኛ ነጥብ ከሙገር ሲሚንቶ ጋር አንድ አቻ የተለያዩበት ሲሆን በርካታ የግብ ክፍያዎችን ይዞ የመጨረሻው ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡
ህዳር 25/2005 የ9ኛው ሳምንት ቀሪ አምስት ጨዋታዎች ይጠበቃሉ፡፡በደቡብ ደርቢ በጉጉት የሚጠበቀው የሀዋሳ ከነማና አርባ ምንጭ ከነማ ፍልሚያ ሀዋሳ ላይ ይደረጋል፡፡ሀዋሳ ከነማ በሜዳው የሚያደርገውን ጨዋታ በድል ከተወጣ ለሁለት ወራት ያህል የደረጃ ሰንጠረዡን መምራት የሚያስችለውን አጋጣሚ ያገኛል፡፡ደደቢት በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታድየም ውጤት ከራቀው አዳማ ከነማ ይገናኛል፡፡እዚህ አዲስ አበባ ስታድየም ላይ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመብራት ሀይል 10 ሰዓት ላይ የሚያደርጉትን ጨዋታም ይጠበቃል፡፡12 ሰዓት ላይ ደግሞ ኢትዮጵያ መድህን ሲዳማ ቡናን ያስተናግዳል፡፡
አሰላ ላይ ደግሞ ዘንድሮ መጥፎ አጀማመር ያሳየው ሙገር ሲሚንቶ አራተኛ ደረጃ ላይ ከተቀመጠው ኢትዮጵያ ቡና ይጫወታል፡፡
 http://www.ertagov.com/ertasport/erta-tv-news-football-addis-ababa-ethiopia/39-amharic-news-catagory-of-sport-football-erta-tv-addis-ababa-ethiopia/1342-9-.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር