የጋዜጠኞች መገደል



ሃያ-ስምንት የኤርትራ ጋዜጠኞች በዳርዊሽ ቋንቋ «የማያዉቁትን ፈንጂ ረግጠዉ» ከማይታወቅ ሥፍራ ከተከረቸሙ ዓመታት አልፏቸዋል።ዳ ብዙ ኢትዮጵያዉያን ጋዜጠኞች እስር ቤቶችን ተመላልሰዉባቸዋል። ዉብሸት ታዬ፥ ርዕዮት ዓለሙ፥ እስክንድር ነጋ እና ሌሎችም ዛሬም በየወሕኒ ቤቱ ይማቅቋሉ።
19 12 12


የተገባደደዉ የጎርጎሮሳዉያኑ ዓመት 2012 ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ጋዜጠኞች የተገደሉበት፥ በርካቶች የታሠሩ ወይም የተንገላቱበት ዓመት እንደሆነ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቾች አስታወቁ።ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች የተሰኘዉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋች ድርጅትና ሌሎች ተቋማት እንዳስታወቁት የግብፅ ሕዝባዊ አብዮት፥ የሶሪያዉ ጦርነት፥ የሶማሊያ ግጭት ለበርካታ ጋዜጠኞች ሞት ምክንያት ሆኗል።እንደ ጎሮጎሮሳዉያኑ አቆጣጠር ከ1995 ወዲሕ በአንድ ዓመት ዉስጥ በርካታ ጋዜጠኞች ሲገደሉ ዘንድሮዉ ከፍተኛዉ ነዉ።ነጋሽ መሐመድ አጭር ዘገባ አለዉ።

«ሶሪያ ዉስጥ ጋዜጠኛ መሆን ፈንጂ በፈሰሰበት ምድር እንደመራመድ ነዉ።ብዙ የማይነኩ ነገሮች አሉ።አንዳዶቹ ለምሳሌ ፖለቲካዊ፥የሰብአዊ መብቶች ወይም የሥርዓቱ ባሕሪያት የመሳሰሉት ርዕሶች በግልፅ ይታወቃሉ።ሌሎች ደግሞ ቀይ መስመራቸዉ የማይታወቅ ግን አይነኬ ብዙ ጉዳዮች አሉ።እና ፈንጂዉን መቼ እንደምትረገጠዉ፥መቼ እንደሚፈነዳም የሚያዉቅ የለም» ብሎ ነበር። ሶሪያዊዉ ጋዜጠኛ ማዘን ዳርዊሽ፥-ሐቻምና መጋቢት።

ዳርዊሽ ፈንጂዉን እንዴት እንደረገጠዉ በርግጥ የሚያዉቅ የለም።ብቻ ፈነዳ። ግን አልገደለዉም። ካልታወቀ ስፍራ-አሳሰረዉ እንጂ።ዳርዊሽ የዘንድሮዉን የድንበር የለሽ ዘጋቢዎችን ሽልማትን አግኝቷል።
---
DW-Grafik: Per Sander
2010_11_30_gefährliches_leben_journalisten.psdሕይወትን ለሙያ


ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች እንደሚለዉ ሃያ-ስምንት የኤርትራ ጋዜጠኞች በዳርዊሽ ቋንቋ «የማያዉቁትን ፈንጂ ረግጠዉ» ከማይታወቅ ሥፍራ ከተከረቸሙ ዓመታት አልፏቸዋል።ዳሪዊሽ የኤርትራዉያኑን ዕጣ ከመጋራቱ በፊትና በሕዋላ ብዙ ኢትዮጵያዉያን ጋዜጠኞች እስር ቤቶችን ተመላልሰዉባቸዋል። ዉብሸት ታዬ፥ ርዕዮት ዓለሙ፥ እስክንድር ነጋ እና ሌሎችም ዛሬም በየወሕኒ ቤቱ ይማቅቋሉ።

በሁለት ሺሕ አስራ-ሁለት፥ ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች እንደሚለዉ ከአንድ ሺሕ የሚበልጡ ጋዜጠኞችና የኢንተርኔት ፀሐፍት (ብሎገርስ) ታስረዋል።ባመቱ ማብቂያ ብዙዎቹ ተለቀዋል።

ከኤርትራ-እስከ ቱርክ፥ ከኢትዮጵያ እስከ ቻይና፥ ከማሊ እስከ ኩባ አንድ መቶ ዘጠና ሰወስት ጋዜጠኞች ያዩ-የሰሙትን፥ የሚያስቡ፥ የሚመስላቸዉን በመዘገባቸዉ ብቻ አሁንም በየወሕኒ ቤቱ ይማቅቃሉ።

ከግብፅ እስከ ሶሪያ፥ ከሶማሊያ እስከ ፓኪስታን፥ ከማሊ እስከ ሜክሲኮ ዘንድሮን አምና ለማለት ካልታደሉ ጋዜጠኞች ዕጣ ጋር ሲነፃፀር ግን ለታሳሪዎቹ-እስር ቤቱም «ዓለም ነዉ» ማሰኘቱ አልቀረም።አስር ቀን በቀረዉ የጎርጎሮሳዉያኑ ሁለት ሺሕ አስራ-ሁለት ሰማንያ-ስምንት ጋዜጠኞች፥አርባ ሰባት የኢንተርኔት ፀሀፍት፥ ስድስት የመገናኛ ዘዴ ተባባሪ ሠራተኞች ተገድለዋል።

ለጋዜጠኞችና ለሙያቸዉ በጀርመን የድንበር የለሽ ዘጋቢዎች ተወካይ ኡልሪከ ግሩስከ እንደሚሉት ዘንድሮ በርግጥ ገደቢስ ዓመት ነዉ።

«2012 ዓመት፥ ድንበር የለሽ ዘጋቢዎች ሥለ ጋዜጠኞች መዘገብ ከጀመረበት ከ1995 ወዲሕ ብዙ ጋዜጠኞች የተገደሉበት ዓመት ነዉ።»

ብዙ ጋዜጠኞች ወይም አምደኞችን በመግደል-ሶሪያ አንደኛ ናት።በአምደ መረብ፥ በተንቀሳቃሽ ሥልክ መረጃና ፎቶ የሚያቀብሉ አርባ-ሰባት፥ሰዎች ተገድለዋል።አስራ-ሰባት ባለሙያ ጋዜጠኞችና ተባባሪዎቻቸዉም እንዲሁ።በድምሩ ሥልሳ አምስት። ዜኒት የተሰኘዉ መፅሔት አዘጋጅ ኒልስ ሜትሲገር እንደሚለዉ የሶሪያ ጋዜጠኞች ለሁሉም ተፋላሚ ሐይላት ጥቃት የተጋለጡ ናቸዉ
ARCHIV - Aktivisten der internationalen Journalistenvereinigung Reporter ohne Grenzen halten in Berlin vor der russischen Botschaft Fotos der ermordeten Journalistin Anna Politkowskaja in die Luft (Archivfoto vom 07.10.2007). Die Journalistenvereinigung Reporter ohne Grenzen erhält für ihren Beitrag zur europäischen Integration den europäischen Medienpreis, die Karlsmedaille 2009. Mit ihrem Einsatz für die Meinungs- und Pressefreiheit leiste die Organisation einen wichtigen Beitrag zum Wertefundament Europas, teilte der Stifterverein am Mittwoch in Aachen mit. Die freie Berichterstattung und Recherche gehöre als elementares Menschenrecht zur Verwirklichung der Einheit Europas. Die Preisverleihung findet am 14. Mai im Krönungssaal des Aachener Rathauses statt. Foto: Johannes Eisele dpa/lbn +++(c) dpa - Bildfunk+++የድንበር የለሽ ዘጋቢዎች አርማ
«የሶሪያዎቹ ባልደረቦቻችን ችግር የተፋላሚ ሐይላት ኢላማ መሆናቸዉ ነዉ።ብዙዎቹ አማፂያን ለሶሪያ መንግሥት መገናኛ ዘዴዎች የሚሰሩ ጋዜጠኞች የጦርነቱን ሒደት በገለልተኝነት አይዘግቡም በማለት ይወነጅሏቸዋል።በተለይም ሙስሊም አማፂያን ለሶሪያ መንግሥት መገናኛ ዘዴዎች የሚሰሩ ጋዜጠኞችን ሆን ብለዉ ይገድላሉ።ወይም ያግታሉ።»

ብዙ ባለሙያ ጋዜጠኞችን በመገደል ሶማሊያ አንደኛ ናት።ሶሪያ በአስራ-ሰባት ጋዜጠኞች ሁለተኛ፥ ፓኪስታን ሰወስተኛ አስር ተገድለዉባል።እያለ ቁጥሩ ይቀጥላል።አመቱ ግን አዲዮስ።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር