ሐዋሳ ከነማ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የደረጃ ሰንጠረዥ መሪ ሆነ



በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ ረቡዕ ህዳር 26/2005 በተከናወነው ጨዋታዎች ሐዋሳ ከነማ እና ደደቢት ድል ሲቀናቸው መብራት ኃይልና
ኢትዮጵያ ቡና ነጥብ ጥለዋል።

በዘጠነኛው ሳንምት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በዕለቱ አምስት ጨዋታዎች ተከናውነዋል።ከነዚህ መካከል ሐዋሳ ላይ ሐዋሳ ከነማ አርባምንጭ ከነማን ያስተናገደበት ጨዋታ ከፍተኛ ግምት አግኝቶ ነበር።

የፕሪምየር ሊጉ መሪ የነበረው ቅዱስ ጊዩርጊስ ህዳር 25/2005 ሐረር ላይ ከሐረር ቢራ ጋር ተጫውቶ ነጥብ ጥሎ በመመለሱ ምክንያት ሐዋሳ መሪነቱን የሚረከብበት መልካም አጋጣሚ ይዞ ነበር ወደ ሜዳ የገባው።

ዘንድሮ ጥሩ እንቅስቃሴ እያሳየ ያለው ሐዋሳ የደቡብ ደርቢውን ጨዋታ 2 ለ 1 በሆነ ውጤት በመርታት ለወራት ያክል የደረጃ አናት ላይ የሚሆንበት ጣፋጭ ድል ይዞ ወጥቷል።ብሩክ አየለ የሐዋሳ ከነማን ሁለቱንም ግቦች ሲያስቆጥር በረከት ዳሙ ደግሞ የአርባምንጭን ብቸኛ ግብ ከመረብ አገናኝቷል።

ከህዳር 27/2005 ጀምሮ ለብሔራዊ ቡድኑ ዝግጅትና አፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ሲባል የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታዎች ስለሚቆረጡ ሐዋሳ ከነማ መሪነቱን ይዞ ለበረካታ ሳምንታት ይቆያል።

ወደ አዳማ ከነማ ተጉዞ በአዳማው አበበ ቢቂላ ሰታዲየም ውጤት የራቀውን አዳማ ከነማን የገጠመው ደደቢትም 3ለ1 አሸንፎ ተመልሷል።ጌታነህ ከበደ ለደደቢት ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል።

በዚህም የሊጉን ከኮከብ ግብ አግቢነት በብቸኝነት ይመራል።በኃይሉ አሰፋ ቀሪዋን የደደቢት ግብ አስቆጥሯል።

በውጤቱም ደደቢት ከቅዱስ ጊዩርጊስ እኩል 18 ነጥብ በመያዝ በግብ ክፍያ በልጦ ሁለተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላል።

ወደ አሰላ ተጉዞ የነበረው ኢትዮጵያ ቡና ከሙገር ሲምንቶ ጋር ያለምንም ግብ በመለያየት ሁለት ነጥቦችን ጥሎ ተመልሶል።ሌሎች ሁለት ጨዋታዎች የተደረጉት በአዲስ አበባ ሰታዲየም ሲሆን ሁለቱም ጨዋታወች ባለመሸናነፍ የተጠናቀቁ ነበሩ።መብራት ኃይል ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ግብ ያልተቆጠረበት ጨዋታ አድርገዋል።።ሲዳማ ቡናን አስተናግዶ የነበረው ኢትዮጵያ መድህን ነጥብ ተጋርቶ ወጥቷል።

ሁለት ለሁለት በተጠናቀቀው ጨዋታ ለኢትዮጵያ መድህን መሃሙድ ናስር ነበር ሁለቱን ግቦች ያስቆጠረው ።በዚህም በሊጉ ኮከብ ግብ አግቢነት ፉክክር በ8 ግቦች ጌታነህ ከበደን ተከትሎ ሁለተኛ ሆኗል።

ለሲዳማ ቡና ሚካኤል ጆርጁና አሸናፊ አዳም ግቦቹን አስቆጥረዋል። ሚካኤል ጆርጅ ግቧን ካስቆጠረ በኃላ የእጅ ውልቃት ጉዳት ደርሶበት ከሜዳ ተቀይሮ ለመውጣት ተገዷል።

አስረኛው ሳምንት የሊጉ መርሃ ግብር ብሔራዊ ቡድኑ ከ2013ቱ አፍሪካ ዋንጫ ተሳትፎ ሲመለስ ከሳምንታት በኃላ የሚቀጥል ይሆናል።

9ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ ህዳር 26/2005 . የደረጃ ሰንጠረዥ


.
ክለብ
ተጫወተ
አሸነፈ
አቻ
ተሸነፈ
ነጥብ
1
ሀዋሳ ከተማ
9
6
1
2
19
2
ደደቢት
9
5
3
1
18
3
ቅዱስ ጊዮርጊስ
9
5
3
1
18
4
ኢትዮጵያ ቡና
9
4
4
1
16
5
ሀረር ቢራ
9
4
4
1
16
6
መብራት ሀይል
9
3
4
2
13
7
መከላከያ
9
3
3
3
12
8
ሲዳማ ቡና
9
2
6
1
12
9
አርባምንጭ ከነማ
9
3
9
3
12
10
ኢትዮጵያመድህን
9
9
3
3
12
11
ንግድ ባንክ
9
1
4
5
7
12
አዳማ ከነማ
9
1
3
5
6
13
ሙገር
9
0
4
5
4
14
ውሃ ስራዎች
9
0
1
8
1
http://www.ertagov.com/am/component/content/article/65-2010-08-26-05-18-49/3523-2012-12-06-08-25-18.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር