የኢትዮጵያ ሴቶች እግር ኳስ ዛሬና ነገ ይቀጥላል



አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 6፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ እግር ኳስ ውድድር ዛሬና ነገ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ ከተሞች ይቀጥላል።
ዛሬ በአዲስ አበባ ስታድየም ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመከላከያ በ9 ሰዓት ፥ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት በ11 ሰዓት ይጫወታሉ።
ውድድሩ ነገ ቀጥሎ ፥ ደደቢት ከኢትዮጵያ መድን ፣ መብራት ኃይል ከኢትዮጵያ ቡና በ9 እና በ11 ሰዓት በአዲስ አበባ ስታድየም ይጫወታሉ።
አዳማ ላይ አዳማ ከነማ  ድሬዳዋ ከነማን ሃዋሳ ላይ ደግሞ ሃዋሳ ከነማ ሲዳማ ቡናን ያስተናግዳሉ።
አርባ ምንጭ ከነማ የሳምንቱ አራፊ ቡድን እንደሚሆን አራያት ራያ ዘግባለች።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር