ጥራት ያለው ትምህርት ለልማት ያለው ፋይዳ ጉልህ በመሆኑ ሁሉመ ባለድርሻ አካላት መረባረብ እንደሚጠበቅባቸው በሲዳማ ዞን የአለታ ጩኮ ወረዳ ትምህርት ቤቶች ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡


በወረዳው የሚገኙ የትምህርት ባለድርሻ አካላት በወረዳው ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ሞዴል በሆነው በማንጉዶ ትምህርት ቤት በመገኘት ሰሞኑን የተሞክሮ ልውውጥ አድርገዋል፡፡
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሽመልስ አየለ እንደገለፁት ጥራት ያለው ትምህርት ለልማት ያለው ፋይዳ የላቀ መሆኑን በመገንዘብ ጥራቱን ለማስጠበቅ ከሚመለከታቸው ከትምህርት ባለ ድርሻ አካላት ጋር ሰፊ ሥራ መስራታቸውን ተናግረዋል፡፡
በዚሁ በተሰራው ሰፊ ስራ በወረዳው የሚገኙ ትምህርት ቤቶች የትምህርትን ጥራት ለማምጣት የእርስ በርስ የሥራ ፉክክር መንፈስ በመላበስ እንዲሰሩ በተደረገው መጠነ ሰፊ እንቅስቃሴ ከወረዳው ከሚገኙ ከ43 ትምህርት ቤቶች መካከል  የመንጉዶ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተያዘው በአንደኛ ሩብ አመት በትምህርት ሥራ የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ሞዴል ትምህርት ቤት መሆኑን አብራርተዋል፡፡
የማንጉዶ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ ዱሬሳ ዮኖራ በበኩላቸው ትምህርት ቤቱ በአሁኑ ጊዜ 1ኛና ሞዴል ሊሆን የቻለው መንግስት የቀረፀውን ስድስቱን የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ፓኬጆችን ከትምህርት ባለ ድርሻ አካላት ጋር ተግባራዊ በማድረጋቸው መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ከሲዳማ ዞን ትምህርት መምሪያ የትምህርት ጥራት ዋና የሰራ ሂደት አስተባባሪ አቶ እሸቱ ቃሬ እንደተናገሩት የትምህርት ቤቶች የልምድ ልውውጥ የትምህርትን ጥራት በማስጠበቁ ረገድ የላቀ ሚና አለው፡፡
ልምድ ልውውጡ ወቅት ለ12 ወላጅ አጥ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው እዳይስተጓጎሉ ከትምህርት ቤቱ ማህበረሰብ ከተገኘው ገንዘብ የተለያዩ አልባሳት ተበርክተውላቸዋል ፡፡ የበንሳ ቅርንጫፈ እንደዘገበው፡፡
http://www.smm.gov.et/

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር