በሲዳማ ዞን አለታ ወንዶ ወረዳ በሁለተኛው ዙር የመሬት ልኬት ከ5 መቶ በላይ የገጠር መሬት የይዞታ ማረጋገጫ ካርታና ሰርተፊኬት ለጊዲቦ ቀበሌ አርሶ አደሮች አዘጋጅቶ መስጠቱን የወረዳው ግብርናና ገጠር ልማት ጽህፈት ቤት ገለፀ

በወረዳው ጊዲቦ በተባለ ቀበሌ ነዋሪ ለሆኑ አባወራና እማወራ አርሶ አደሮች ለሁለተኛ ዙር የመሬት ልኬት ካርታና ሰርተፍኬት አሰጣጥ ስነ ስርዓት ላይ የተገኙት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታምሩ ሳሙኤል ባሰሙት ንግግር አርሶ አደሩ የይዞታ ማረጋገጫ ካርታና ሰርቲፍኬት ማግኘቱ በመሬቱ የባለቤትነት መብት ተሰምቶት ልማቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ያስችላል፡፡


የወረዳው ግብርና ገጠር ልማት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በርናባስ ሮማ በበኩላቸው መንግስት የአርሶ አደሩን የመሬት ይዞታ ዋስትና ለማረጋገጥ መሬቱን አልምቶ የምርቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ሰፊ ስራ እያከናወነ ይገኛል ብለዋል፡፡
ከቀበሌው ነዋሪዎች መካከል  አርሶ አደር ብሩ ሙፋቶሃና ሴት አርሶ አደር አማረች ተስፋዬ በሰጡት አስተያየት የይዞታ ማረጋገጨ ካርታና ሰርቲፍኬት መስጠቱን በንብረታቸው ይበልጥ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ከማስቻሉም ሌላ ሁሉንም ፆታዎች በእኩል ደረጃ የመሬት ባለቤት እንዲሆኑ በማድረጉ መደሰታቸውን ገልፀዋል፡፡ የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን እንደዘገበው፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/23HidTextN205.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር