በሀዋሳ ከተማ ከ253 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የልማት ፕሮግራም እየተካሄደ ነው


ሃዋሳ ታህሳስ 04/2005 በሀዋሳ ከተማ መንግስታዊ ያልሆኑ 74 ድርጅቶች ከ253 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ በጀት ህብረተሰቡን ያሳተፉ የልማት ፕሮግራሞች እያካሄዱ መሆናቸውን የከተማው ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምሪያ ገለጸ፡፡ የመምሪያው ምክትል ሃላፊ አቶ አሻሬ ኡጋ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በከተማው ስምንት ክፍለ ከተሞች የሚካሄደው የልማት ፕሮግራም ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት የሚቆዩ ናቸው፡፡ ከልማት ፕሮግራሞቹ መካከል የጤና፣ የትምህርት፣ የከተማ ግብርና፣ የአካባቢ ጥበቃ፣ የህጻናት ድጋፍና ክብካቤ፣የገቢ ማስገኛ ፣አቅም ግንባታን ጨምሮ ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚ ጠቀሜታ ያላቸው ዘርፎች መሆናቸውን አስታውቀዋል የከተማውን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ልማት ለማፋጠን መንግስት የሚያደረገውን ጥረት ለማገዝ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ህብረተሰቡን በማሳተፍ የሚካሄዱት የልማት ፕሮግራሞች ሲጠናቀቁ ከ200ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ገልጸዋል፡፡ የድርጅቶቹን የስራ አንቅስቃሴና አፈጻጸም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ክትትልና ቁጥጥር እያደረጉ መሆናቸውንም አመልከተዋል፡፡ እየተጠናቀቀ ባለው የአውሮፓውያኑ 2012 የስራ ዘመን ድርጅቶቹ በመደቡት ከ84 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የከተማው ነዋሪዎች ተጠቃሚ ያደረጉ ተመሳሳይ የልማት ፕሮግራሞች ማካሄዳቸውን የመምሪያው ምክትል ሃላፊ ገልጸዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=3941&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር