ከሲዳማ ዞን በህገ ወጥ መንገድ የእሸት ቡና ወደ ሌሎች አካባቢ ሲያዘዋውሩ የተገኙ የሦስት የጭነት መኪናዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡

የጭነት መኪናዎቹ የተያዙት የዞኑ ፖሊሲ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ በዘርፉ ከተቋቋመው ግብረ ኃይል በመተባበር ነው፡፡
የጭነት መኪናዎቹ ሦስት አይሱዚዎች ሲሆኑ ኮድ ሦስት ታርጋ ቁጥር 67218፣ 68896፣ እና 48 3ዐ7 አዲስ አበባ የሚሉ ናቸው፡፡
የሲዳማ ዞን ፖለሲ መምሪያ ህገ ወጥ የቡና ግብይትን ለመቆጣጠር በዞኑ ከተቋቋመው ግብረ ኃይል ጋር በመተባበር ባለፈው አርብ ከሌሊቱ 9 ሰዓት በተደረገው ክትትል ተሽከርካሪዎቹ በቁጥጥር ሲውሉ አሽከርካሪዎቹ አምልጠዋል፡፡
የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኢንስፔክተር ተስፋዬ ዴቢሶ አንደገፁት ቡና ጥራቱን ጠብቆ ለማዕከላዊ ገበያ ቀርቦ ለአገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት የሚጫወቱት ሚና በተገቢው መልኩ እንዲወጣ ማድረግ ከተፈለገ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴዎች ሊቆሙ ይገባል፡፡
የአገሪቱን ኢኮኖሚ የሚጐዱ የንግድ እንቅስቃሴዎችን የሚያደርጉ የንግዱ ማህበረሰብ ከድርጊታቸው ከወዲሁ ሊቆጠቡ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡
ድርጊቱን የማጋለጥ ሥራ በዞኑ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ኢንስፔክተር ተስፋዬ አልክተዋል፡፡
የሲዳማ ዞን ቡና አቅርራቢዎች ማህበር ምክትል ሊቀመንብር አቶ ቶንጐላ ቶርባ በሰጡት አስተያየት ቡና የአገሪቱ ኢኮኖሚ ዋልታ በሆኑ በዘርፉ የተሰማሩ በተቀመጠው ደንብና መምሪያ መሠረት መንቀሳቀስ ሲገባ ህገ ወጥ የንግድ እንቅስቃሴ የሚያደርገትን አጥብቀው እንደሚቃወሙ ተናግረዋል፡፡
ህገና ህጋዊነት ለማክበር መዘጀታቸውን በማረጋገጥ የዞኑ ግብይትና ህብረት ስራ መምሪያ ኃላፊ አቶ ቡርቃ ቡላሾ በበኩላቸው ማንኛውም የቡና ግብይት በተፈጠረላቸው የግብይት ማዕከላት ብቻ እንዲካሄድ የወጣውን ደንብ ወደ ጐን በመተው የተፈፀመ ድርጊት በቡና ጥራት ላይ አሉታዊ ተፅኖ የሚፈጥር ነው ብለዋል፡፡
በዞኑ እንዲሁ ዓይነት ድርጊት እንዳይፈጠር ለማድረግ በበጀት ዓመቱ መጀመያ ላይ ከቡና አቅራቢ ማህበራትና ነጋዴዎች ጋር የግንዛቤ መፍጠሪያ ውይይት መደረግን አውስተዋል፡፡
ከዞን እስከ ወረዳ የተቋቋመ ግብረ ኃይል ህገ ወጥ የቡና ግብይት ሠራዓትን ለማጋለጥ በሚያደርገው ተግባር የመላው ህብረተሰብ ተሳትፎ ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት አቶ ቡርቃ አሳስበዋል፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/19TikTextN605.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር