በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ በተያዘው የበጀት ዓመት የጤና ልማት ሠራዊት አቅምን በማጎልበት ጤናው የተጠበቀ ህብረተሰብ ለመፍጠር እየሠራ መሆኑን የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የወረዳው ምክትል አስተዳዳሪና የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ታሪኩ ታደሰ አንዳስታወቁት በወረዳው የሰለጠኑ ሞዴል ቤተሰቦችን በ1 ለ5 ቁርኝት በማደራጀትና የየግላቸውን እቅድ እንዲያዘጋጁ በማድረግ ህብረተሰቡ የግልና የአካባቢ ንፅህናን እንዲጠበቅ መደረጉን ገልፀዋል፡፡
በተያዘው የበጀት ዓመትም ጽህፈት ቤቱ ተላላፊ በሽታዎችን በመከላከል ረገድ የህብረተሰቡን ግንዛቤ ለማሳደግ የተጠናከረ የማህበረተሰብ ውይይቶች በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ የጠቆሙት ኃላፊው በተለይም ከወረዳው ወባማ በሆነ 6 ቀበሌያት ለእያንዳንዱ ቤተሰብ እስከ 5 አጎበር ከመከፋፈሉ በተጨማሪ የኬሚካል ርጭትም መከናወኑን ተናግረዋል፡፡
የጤና ተቋማት ተደራሽነት ለማስፋፋት በወረዳው አገልግሎት እየሰጡ ከሚገኙ 5 ጤና ጣቢያዎች በተጨማሪ በመንግስት በጀት በ2ዐዐ4 ግንባታቸው እየተገነቡ ካሉ ሁለት አዳዲስ ጤና ጣቢያዎች የአንደኛው ግንባታ ተጠናቆ ርብርብ መደረጉንና በወረዳው ዋና ከተማ በቀባዶ አንድ ሆስፒታል በመገንባት ላይ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡
የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች እንደዘገበው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር