«ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የምርጫና ዴሞክራሲ አማካሪ ተቋም ጋር ተባብሮ ለመሥራት ዝግጁ ናት» ጠ/ሚ ኃይለማርያም


ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የምርጫና ዴሞክራሲ አማካሪ ተቋም ጋር ተብብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆኗን ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ አረጋገጡ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም የአማካሪ ተቋሙን ዋና ጸሐፊ ቪዳር ሄልግሰን ጥቅምት 22/2005 በፅህፈት ቤታቸው ተቀብለው ሲያነጋግሩ እንደገለፁት ኢትዮጵያ ከተቋሙ ጋር ተባብራ ለመሥራት ፍላጎቷ ነው።

ተቋሙ በኢትዮጵያ በ2002 የተካሄደውን ብሔራዊና ክልላዊ ምርጫ በምርምር ያቀረበው የሥነ ምግባር መመሪያ በሁሉም ወገኖች ዘንድ ተቀባይነት ያተረፈ እንደነበር አስታውሰዋል።

መንግሥት ቀደም ሲል የተፈጠረውን ግንኙነት መሠረት በማድረግ ከተቋሙ ጋር በቀጣዩም ተባብሮ ለመሥራት ፍላጎት እንዳለውም አስታውቀዋል፡፡

ተቋሙ በምርጫና በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ላይ አዳዲስ ሐሳቦችን በማመንጨት እንዲያቀርብም መጠየቃቸውን አንድ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣን ለጋዜጠኞች ገልፀዋል።

ሚስተር ሄልገሰን በበኩላቸው በጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሞት ጥልቅ ኀዘን እንደተሰማቸው አስታውቀው፣ በእሳቸው አመራር ዘመን በኢትዮጵያ የተጀመሩ የዴሞክራሲ ባህል ግንባታ ወደፊትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉም እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡

በተለይ በአገሪቱ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት እስካሁን የተመዘገቡ ስኬቶች በአዲሱ አመራር ለማስቀጠል በስፋት ተነጋግረዋል፡፡

ዋና ፀሐፊው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ የኢኮኖሚ ኮሚሽንና በአፍሪካ ኅብረት ትብብር አዲስ አበባ ውስጥ ''ወጣቶችና የአፍሪካ ዴሞክራሲ'' በሚል ርዕስ በተዘጋጀ ዐውደ ጥናት እየተሳተፉ ናቸው።
http://www.ertagov.com/amerta/erta-news-archive/49-erta-tv-hot-news-addis-ababa-ethiopia/2464-l-r-.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር