በጃፓን የኢፌዴሪ የክብር ቆንስላ ጽሕፈት ቤት ተከፈተ


አዲስ አበባ፡- በጃፓን ናጎያ ከተማ የኢፌዴሪ የክብር ቆንስላ ጽሕፈት ቤት መከፈቱን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።
የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ ጽሕፈት ቤት ለጋዜጣው በላከው መግለጫ፤ ጽሕፈት ቤቱ በተከተፈበት ወቅት በጃፓን የኢፌዴሪ አምባሳደር ማርቆስ ተክሌ «ኢትዮጵያ ነፃነቷን አስጠብቃ የቆየችና ለጥቁር ሕዝቦች ነፃነትና ፓን አፍሪካኒዝም የጐላ ሚና የተጫወተች ሀገር ናት» ማለታቸውን አስታውቋል። በአሁኑ ወቅትም ሠላምና መረጋጋት የሰፈነባት ከመሆኗም ባሻገር ልማቷን በማፋጠን ድህነትን ድል ለማድረግ እየተንቀሳቀሰች መሆኑ ተጠቁሟል።
እንደ አምባሳደር ማርቆስ ገለጻ፤ የሁለቱ ሀገራት ግንኙነት ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ያስቆጠረ ነው። ጃፓን በጠንካራ አጋርነቷ በተለይም የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪዎች ውጤታማነትን ከፍ በማድረግና በጐ ፈቃደኞችን በመላክ የቴክኒክና ዕውቀት ሽግግር እንዲስፋፋ አስተዋፅኦ እያበረከተች ነው።
በጃፓን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ቪንቺ አሳዙማ በበኩላቸው፤ ጃፓንና ኢትዮጵያ ረጅም ጊዜ የቆየ ጠንካራ ግንኙነት እንዳላቸው አመለክተው፤ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ አካባቢ ሠላምና መረጋጋት እንዲሰፍን እያደረገች ያለው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በቀጣይ በምታዘጋጀው ለአፍሪካ ልማት የቶክዮ ዓለም አቀፍ ጉባኤ ላይም ጠንካራ አስተዋፅኦ እንደሚኖራት ያላቸውን እምነት ጠቁመዋል። የክብር ቆንስላ ጽሕፈት ቤቱ መከፈት ሁለቱ አገራት ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር የራሱ አስተዋፅኦ እንዳለው አመልክተዋል።
በዕለቱ በጃፓን የኢትዮጵያ መንግሥት የክብር ቆንስላ ሆነው እንዲሠሩ የተመረጡት ሚስተር ላዲማቺ ማትሲሞት የሹመት ደብዳቤ የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማን ከአምባሳደር ማርቆስ ተክሌ እጅ ተረክበዋል። 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር