በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ ኢትዮጵያ ቡና እና ሀዋሳ ከነማ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸነፉ


በ7ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መለስ ዋንጫ ህዳር 16/2005  በተለያዩ ከተሞች አምስት ጨዋታዎች ተካሂደዋል።

አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ በ8 ሰዓት ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ሙገር ሲሚንቶ ተገናኝተው 2 አቻ በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል።
ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ታዬ አስማረ እና ሳምሶን ሙሉጌታ ሲያስቆጥሩ ለሙገር ሲምንቶ እስክንድር አብዱአሚድ እና አዲሱ ዋናሮ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
10 ሰዓት ላይ የተደረገው ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮጵያ መድህን ያደረጉት ጨዋታ በኢትዮጵያ ቡና 4 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ለኢትዮጵያ ቡና ታፈሰ ተስፋዬ ፣ሰለሞን ገብረመድህን ፣ቶክ ጀምስ እና ፋሲል አስፋው ጎሎቹን አስቆጥረዋል።አራቱም ጎሎች በመጀመሪያው አጋማሽ ነው የተቆጠሩት።
ኢትዮጵያ መድህን ሁለተኛው ግማሽ ላይ በመሐመድ ናስር የማስተዛዘኛውን ጎል አስቆጥሯል።
በመብራት ኃይል እና በመከላከያ መካከል የተደረገው ጨዋታ 2 ለ 2 በሆነ ውጤት ተጠናቋል። ጨዋታው በተጀመረው በአራተኛው ደቂቃ መብራት ኃይል በበረከት ይሳቅ የመጀመሪያውን ጎል በማስቆጠር መሪ መሆን ቢችልም መከላከያ ሁለት ጎሎችን በዮሐንስ ኃይሉ አስቆጥሮ እረፍት ወጥቷል።
የመብራት ኃይሉ በረከት ጎል ሊሆኑ የሚችሉ አጋጣሚዎች ሳይጠቀምበት ቀርቷል።
ሁለተኛው አጋማሽ ላይ መብራት ኃይል ያገኛትን የፍፁም ቅጣት ምት አዲስ ነጋሽ አስቆጥሮ አቻ ወጥቷል። ሀዋሳ ላይ ሀዋሳ ከነማ የኢትዮጵያ ውሃ ሰራዎችን አስተናግዶ 4 ለ 1 በሆነ ሰፊ ውጤት ሲረታ። ሀረር ቢራ ከሲዳማ ቡና 1 አቻ በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተዋል።
ውጤቱን ተከትሎ ሀዋሳ ከነማ ከቅዱስ ጊዮርጊስ በአንድ ነጥብ ዝቅ ብሎ በ13 ነጥብ በሁለተኛነት የሊጉን ደረጃ ይዟል።
መብራት ኃይል ፣ኢትዮጵያ ቡና ፣ ሀረር ቢራ በእኩል 12 ነጥብ በጎል ተበላልጠው ተከታዮቹን ደረጃዎች ይዘዋል። በፕሪምየር ሊጉ የኢትዮጵያ ውሃ ሰራዎች 3 ነጥብ ለማግኘት የተቸገረ ቡድን ሆኗል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር