በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ለመከላከል የሚያስችል ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ የአለታ ጩኮ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉደዮች ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በወረዳው ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ከተውጣጡ 1ዐዐ በላይ ሰዎች እንዲሁም ከሀይማኖት መሪዎች ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመከላከል ዙሪያ ሰሞኑን ውይይት ተካሂዷል፡፡

የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ ወይዘሮ ሮማን ማሞ እንደገለፁት መንግስታዊ ካልሆኑ በጎ አድራጊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር በሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ያለ እድሜ ጋብቻ፣ ጠለፋና አሰገድዶ የመድፈር ችግሮችን ለመቅረፍ ጥረት እየተደረገ ይገኛል፡፡
ከዚሁ በተያያዘም የቤተሰብ ምጣኔ፣ በሴት ልጅ ግርዛትና በተዛማጅ ችግሮች ዙሪያ ላይ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ትምህርት እየተሰጠ እንደሚገኝ አስረድተዋል፡፡
በአለታ ጩኮ ወረዳ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነ ኡየሱስ የምግብ ዋስትናና ልማት ኘሮጀክት አስተባባሪ አቶ አብርሃም ቲራሞ በበኩላቸው ቤተክርስቲያኗ ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን ከመከላከል ጎን ለጎን የጤና ለማት ሠራዊት ለመገንባት በሚደረገው ጥረት የበኩሏን ድርሻ እየተወጣች እንደምትገኝ መግለፃቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር