ቦርዱ የአካባቢና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች ምርጫ የጊዜ ሰሌዳን ይፋ አደረገ



አዲስአበባ፣ጥቅምት 21፣2005 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ በመጪው ሚያዚያ ለሚካሄደው የአካባቢና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ ይፋ አደረገ።
በቀጣይም የምርጫውን ሂደት በተመለከተ ፥ ከፓርቲዎች ጋር ተከታታይ ምክክሮች እንደሚያደርግም አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ይፋ ያደረገው 22 ክንውኖችን ያካተተ የአካባቢና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤቶች አባላት ምርጫ አፈጻጸም የጊዜ ሰሌዳ ነው።
የቦርዱ ዋና ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና እንዳሉት ፥ ቦርዱ የጊዜ ሰሌዳውን ያጸደቀው  ከ75 የፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በረቂቅ ሰነዱ ላይ ሰፊ ውይይት ካካሄደ በኋላ ነው።
በውይይቱም ፓርቲዎቹ የጊዜ ሰሌዳው የሚያሰራ መሆኑን መግለጻቸውን ያስታወሱት ሰብሳቢው  ፥ የተሰጡ አስተያየቶችን ከግንዛቤ ባስገባ መልኩ የግዜ ሰሌዳው መጽደቁን ነው የተናገሩት።
በግዜ ሰሌዳው በተቀመጡ ት  ክንውኖች መሰረት ወደ ትግበራ እንደሚገባ  የገለጹት ደግሞ የቦርዱ ጽህፈት ቤት ዋና ሃላፊ አቶ ነጋ ዱሪሳ ናቸው።
በዚህም መሰረት የፖለቲካ ፓርቲዎች የመወዳደሪያ ምልክቶቻቸውን ህዳር 14  2005 ቀርበው የሚወስዱ ሲሆን ፥ የየምርጫ ክልሉ ጽህፈት ቤቶች ደግሞ ህዳር 24  ቀን 2005  ተከፍተው ስራቸውን የሚጀምሩ ይሆናል።
የመራጩ ዝብ ፣ የየፖለቲካ ፓርቲዎች እጩዎች ፣ እንዲሁም የግል እጩ ተወዳዳሪዎች  ምዝገባ ከታህሳስ 22 እስከ ጥር 21 2005  ይሆናል።
የከተማ ፣ የወረዳና የቀበሌ ምክር ቤት ምርጫ የድምጽ ቆጠራ በየምርጫ ጣቢያው የሚከናወንበት እለት ሚያዚያ 6 ከምሽቱ 12 ሰኣት ጀምሮ ሲሆን ፥ ሚያዚያ 7 ደግሞ በየምርጫ ጣቢያው ውጤት ለህዝብ ይፋ ይሆናል።
በመጨረሻም የአካባቢ ምርጫ አጠቃላይ ውጤት በብሄራዊ ደረጃ በምርጫ ቦርድ ለህዝብ ይፋ የሚደረግ ሲሆን ፥ በቀጣይም የምርጫውን ሂደት በተመለከተ  ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር ተከታታ ይ  ምክክር እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ብሄራዊ የምርጫ ቦርድ አስታውቋል።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር