የህዳሴ ግድብ በተያለዘት ጊዜ እንዲጠናቀቅ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት መወሰናቸውን የወንዶ ገነት ወረዳ የወጣቶችና የሴቶች ሊግ ገለፀ፡፡

የ2ዐዐ4 ዓ/ም የስራ ክንውን በመገምገም በተያዘው የበጀት አመት አበይት የትኩረት አቅጣጫዎችን ለይተው ተቀናጅተው ለመስራት ከስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ለአንድ ቀን ባካሄዱት የወጣቶችና ሴቶች ሊግ የጋራ ስብሰባ ባለፈው አመት ባከናወኗቸውና በቀጣይ በሚሰbቸው አበይት ስራዎችን ለአባላቱ በማቅረብ ተወያይተውበታል፡፡
በዚህም የወጣቶች ሊግ በተጠናቀቀው አመት በከተማ የስራ አጥነት ችግር በቁጠባ፣ በአካባቢ ፅዳት ስራዎች የበጎ አገልግሎት ላይ ወጣቶች በስፋት እንዲሳተፉ ተደርጓል፡፡
በገጠር ወረዳው ያለውን ምቹ የመሰኖ አቅምን  በዘመናዊ መንገድ እንዲጠቀሙ ግንዛቤ መፍጠር መቻላቸውን የወረዳው ወጣቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሙሴ ሙዴ ገልፀዋል፡፡
በተመሳሳይ የወረዳው ሴቶች ሊግ ጽህፈት ቤት ኃለፊ ወይዘሮ ድንቅነሽ ደግፌ እንዳሉት የወረዳው ሴቶች በተለይም የገጠር ሴቶች በሰብልና በእንስሳት ሀብት ዘርፍ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ተጠቃሚ እንዲሁኑ ስራዎችን በመስራት ምርታማ ለማድረግ ተንቀሳቅሰናል ይላሉ፡፡

የሁለቱ ሊጐች አባላት በተደረገ ውይይትም የ2ዐዐ5 የትኩረት አቅጣጫ ላይ ከመግባበት የደረሱ ሲሆን በጋራ ሆነው የተጀመሩ ስራዎች ቀጥሏል ብለዋል፡፡
በተጨማሪም የህዳሴው ግድብ በተያለዘት ጊዜ እንዲጠናቀቅ ከወጣቶችና ሴቶች ሊግ የሚጠበቅባቸውን ለመወጣት መወሰናቸውን አቶ ሙሴ ተናግረዋል፡፡
ሌላው ትልቁተግባራቸውም በቀጣይ በሚከናወነው ማሟያ ምርጫ ላይ እነዚህ አካላት ከዚህ ቀደም ከከነበራቸው ተሳትፎ በላቀ ደረጃ እንደሚሳተፉ ም ተስማሟተዋል፡፡
የወረዳው ዴህዴን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኤርሚያስ ደበላ በበኩላቸው ሊጐቹ ለወጣቶችና ሴቶች ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ትልቅ ኃላፊነት እንዳለባቸው በማሳሰብ በቀጣይ ደካማ አፈፃፀማቸውን በማረም ጠንካራ ጎናቸውን በማጠናከር መስራት እንዳለባቸው አስገንዝበዋል፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/04HidTextN105.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር