ዓለም አቀፍ የቡና ጉባዔ ይካሄዳል


አዲስ አበባ፡- የመጀመሪያው ዓለም አቀፍ የኢትዮጵያ ቡና ጉባዔ በአዲስ አበባ ለሁለት ቀናት እንደሚካሄድ ኢትዮጵያን ኮፊ ኤክስፖርተስ አሶሴሽን አስታወቀ።
አሶሴሽኑ ለዝግጅት ክፍላችን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ «የቡናችን መገኛ ታሪካችንን ማጠናከር» በሚል መሪ ሃሳብ ጥቅምት 29 እና 30 ቀን 2005 ዓ.ም በአዲስ አበባ ሒልተን ሆቴል በሚካሄደው በዚህ ጉባዔ ከ250 በላይ ተሣታፊዎች ይገኛሉ።
ከንግድ ሚኒስቴርና ሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር የሚካሄደው የዚህ ጉባዔ ዓላማ የኢትዮጵያ ቡና በዓለም አቀፍ ገበያ ውስጥ የሚኖረውን ድርሻ ማሳደግ በሚያስችሉ ስልቶች ላይ ለመወያየትና መረጃና ልምድ ለመለዋወጥ ነው።
ባለድርሻ አካላት በቡና ዓለም አቀፍ ግብይት ላይ ስላሉት ዕድሎችና ተግዳሮት በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ እና የኢትዮጵያን ቡና ልዩ ጣዕም በማስተዋወቅ ረገድ መጫወቱ ስለሚገባቸው ሚና እንዲያውቁ ለማድረግ ታስቦ መዘጋጀቱንም መግለጫው አመልክ ቷል።
በጉባዔ በቡና ንግድ ዘርፍ ላይ ዋነኛ ተዋንያን የሆኑትን ላኪዎች፣ አቅራቢዎች፣ ወኪሎች፣ ማኅበራት፣ የክልል ግብርና ቢሮዎች፣ የንግድ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ፣ የግብርና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ባለሥልጣን፣ የአካባቢ የፋይና ንስ ተቋማት፣ ዓለም አቀፍ ቡና ገዥ ኩባንያዎች ይሣተፋሉ።
የዓለም አቀፉ የቡና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ሮቤይሮ ኦሊቬይራ ሲልቫ፣ የአውሮፓ ሕብረት ልዑክ መሪ እና በኢትዮጵያ የዩኤስ ኤይድ ዳይሬክተር በጉባዔው ላይ ተገኝተው ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
«ወደ ውጭ የሚላከው ቡና በ25 በመቶ የሚጨምር፣ መጠኑም ከ200ሺ ቶን በላይ፣ የሚገኘው የውጭ ምንዛሬ አንድ ቢሊዮን ዶላር እንደሚልቅ ይጠበቃል» ሲል መግለጫው አመልክቷል። 

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር