የመልካም አስተዳደር ችግር -ያልተሻገርነው የዕድገት ማነቆ


ብሩክታይት ፀጋዬ

በእኛ ሀገር በአንድ ወቅት ደመቅ በሌላ ጊዜ ደግሞ ድብዝዝ የሚሉ ጉዳዮች በርካታ ናቸው፡፡ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ስለተናገሩትና በመገናኛ ብዙሃን ስለ ተቀባበሉት ብቻ ሞቅ የሚሉ ጉዳዮች በርካታ ናቸው፡፡ አንዳንዴ ሞቅታው በቃላት ብቻ ሳይሆን በተግባርም ይገለጻል፡፡ ከእነዚህ አንድ ወቅት ያዝ ሌላ ጊዜ ደግሞ ለቀቅ ከምናደርጋቸው ብዙ ጉዳዮች አንዱ የመልካም አስተዳደር ጉዳይ ነው፡፡
በአንድ ወቅት ስለ መልካም አስተዳደር ብዙ ብዙ ተባለ፡፡ በእርግጥ ይህ ጊዜ ማን አገልጋይ ማን ደግሞ ተገልጋይ እንደሆነ ጥርት ያለ ግንዛቤ የተያዘበትና በመልካም አስተዳደር ረገድ አንድ ወሳኝ ምዕራፍ የተሸጋገርንበት በመሆኑ ጉዳዩ መነሳቱ በራሱ መልካም ነገር ነው ማለት ይቻላል፡፡ ጉዳዩ በመነሳቱ «ደንበኛ ንጉሥ ነው» አመለካከትን ለማዳበርም ተችሎ ነበር፡፡ የዛሬን አያድ ርገውና፡፡
«የት መሄድ ይፈልጋሉ?»ከሚለው አቅጣጫ ጠቋሚ ጀምሮ የሠራተኞችን ስም በየቢሮው በር ላይ መለጠፍና ባጅ እንዲያን ጠለጥሉ እስከማድረግ፣የቅሬታ ሰሚ አካላት በማቋቋም ተጠያቂነት ያለው አሠራር እስከማስፈን እሰየው የሚያሰኙ በጐ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ከዓመታት በፊት የተተከሉት የአስተሳሰብና የአሠራር ሥርዓቶች አሁንም ቀጥለውና ተጠናክረው የሚተገበሩባቸው ተቋማት እንዳሉ ሁሉ እነዚህ የሕዝብ አገል ጋይነት መገለጫዎች ለሙሰኞችና ለመልካም አስተዳደር ጠንቆች ሽፋን ሲሰጡም ተመል ክተናል፡፡
ተጠቃሚዎችን በአግባቡ ማስተናገድ ዓላማቸው አድርገው ከሚንቀሳቀሱ እንደ ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ዓይነት ተቋማት እንዳሉ ሁሉ አንዴ መልካም ሌላ ጊዜ ደካማ አፈፃፀም እያሳዩ በአንድ ወቅት ደመቅ ብለው ሌላ ጊዜ ደግሞ ሸርተት ሲሉ የምናያቸው ተቋማትም መኖራቸው የማይካድ ነው፡፡ ሌሎቹ ደግሞ የሕዝብ ተቋምነታቸው ቀርቶ ወደ ግለሰብና ቡድን ተቋማትነት የተቀየሩ እስኪመስለን ድረስ ሕዝብን በሕግና በሕግ አግባብ ከማገልገል ይልቅ ከራስ ጥቅምና ጉዳት አንፃር እየመዘኑ ሕዝብን የሚያጉላ ሉትም ቁጥራቸው የትየለሌ ነው፡፡
በተለይም በክፍለ ከተሞችና ወረዳዎች አካባቢ የመልካም አስተዳደር ጉድለት እጅግ ጐልቶ ይታያል፡፡ እነዚህ ሕዝብን በስፋት የሚያስተናግዱ ተቋማት «የት መሄድ ይፈልጋሉ?» ከሚለው ጀምሮ ዓላማቸውን፣ ራዕያቸውንና ግባቸውን በግልጽ በሚታይ ቦታ ለመግለጽ የቀደማቸው አልነበረም፡፡ በእርግጥ በአንድ ወቅት ሕዝቡን በሥርዓትና በአግባቡ ለመምራትና ለማገልገል የተደረጉ ጥረቶች እንዳሉ መካድ አይቻልም፡፡ እንዲያውም አንዳንዶቹ ክፍለ ከተሞች «እንኳን ደህና መጣችሁ»የሚሉ ባነሮችን ለጥፈው እንደ ነበርም አስታውሳለሁ፡፡ አሁን አሁን ግን በክፍለ ከተሞችና በወረዳዎች የሚታየው የመልካም አስተዳደር ችግር ወደከፋ አቅጣጫ መሄዱን በድፍረት መናገር ይቻላል፡፡
ወደ አንዳንድ ክፍለከተሞችና ወረዳዎች ጉዳይ ለማስፈጸም ሲሄዱ እጃቸውን ወደኋላ አጣምረው በታላቅ ትህትና የሚቀበሉና ጉዳይዎን በጥሞና የሚያዳምጡ ኃላፊዎችና ሠራተኞች አጋጥሞዎት ደስ ብለዎት ይሆ ናል፡፡ ግና ይህ በትህትና የቀረበል ዎት ባለሙያ ያጋጠመዎትን ችግር ጥርት አድርጐ ከሰማ በኋላና የሚፈልጉትን አገልግሎት ከተረዳ በኋላ ችግ ርዎን በመፍታት ፈንታ አወሳስቦና አስደንግጥዎት ቁጭ ይላል፡፡ ሕጋዊነትዎን እያወቁ ሕገወጥነትዎን እንዲያምኑ ነገሮችን ከጠበቁት በላይ አወሳስቦ እጁ ላይ ይጥልዎታል፡፡
በእዚህ መሰሉ ወጥመድ ውስጥ የወደቁ ባለጉዳዮች ጉዳያቸውን ለማስፈጸም ሊወስድ ባቸው የሚችለውን ጊዜና የተወሳሰበ ጉዳያቸውን ከግምት ውስጥ አስገብተው በሕገወጥ መንገድ ጉዳያቸውን ለማስፈጸም ረጅም ርቀት ይሄዳሉ፡፡ ቀድሞውኑ ይህ እንደሚሆን የሚያውቁት ባለሙያዎች በውስጣቸው እየሳቁ በአደባባይ ግን ለሕግ የቆሙና ከአሠራሩ ውልፍት እንደማይሉ አጋንነውና አብዝተው እየተናገሩ ዋጋቸውን ከፍ ለማድረግ ይሞክራሉ፡፡ በእዚህ መልክ መጓዝ የማይፈልግ ባለጉዳይ ካለ «ፋይሉ ጠፍቷል፣አዲስ መመሪያ ይጠብቁ፣ ብዙ የሚጣሩ ጉዳዮች አሉ...» በሚሉና በሌሎችም አስደንጋጭ መልሶች እየተሸማቀቀ ለዓመታት እንዲጉላላ ይደረጋል፡፡
ቀደም ሲል የመልካም አስተዳደር ችግሩ ገና ከበር ጥበቃው ጀምሮ አፍ አውጥቶ ይናገር ነበር፡፡ ጥበቃው«አይቻልም» ብሎ የመመለስ በአጭር አነጋገር ውሳኔ የመስጠት አቅም ነበረው፡፡ አሁን ደግሞ በታላቅ ትህትና ተቀብሎ ማብቂያ በሌለው የችግር ማዕበል የማላጋቱ ትርዒትና ድራማ የመያተኞች ድርሻ ሆኗል፡፡
በአገር ደረጃ የመልካም አስተዳደር ችግር ልዩ ገፅታ ይዞና ገዝፎ ይታያል፡፡ በተለይም በከተሞች አካባቢ ካለው ከፍተኛ ዕድገት ጋር ተያይዞ የመልካም አስተዳደር ችግሩም አብሮ እያደገ መጥቷል ማለት ይቻላል፡፡
አገራችን በሁለንተናዊ መልኩ ከፍተኛ ዕድገትን እያስመዘገበች መሆኗን ተረድቶ ግንዛቤው ከዳበረና በእውቀት ከደረጀ ሠራተኛ ጀምሮ ይህንን በዕድገት ጐዳና ላይ የሚገኝ የኅብረተሰብ ክፍል ለማስተናገድ በሚያስችል ደረጃ መዘጋጀት ከመንግሥት ተቋማት የሚጠበቅ ነው፡፡ አሁን የሚታየው ግን በተቃራኒው ነው፡፡ የሚሰጠው አገልግሎት በቂና ቀልጣፋ ካለመሆኑ ጋር በተያያዘ የሙስና በሮች እየሰፉ ባለጉዳዮችን የማንገላ ታት ዕድሉም እየጨመረ መጥቷል ለማለት ያስደፍራል፡፡
በቴክኖሎጂ የዳበሩ ተቋማትን ካለመገን ባትና ቴክኖሎጂውን በአግባቡ ሊጠቀም የሚችል የሰው ኃይል ካለማሰማራት ጋር በተያያዘ ተጠቃሚዎች በቂና ቀልጣፋ አገልግሎት እያገኙ አይደለም፡፡ ወደ መንግ ሥት ካዝና ገንዘብ ለማስገባት የሚመጡትን ተገልጋዮች አሰልፎ ወረፋ ማስጠበቅና ሆነ ተብሎ እንዲማረሩ ማድረግ ነው፡፡ ለእዚህ እንደ ምሳሌ ሊወሰድ ይቻላል፡፡ 
«አገራችንን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ተርታ እናሰልፋለን» የሚል ራዕይ ተይዞ ልማቱ በሚጧጧፍበት ሀገር ቀርፋፋ፣ በሙስናና በመልካም አስተዳደር ችግር በተተበተበና በታጠረ አገልግሎት አሳጣጥ የሚፈለገውን ያህል ርቀት መሄድ አዳጋች ይሆናል፡፡ ኢኮኖሚያዊ ዕድገቱ እየቀደመንና ከምንችለው አቅም በላይ እየፈጠነ መሆኑን ተገንዘብን አሠራራችንን ካላስተካከልን የሚፈለግበት ደረጃ ለመድረስ እጅግ እንቸ ገራለን፡፡ በተለይ ደግሞ በሐቅና በታማ ኝነት፣ ከመሥራት ይልቅ ግላዊ ተጠቃሚነትን በማሳደድ ጊዜያችንን ስለምናጠፋም አግባ ብነት ያለውን ሥራ ለማከናወን ጊዜ ያጣን የምንመስልም ብዙዎች ነን፡፡
ብዙዎች በአገራችን ድህነትና ኋላቀርነት ሲቆጩና ሀገራቸውን እንደሚወዱ ሲናገሩ ይደመጣሉ፡፡ ነገር ግን ይህንን ችግር ከላይዋ ላይ ለማንሳት ከመረባረብ ይልቅ በአብዛኛው እላዩዋ ላይ ሲጫኗት ነው የሚስተዋለው፡፡ ድህነትና ኋላቀርነት ሳያንሳት ተጨማሪ ጫና አገሪቷ ላይ ሲፈጥርና አንገቷን ሲያስደፋት የሚታየው መብዛቱ ቃልን ተግባር አራምባና ቆቦ መሆናቸውን ያመለክታል፡፡
አገርን መውደድ ማለት ሕዝብን መው ደድ ማለት ነው፡፡ ሃገርን ማገልገል ማለት ሕዝብን ማገልገል ማለት ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ከአፋቸው ወደ እጃቸው የማይ ወርድላቸው ብዙዎች ናቸው፡፡ ሃገርን ማገልገል ወጥቶ መግባት ብቻ የሚመስላ ቸውም ብዙዎች ናቸው፡፡ ሃገር በማገልገል ስም ሃገርን የሚበድሉ በርካቶች ናቸው፡፡ ጠብታ ውሃ ዋጋ እንዳላት ሁሉ የእያንዳን ዳችን ሥራ ለሃገር ልማትም ሆነ ውድቀት ጠጠር እንደምታ ቀብል የማይገነዘቡም ጥቂቶች አይደሉም፡፡ 
በቅርቡ ቃል የገባንለት የታላቁ መሪ ውርስም እንዲሁ በዘልማድ ወደ መሆን እንዳይቀየር እሰጋለሁ፡፡ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ በሞት ከተለዩን በኋላ በዕንባው ሲራጭ የነበረው ሁሉ የእርሳቸውን ራዕይ ለማሳካት ቃል ገብቷል፡፡ የእርሳቸውን አርአያነት ለመከተልም ብዙ ብዙ ብሏል፡፡ አንዳንድ የመንግሥት ተቋማትም ከስም ንት ሰዓቱ የሥራ ሰዓት ገፋ አድርገው ሕዝብ ሊያገግሉ ቃል መግባታቸውን ሰምቻለሁ፡፡ ይህ ይበል የሚያሰኝ ቢሆንም እስከ ምሽት ድረስ ቢሮ ከፍቶ ተገልጋይ መጠበቁ ብቻ ዋጋ እንደሌለው መታወቅ ይኖርበታል፡፡ የምንሠራው ሥራ በንፅሕና ላይ፣በቅንነት ላይ፣ በመልካም አስተዳዳር ላይ የተመሠረተ ስለመሆኑ ማረጋገጥ አለብን፡፡ አልያ ሕዝብ ለማን ገላታት እስከ ምሽት ቢሮ ክፍት ማድረግ ላያስፈልግ ይችላል፡፡ እንደእኔ እንደእኔ የሥራ ሰዓት የማራዘሙ ጥሩነት እንዳለ ሆኖ ከእዚያ ይልቅ ግን በመደበኛው የሥራ ሰዓት ምን ያህል ከሙስና ከብልሹና አድሏዊ አሠራር የፀዳ ሥራ አከናውነናል? የሚለውን መፈተሹ መቅደም ያለበት ይመስለኛል፡፡
የቀድሞ ጠቅላይ ሚነስትር መለስ ዜናዊ አርአያነት በቀላሉ በቃላችን ተናግረን የምናልፈው አይደለም፡፡ ከእርሳቸው ጥልቅ የሃገርና የሕዝብ ፍቅር ጥቂቱን እንኳን መታደል ይጠይቃል፡፡ ከእርሳቸው ገደብ የሌለው መስዋዕትነት ጥቂቱን እንኳን ለመክፈል ድፍረትን ይጠይቃል፡፡ የእርሳ ቸውን ንፅሕና ያክልም ባይሆን ታማኝነትን ማረጋገጥ ያስፈልጋል፡፡ የእርሳቸውን ያህል ባይሆንም ያለመታከት ለሕዝብ መሥራትን መቀበልን ይጠይቃል፡፡
የእርሳቸውን አርአያ መከተልና ራዕያቸ ውን ከግብ የማድረስ ጉዳይ ጥልቅ ትርጉም ያለው ነው፡፡ እንደ እርሳቸው እስከመጨ ረሻው መሞትንም ባይሆን ትንሽ ትንሽ መሞትን ይጠይቃል፡፡ የታላቁን መሪ ውርስ ማስቀጠል በአማረ ቋንቋ መግለጽ ብቻውን ዕምባ አያብስም፡፡ በምንናገረው ልክ ለሕዝብ ቅንና ታማኝ ሆነን እንድንገኝ ግድ ይለናልና፡፡
በመልካም አስተዳደር ችግር በእዚህም በእዚያም ታጥረን እርሳቸው ያለፉለትን ዓላማ ከግብ እናደርሳለን ማለት ቀልድ ነው የሚሆነው፡፡ ስለዚህ ከልማት ሥራዎቻችን ጐን ለጐን የመልካም አስተዳደር ችግርን በዋነኛነት መታገልና ማጥፋት አለብን፡፡
በተለይም የዴሞክራሲ ተቋማት ተጠና ክረው ይህንን በሃገሪቱ ዕድገትና በሕዝቦቿ ብልጽግና ላይ ቀይ መብራት የሚያበራውን ጉዳይ ሊያስወግዱ ይገባል፡፡ ጠንካሮችና ተጋፋጮች መሆንም ይጠበቅባቸዋል፡፡ የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋምን ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን፣ ሥነ ምግባርና ፀረ ሙስና ኮሚሽን መሠረት የያዘ ሥራ ማከናወን ይኖርባቸ ዋል፡፡ የችግርን ዳርዳር ብቻ ሳይሆን መሃ ሉንም መነካካት ይጠበቅባቸዋል፡፡
መንግሥት ዘንድሮ ዋናው ትኩረቱ መልካም አስተዳደር ጉዳይ እንደሆነ አሳው ቋል፡፡ አንዳንድ ኃላፊዎችና ባለሥልጣኖች ደግሞ ፀሐይ የሞቀውን እውነታ በአደባባይ ለመካድ መሞከራቸው ብዙዎችን ያሳዘነ ጉዳይ ነው፡፡ መንግሥት መልካም አስተዳደር ላይ ትኩረት የሚሰጠውን እንዲያው ዘልማድ ሆኖበት አይመስለኝም፡፡ ችግሩ ስር መስደዱን ተገንዝቦ እንጂ፡፡ ችግሩ በመንግሥት እና በሕዝብ የልማት ፍላጐት ላይ የተደቀነ ጋሬጣ ነው፡፡ በአንድ ወቅት የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ«ወይ ሕጋዊነት ያሸንፋል፤ወይ ኪራይ ሰብሳቢነት ያሸንፋል» ብለው ነበር፡፡ እርሳቸው በሕይወት በነበሩበት ወቅት ይህንን ጋሬጣ ታግለውታል፡፡ ዛሬም እኛ የእርሳቸውን ሌጋሲ (ውርስ) እናስቀጥ ላለን የምንል ሁሉ ልንታገለው የሚገባን ባላንጣችን ነውና ወገባችንን ጠበቅ እናድርግ፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር