የክልሉ መንግስት በሁሉም አካባቢዎች ፍትሀዊ የሀብት ክፍፍልና የመሠረተ ልማት ዝርጋታን ለማረጋገጥ እየሠራ መሆኑን የደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ክቡር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ አስታወቁ፡፡




ከአራት የአውሮፖ አገራት ፓርላማዎች የተውጣጡ ልዑካን ቡድን አባላት በክልሉ በአውሮፖ ህብረት ድጋፍ እየተሠሩ ያሉ ሥራዎች ውጤታማ እንደሆኑ ተናግረዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ፣ም/ርዕሰ መስተዳድርና ግብርና ቢሮ ኃላፊና ከክልሉ ምክር ቤት ኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት ጋር መክረዋል፡፡
ዝርዝሩ የደቡብ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ነው፡፡
በአውሮፖ ህብረት የገንዘብ ድጋፍ በኢትዮጵያ የሚካሄዱ የልማት ኘሮጀክቶችን እንስቃሴ ለማየት ከሀንጋሪ፣ ክቼክ ሪፓብሊክ ፣ ከሶሎቫኪያና ከፖላንድ ፓርላማዎች የተወከሉና የልማት ድርጅቶች ተወካዮች ጉብኝት እያደረጉ ናቸው፡፡
የልዑካኑ ቡድን አባላት ከደቡብ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጋር ተወያይተዋል፡፡
በወቅቱ ርዕሰ መሰተዳድሩ እንዳሉት የክልሉ መንግስት በሁሉም የልማት ዘርፎች የክልሉን አካባቢዎች እኩል ተጠቃሚ ለማድረግ እየሠራ ነው፡፡
ባለፉት አመታት በክልሉ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌያት የህፃናትን ሞትን ለመቀነስ ተችሏል፡፡ ከ6ዐዐ በላይ ጤና ጣቢያዎችም ተገንብተው አገልግሎት እየሠጡ ናቸው፡፡
አርሶ አደሩ በቂ ምርት እንዲያመርትና ራሱን ከመመገብ አልፎ ለገበያ እንዲያቀርብ የተደረገው ጥረት ውጤታማ መሆኑን አቶ ሽፈራው ተናግረዋል፡፡

በሀገሪቱ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት የሚያሰችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸሉ ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ በ2ዐዐ5 ዓ/ም 65ዐ ሚሊዮን ብር በመመደብ ንፁህ የመጠጥ ውሃ ለህብረተሰቡ ለማቅረብ እየተሠራ ያለውን ለአብነት አንስተዋል፡፡
በቼክ ሪፓብሊክ ኤምባሲ የልማት ተልዕኮው ምክትል ኃላፊ ሚስስ ጃና ኮርቤሎቫ እንዳሉት በክልሉ የሚደረጉ የልማት ሥራዎች ውጤታማ ናቸው፡፡ እነዚህን በ9 ወረዳዎች በግብርና፣ በትምህርት ፣ በጤና በአቅም ግንባታ የተጀመሩ ሥራዎችን በሌሎችም አካባቢዎች ለማስፋፋት ጉብኝቱ ምቹ አጋጣሚ ይፈጥራል ብለዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ በክልሉ ምክር ቤት ኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴና ከግብርና ቢሮ ኃላፊ ጋርም ተወያይተዋል፡፡ በወቅቱም ስለ ክልሉ አጠቃላይ ገፅታና በቼክ መንግስት በክልሉ የሚሠሩ የግብርና ሥራዎችን በተመለከተ በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ ሳኒ ረዲኢ አማካይነት ማብራሪያ ተሰጥቷቸዋል፡፡
በአውሮፓ ህብረት የሚደገፉ የልማት ድርጅቶች በግብርና ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ በምርምር ፣ በአቅም ግንባታና በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ ላይ የሚያደርጉትን ድጋፍ እንዲያሰፉ አቶ ሳኒ ጠይቀዋል፡፡
የልዑካን ቡድኑ አባላት ጉብኝት ለአንድ ሳምንት ይቆያል ፡፡ በተለያዩ አካበቢዎች የሚተገበሩ ኘሮጀክቶች በአግባቡ መስራታቸውንና ድጋፍ ለታለመለት አላማ መዋሉን ይገመግማሉ ፡፡
በክልሉ የተደረገው አቀባበልና እየተሠራ ያሉ ሠራ እንዳስደሰታቸው የቡድኑ አባላት ተናግረዋል፡፡ ዘገባው የደቡብ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ነው፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/06HidTextN105.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር