በደቡብ ክልል በከተሞች ለነዋሪዎች ስኳር ስንዴና የምግብ ዘይት ተከፋፈለ

አዋሳ ጥቅምት 22/2005 በደቡብ ክልል ከተሞች ገበያን ለማረጋጋት ባለፉት ሶስት ወራት 27ሺህ 475 ኩንታል ስኳርና ስንዴ እንዲሁም ከ613ሺህ ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለተጠቃሚው መከፋፈሉን የክልሉ ግብይትና ህብረት ስራ ቢሮ ገለፀ፡፡ የቢሮው የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሂደት ባለቤት አቶ መላኩ እንዳለ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የፍጆታ ሸቀጦቹ የተከፋፈሉት ሀዋሳን ጨምሮ በክልሉ ከተሞች በሚገኙ 133 የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ነው፡፡ ከተከፋፈለው መካከል 19ሺህ 345 ኩንታል ስኳር፣ 8ሺህ 130 ኩንታል ስንዴና ከ613ሺህ ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለአባላትና ለአካባቢው ህብረተሰብ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ባለፉው የበጀት ዓመትም በ123 የሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት አማካኝነት ከ2 ነጥብ 5 ሚልዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት፣ ከ533ሺህ ኩንታል በላይ ስኳር ፣ የምግብ እህልና የተለያዩ ሸቀጦች በተመሳሳይ ለተጠቃሚዎች መከፋፈሉን ገልጸዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር