በሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ በየደረጃው ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ለማሠራጨት ግብ ጥሎ እየሠራ መሆኑን የወረዳው ኦሞ ማክሮ ፋይናንስ ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡


በሲዳማ ዞን ሎካ አባያ ወረዳ በየደረጃው ከ26 ሚሊዮን ብር በላይ ለማሠራጨት ግብ ጥሎ እየሠራ መሆኑን የወረዳው ኦሞ ማክሮ ፋይናንስ ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ደሳለኝ ሀይለኢየሱስ እንደገለፁት መንግስት የዜጎችን የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል በነደፈው ስትራቴጂ መሠረት በተያዘው በጀት ዓመት 1ዐ ሚሊዮን ብር ብድር ለማሰራጨት እና 18 ሚሊዮን ብር ከቁጠባ ለመሰብሰብ አቅዶ እየሰራ ነው፡፡

ንዑስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ከንግድና ኢንዱስትሪ ጽህፈት ቤት ጋር በመተባበር ከተለያዩ ዩንቨርስቲዎችና ኮሌጆ  ለተመረቁ  ተማሪዎችን ከ5 መቶ ሺህ ብር በላይ የብድር አገልግሎት ለመስጠት ማቀዱን ገልፀዋል፡፡
በተያዘው እሩብ በጀት ዓመት 3 ሚሊዮን 6 መቶ ሺህ ብር ብድር ማሰራጨቱንና መቶ ሺህ ብር ቁጠባ መሰብሰብ መቻሉን ጠቁመው 6 ሺህ 8 መቶ የሚሆኑ የህብረተሰቡ ክፍሎች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ መሆናቸውን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል ሲል ሪፖርተር አካሉ ጥላሁን ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር