የእጭዎችና የመራጮች ምዝገባ ከታህሳስ 22/2005 ጀምሮ ይካሄዳል


አዲስ አበባ፤   ጥቅምት 28/ 2005 (ዋኢማ) - ለአራተኛውን  የአካባቢና የአዲስ አበባ   ምርጫ የእጩዎችና የመራጮች ምዝገባ  ከታህሳስ   22 እስከ ጥር 21/2005 ዓ/ም እንደሚካሄድ   ምርጫ ቦርድ አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ  ምርጫ ቦርድ   የህዝብ  ግንኙነት   ማስተባበሪያ   ኋላፊ   ወይዘሮ   የሺ ፈቃድ   ለዋልታ   እንደገለጹት በ2005 ለሚካሄደው የአዲስ አበባ ምክር ቤትና የአካባቢ ምርጫ  የእጩዎችና የመራጮች ምዝገባ  በወጣው የጊዜ ሰሌዳ ለማከናወን ከወዲሁ አንዳንድ ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው።

እንደ ሃላፊዋ ገለጻ ከዚህ   በፊት  የተደረጉትን   የአካባቢ   ምርጫዎችን     በመገምገም የነበሩባቸውን ጥንካሬዎችና ድክመቶችን በመለየት  የዘንድሮውን ምርጫ  በተሻለ   መልክ ለማጠናቀቅ  ቦርዱ  ዝግጅቱን እያጠናቀቀ ነው።፡

ቀደም ሲል የመራጮች   የስነ  ዜጋ   ትምህርት  መሥጫ  መመሪያ አለመኖሩን  ያስታወሱት ወይዘሮ  የሺ  ለ2005 ዓ/ም  የአካባቢ   ምርጫ   የዜጎች  የስነ    ዜጋ  መመሪያ   በ13  የተለያዩ  ቋንቋዎች ተቀርጾ  ሥልጠና  እየተሰጠ   ይገኛል  ብለዋል፡፡ � 

የባለድርሻ   አካላት አቅም   አለመገንባት አንዱ ችግር እንደሆነ  የጠቆሙት ወ/ሮ  የሺ    ችግሩን   ለመቅረፍም  ቦርዱ  ለፖለቲካ   ፓርቲዎች   የምክክር   መድረክ   በማዘጋጀትና የተለያዩ  ሥልጠናዎችን በመሥጠት   ላይ   እንደሚገኙ    ገልጸዋል ፡፡ 

እንደ ሃላፊዋ ገለጻ      በ2005ቱ   የአካባቢ   ምርጫ የሴቶችን   ተሳትፎ    ለማሳደግ   የሚያስችሉ   ሥልጠናዎች   ከተለያዩ   የሴቶችና የወጣቶች አደረጃጀቶች ጋር  በመተባበር  ስልጠና  እየተሰጠ  መሆኑን   ገልጸዋል ፡፡
http://www.waltainfo.com/index.php?option=com_content&view=article&id=6097:-222005-&catid=80:2011-09-07-15-03-51&Itemid=399

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር