በሲዳማ ዞን ከ12 ሚልዮን ብር የሚበልጥ ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው ስራ ጀመሩ


አዋሳ ጥቅምት 22/2005 በሲዳማ ዞን ባለፉት ሶስት ወራት ከ12 ሚልዮን ብር የሚበልጥ የኢንቨስትመንት ካፒታል ያስመዘገቡ ባለሃብቶች ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ መሰማራታቸውን የዞኑ ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ ገለጸ፡፡ በመምሪያው የኢንቨስትመንት ማስፋፊያ ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ብርሃኑ ወልደሚካኤል ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በመጀመሪያ ሩብ ዓመት አራት ባለሃብቶች ፈቃድ በማውጣት ስራ ጀምረዋል፡፡ ባለሃብቶቹ ከተሰማሩባቸው የስራ መስኮች መካከል አገልግሎት መስጫ ተቋማት፣ ግብርናና ኢንዱስትሪዎች እንደሚገኙበት አስታውቀው ባለሃብቶቹ በጀመሩት የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ለ88 ቋሚና 894 ዜጎች ጊዜያዊ የስራ ዕድል ማግኘታቸውን ገልጸዋል። አንዳንድ ከተሞች ላይ ባለፈው ዓመት የተጀመረው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከአምስት ሺህ ለሚበልጡ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠራቸውን አስታውቀዋል፡፡ መምሪያው ለ12 ባለሃብቶች የፈቃድ እድሳትና ተጨማሪ የማስፋፊያ ፈቃድ መሰጠቱን ጠቁመው ከዚህ ቀደም ቦታ ወስደው ወደ ስራ ያልገቡ ባለሃብቶችን በመከታተልና ድጋፍ በመስጠት በፍጥነት ወደ ስራ የሚገቡበትን ሂደት ለማመቻቸት ባደረገው ጥረት 32 ፕሮጀክቶች የአገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል ብለዋል፡፡ በሲዳማ ዞን ባለፈው በጀት ዓመት ከ267 ሚልዮን ብር በላይ ካፒታል ያስመዘገቡ 56 ባለሃብቶች በተለያዩ መስኮች የተሰማሩ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ብርሃኑ በተለይ በይርጋዓለም፣ በወንዶ ገነት፣ በሸበዲኖ፣ በለኩና በበንሳ ከተሞች የሚታየው የባለሃብቶች የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አዲስ ፈቃድ ወስደው ወደ ስራ ከገቡት ባለሃብቶች መካከል አቶ ብርሃኑ አድማሱና ወይዘሪት ሶፋኒት አምዴ ልማታዊ መንግስት ለግል ኢንቨስትመንት እያደረገ ያለው ድጋፍ በርካታ ባለሃብቶች በሀገር ውስጥ እንዲፈጠሩ ከማድረጉም ባሻገር በድህነት ላይ ለሚደረገው ትግል የራሳቸውን አሻራ በማሳረፍ ለብዙዎች የስራ ዕድል እንዲፈጠር ከፍተኛ እገዛ ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=3103

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር