የዴሞክራሲ ስርዓትና መልካም አስተዳደር ለመገንባት የህግ የበላይነት መረጋገጥ ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት አስታወቀ፡፡

የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልሉ ለሚገኙ ዳኞች በወንጀለ ቅጣት አወሳሰን በግሙሩክና በታክስ ጉዳዮች የእስራት ቅጣት ዙሪያ በቡታጅራ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡
        
የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዝዳንት አቶ ታረቀኝ አበራ እንደተናገሩት መልካም አስተዳደር ለመገንባትና ልማትን ለማፋጠን እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን ለማስቀጠል በህግ የበላይነት ላይ የተመሰረተ የፍትህ አሰጣጥ እንዲኖር የቅጣት አወሳሰን ወጥና ትክክለኛ መሆን አለበት፡፡

በወንጀል ፍትህ ስርዓት ውጤታማነትና ፍትሀዊነትን በማረጋገጥ ስራ ላይ ከዚህ በፊት የተለያዩ ችግሮች ይታዩ እንደነበር የጠቆሙት ኘሬዝዳንቱ ችግሩን ለመቅረፍ በቅጣት አወሳሰን ላይ ተቀራራቢ የሆነ የቅጣት አወሳሰን እንዲኖር እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ስልጠናው ሁሉም ዳኞች በተገቢው እውቀት ቅጣት አወሳሰድ ላይ ወጥ የሆነ ሥራ  እንዲሰሩ የሚያስችል መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በስልጠናቸው ከክልሉ የተውጣጡ የዞኑ የወረዳ የፍርድ ቤት ኘሬዝዳንቶች እንዲሁም ዳኞች ተሳታፊ ሆነዋል ሲል የጠቅላይ ፍርድ ቤት የመንግሰት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዘግቧል፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/13TikTextN105.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር