መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የህብረተሰቡን ችግር ለመፍታት የሚያደርጉት ጥረት የሚበረታታ እንደሆነ ተገለፀ፡፡


ታቦር የህፃናት ወጣቶች ልማት ድርጅት በሀዋሣ ከተማ በመናኸሪያ ክፍለ ከተማ ፒያሳ ቀበሌ ለሚገኙ 35 ህፃናት የትምህርት ቁሳቁስ በእርዳታ ሰጥቷል፡፡
በሥነ ሥርዓቱ ላይ በሀዋሣ ከተማ ጤና መምሪያ የኤች አይ ቪ ኤድስ ሚኒስትርሚኒግ ኦፊሠር አቶ መንግስቴ መኮንን እንዳሉት ድርጅቱ አቅመ ደካማ የሆኑ ህፃናትን በትምህርት በማገዝ ያደረገው ጥረት የሚበረታታ ነው ብለዋል፡፡


የድርጅቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ውብሸት ተሠማ በበኩላቸው ድርጅቱ በህፃናት በትምህርት ቁሳቁስ ችግር ሳቢያ ከትምህርታቸው እንዳይስተጓጐሉ የሚያደርጉትን ጥረት በቀጣይም በሌሎችም ተግባራትም አጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
የፒያሳ ቀበሌ ዋና ሥራ አሰኪያጅ አቶ መካሻ ሳሙኤል እንዳሉት ድርጅቱ በወላጆቻቸው ችግር ሳቢያ ትምህርታቸውን መማር ላልቻሉ ህፃናት ያደረገው ተግባር በአርአያነት የሚጠቀስ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
የህፃናቱ ወላጆች በተደረገላቸው የትምህርት ቁሳቁስ  ድጋፍ መደሰታቸውን ባልደረባችን ታሪኩ ለገሰ ዘግቧል፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/16MesTextN105.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር